وَقَالَ ٱلَّذِى ٱشْتَرَىٰهُ مِن مِّصْرَ لِٱمْرَأَتِهِۦٓ أَكْرِمِى مَثْوَىٰهُ عَسَىٰٓ أَن يَنفَعَنَآ أَوْ نَتَّخِذَهُۥ وَلَدًا وَكَذَٰلِكَ مَكَّنَّا لِيُوسُفَ فِى ٱلْأَرْضِ وَلِنُعَلِّمَهُۥ مِن تَأْوِيلِ ٱلْأَحَادِيثِ وَٱللَّهُ غَالِبٌ عَلَىٰٓ أَمْرِهِۦ وَلَٰكِنَّ أَكْثَرَ ٱلنَّاسِ لَا يَعْلَمُونَ
Amharic Translation - Africa Academy21. ያም ከምስር የገዛው ሰው ለሚስቱ «ይህ ልጅ መኖሪያውን አክብሪ ሊጠቅመን ወይም ልጅ አድርገን ልንይዘው ይከጅላልና።» አላት:: ልክ እንደዚሁ ለዩሱፍ ገዥ ልናደርገውና የሕልሞችንም ፍች ልናስተምረው በምድር ላይ አስመቸነው:: አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ አሸናፊ ነው። ግን አብዛኞቹ ሰዎች ይህን አያውቁም::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqያም ከምስር የገዛው ሰው ለሚስቱ «መኖሪያውን አክብሪ፡፡ ሊጠቅመን ወይም ልጅ አድርገን ልንይዘው ይከጀላልና» አላት፡፡ እንደዚሁም ለዩሱፍ (ገዥ ልናደርገውና) የሕልሞችንም ፍች ልናስተምረው በምድር ላይ አስመቸነው፡፡ አላህም በነገሩ ላይ አሸናፊ ነው፤ ግን አብዛኛዎቹ ሰዎች አያውቁም፡፡