وَرَٰوَدَتْهُ ٱلَّتِى هُوَ فِى بَيْتِهَا عَن نَّفْسِهِۦ وَغَلَّقَتِ ٱلْأَبْوَٰبَ وَقَالَتْ هَيْتَ لَكَ قَالَ مَعَاذَ ٱللَّهِ إِنَّهُۥ رَبِّىٓ أَحْسَنَ مَثْوَاىَ إِنَّهُۥ لَا يُفْلِحُ ٱلظَّٰلِمُونَ
Amharic Translation - Africa Academy23. ያችም እርሱ በቤትዋ የነበረባት ሴት ከነፍሱ አባበለችው:: ደጃፎቹንም ዘጋችና «ይኸው ላንተ ተዘጋጂቼልሃለሁና ቶሎ በል» አለችው:: እሱም «ከዚህ ጸያፍ ተግባር በአላህ እጠበቃለሁ:: እርሱ የገዘኝ ጌታዬ ኑሮዬን ያሳመረልኝ ነውና አልከዳዉም:: እነሆ በደለኞች ሁሉ አይድኑምና» አላት።
Amharic Translation - Muhammad Sadiqያቺም እርሱ በቤቷ የነበረባት (ሴት) ከነፍሱ አባበለችው፡፡ ደጃፎቹንም ዘጋች፤ «ላንተ ተዘጋጅቼልሃለሁና ቶሎ ናም» አለችው፡፡ «በአላህ እጠበቃለሁ እርሱ (የገዛኝ) ጌታዬ ኑሮዬን ያሳመረልኝ ነውና፤ (አልከዳውም)፡፡ እነሆ! በደለኞች አይድኑም» አላት፡፡