قَالُوٓا۟ إِن يَسْرِقْ فَقَدْ سَرَقَ أَخٌ لَّهُۥ مِن قَبْلُ فَأَسَرَّهَا يُوسُفُ فِى نَفْسِهِۦ وَلَمْ يُبْدِهَا لَهُمْ قَالَ أَنتُمْ شَرٌّ مَّكَانًا وَٱللَّهُ أَعْلَمُ بِمَا تَصِفُونَ
Amharic Translation - Africa Academy77. «እርሱ ቢሰርቅ ከአሁን በፊት የእርሱው ወንድም በእርግጥ ሰርቋል።» አሉ። ዩሱፍም ይህችን (አስቀያሚ ንግግር) በነፍሱ ውስጥ ደበቃት:: ለእነርሱም አልገለጣትም። በልቡ «እናንተ ሥራችሁ የከፋ ነው:: አላህ የምትሉትን ሁሉ ይበልጥ አዋቂ ነው።» አለ።
Amharic Translation - Muhammad Sadiq«ቢሰርቅ ከአሁን በፊት የርሱው ወንድም በእርግጥ ሰርቋል» አሉ፡፡ ዩሱፍም (ይህችን ንግግር) በነፍሱ ውስጥ ደበቃት፡፡ ለእነሱም አልገለጣትም፡፡ (በልቡ) «እናንተ ሥራችሁ የከፋ ነው፡፡ አላህም የምትሉትን ሁሉ ይበልጥ ዐዋቂ ነው» አለ፡፡