قَالَ لَا يَأْتِيكُمَا طَعَامٌ تُرْزَقَانِهِۦٓ إِلَّا نَبَّأْتُكُمَا بِتَأْوِيلِهِۦ قَبْلَ أَن يَأْتِيَكُمَا ذَٰلِكُمَا مِمَّا عَلَّمَنِى رَبِّىٓ إِنِّى تَرَكْتُ مِلَّةَ قَوْمٍ لَّا يُؤْمِنُونَ بِٱللَّهِ وَهُم بِٱلْـَٔاخِرَةِ هُمْ كَٰفِرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy37. ዩሱፍም አለ: «ማንኛዉም የምትሰጡት ምግብ ለእናንተ ከመምጣቱ በፊት ፍችውን የምነግራችሁ ቢሆን እንጂ አይመጣላችሁም:: ይህ ጉዳይ ጌታዬ ካሳወቀኝ ነገር ነው:: እኔም በአላህ የማያምኑትንና በመጨረሻይቱ ዓለም ከሓዲያን የሆኑ ሕዝቦችን ሃይማኖት ትቻለሁ::
Amharic Translation - Muhammad Sadiq(ዩሱፍም) አለ፡- «ማንኛውም የምትስሰጡት ምግብ ለናንተ ከመምጣቱ በፊት ፍቹን የምነግራችሁ ቢሆን እንጂ አይመጣላችሁም፡፡ ይኸ ጌታዬ ካሳወቀኝ ነገር ነው፤ እኔ በአላህ የማያምኑን እነርሱም መጨረሻይቱን ዓለም እነርሱ ከሓዲዎች የሆኑትን ሕዝቦች ሃይማኖት ትቻለሁ፡፡