caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Yusuf፣ አንቀጽ 80

መካ · የወረደበት ቅደም ተከተል 53 · 12:80

فَلَمَّا ٱسْتَيْـَٔسُوا۟ مِنْهُ خَلَصُوا۟ نَجِيًّا قَالَ كَبِيرُهُمْ أَلَمْ تَعْلَمُوٓا۟ أَنَّ أَبَاكُمْ قَدْ أَخَذَ عَلَيْكُم مَّوْثِقًا مِّنَ ٱللَّهِ وَمِن قَبْلُ مَا فَرَّطتُمْ فِى يُوسُفَ فَلَنْ أَبْرَحَ ٱلْأَرْضَ حَتَّىٰ يَأْذَنَ لِىٓ أَبِىٓ أَوْ يَحْكُمَ ٱللَّهُ لِى وَهُوَ خَيْرُ ٱلْحَٰكِمِينَ

Amharic Translation - Africa Academy80. ከእርሱም ተስፋን በቆረጡ ጊዜ የሚመካከሩ ሆነው ገለል አሉ:: ታላቃቸውም አለ: «አባታችሁ በእናንተ ላይ ከአላህ የሆነን መተማመኛ ቃል ኪዳን በእርግጥ የያዘባችሁ መሆኑንና ከዚህም በፊት በዩሱፍ ላይ ግፍ የሠራችሁትን አታውቁምን? ስለዚህ አባቴ ለእኔ እስከሚፈቅድልኝ ወይም አላህ ለእኔ እስከሚፈርድልኝ ድረስ የምስርን (የግብጽን) ምድር አልለይም:: እርሱ ከፈራጆች ሁሉ በላጭ ነው።
Amharic Translation - Muhammad Sadiqከርሱም ተስፋን በቆረጡ ጊዜ የሚመካከሩ ሆነው ገለል አሉ፡፡ ታላቃቸው አለ «አባታቸሁ በናንተ ላይ ከአላህ የሆነን መታመኛ ኪዳን በእርግጥ የያዘባችሁ መሆኑን ከዚህም በፊት በዩሱፍ ላይ ግፍ የሠራችሁትን አታውቁምን? ስለዚህ አባቴ ለእኔ እስከሚፈቅድልኝ ወይም አላህ ለኔ እስከሚፈርድልኝ ድረስ (የምስርን) ምድር አልለይም፡፡ እርሱም ከፈራጆች ሁሉ በላጭ ነው፡፡
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70