قَالَ ءَامَنتُمْ لَهُۥ قَبْلَ أَنْ ءَاذَنَ لَكُمْ إِنَّهُۥ لَكَبِيرُكُمُ ٱلَّذِى عَلَّمَكُمُ ٱلسِّحْرَ فَلَأُقَطِّعَنَّ أَيْدِيَكُمْ وَأَرْجُلَكُم مِّنْ خِلَٰفٍ وَلَأُصَلِّبَنَّكُمْ فِى جُذُوعِ ٱلنَّخْلِ وَلَتَعْلَمُنَّ أَيُّنَآ أَشَدُّ عَذَابًا وَأَبْقَىٰ
Amharic Translation - Africa Academy71. (ፈርዖንም) «ለእናንተ ሳልፈቅድላችሁ በፊት ለእርሱ አመናችሁለትን! እርሱ በእርግጥ ያ ድግምትን ያስተማራችሁ መሪያችሁ ነው:: እጆቻችሁንና እግሮቻችሁን (በማናጋት) ግራንና ቀኝን በማፈራረቅ እቆራርጣችኋለሁ:: በዘምባባም ግንዶች ላይ እሰቅላችኋለሁ:: የማንኛችን ቅጣት በጣም ብርቱና የሚቆይ መሆኑን በዚያ ጊዜ ታውቃላችሁ።» አላቸው።
Amharic Translation - Muhammad Sadiq(ፈርዖንም) «ለእናንተ ሳልፈቅድላችሁ በፊት ለእርሱ አመናችሁን? እርሱ በእርግጥ ያ ድግምትን ያስተማራችሁ ትልቃችሁ ነው፡፡ እጆቻችሁንና እግሮቻችሁን በማናጋት (ግራናቀኝን በማፈራረቅ) እቆራርጣችኋለሁ፡፡ በዘምባባም ግንዶች ለይ እሰቅላችኋለሁ፡፡ ማንኛችንም ቅጣቱ በጣም ብርቱ የሚቆይም መኾኑን ታውቃላችሁ» አላቸው፡፡