وَلَمَّا فَتَحُوا۟ مَتَٰعَهُمْ وَجَدُوا۟ بِضَٰعَتَهُمْ رُدَّتْ إِلَيْهِمْ قَالُوا۟ يَٰٓأَبَانَا مَا نَبْغِى هَٰذِهِۦ بِضَٰعَتُنَا رُدَّتْ إِلَيْنَا وَنَمِيرُ أَهْلَنَا وَنَحْفَظُ أَخَانَا وَنَزْدَادُ كَيْلَ بَعِيرٍ ذَٰلِكَ كَيْلٌ يَسِيرٌ
Amharic Translation - Africa Academy65. እቃቸውንም በከፈቱ ጊዜ ሸቀጣቸውን ወደ እነርሱ ተመልሶ አገኙት። «አባታችን ሆይ! ምን እንፈልጋለን? ይህች ሸቀጣችን ናት ወደ እኛ ተመልሳልናለች እንረዳባታለን:: ለቤተሰቦቻችንም እንሸምታለን። ወንድማችንንም እንጠብቃለን:: የአንድ ግመልን ጭነትም እንጨምራለን:: ይህ በንጉሱ ላይ ቀላል ስፍር ነው።» አሉ።
Amharic Translation - Muhammad Sadiqዕቃቸውንም በከፈቱ ጊዜ ሸቀጣቸው ወደእነርሱ ተመልሳ አገኙ፡፡ ፡-«አባታችን ሆይ! ምን እንፈልጋለን ይህቺ ሸቀጣችን ናት፡፡ ወደኛ ተመልሳልናለች፤ (እንረዳባታለን)፡፡ ለቤተሰቦቻችንም እንሸምታለን፡፡ ወንድማችንንም እንጠብቃለን፡፡ የግመልንም ጭነት እንጨምራለን፡፡ ይህ (በንጉሡ ላይ) ቀላል ስፍር ነው» አሉ፡፡