caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Yusuf፣ አንቀጽ 31

መካ · የወረደበት ቅደም ተከተል 53 · 12:31

فَلَمَّا سَمِعَتْ بِمَكْرِهِنَّ أَرْسَلَتْ إِلَيْهِنَّ وَأَعْتَدَتْ لَهُنَّ مُتَّكَـًٔا وَءَاتَتْ كُلَّ وَٰحِدَةٍ مِّنْهُنَّ سِكِّينًا وَقَالَتِ ٱخْرُجْ عَلَيْهِنَّ فَلَمَّا رَأَيْنَهُۥٓ أَكْبَرْنَهُۥ وَقَطَّعْنَ أَيْدِيَهُنَّ وَقُلْنَ حَٰشَ لِلَّهِ مَا هَٰذَا بَشَرًا إِنْ هَٰذَآ إِلَّا مَلَكٌ كَرِيمٌ

Amharic Translation - Africa Academy31. እርሷም ሐሜታቸውን በሰማች ጊዜ ወደነሱ ላከችባቸው:: ግብዣንም ለእነርሱ አዘጋጀችላቸው:: ለያንዳንዳቸዉም ቢላዋን ሰጠችና «በእነርሱም ላይ ውጣ።» አለችው:: እነርሱም በተመለከቱት ጊዜ በጣም አደነቁት:: እጆቻቸዉንም ቆረጡ። «ለአላህ ጥራት ይገባው:: ይህ ሰው አይደለም:: ይህ የተከበረ መልአክ እንጂ ሌላ አይደለም።» አሉ።
Amharic Translation - Muhammad Sadiqሀሜታቸውንም በሰማች ጊዜ ወደነሱ ላከችባቸው፡፡ ምግብንም ለእነርሱ አዘጋጀችላቸው፡፡ ከእነሱ ለያንዳንዳቸውም ቢላዋን ሰጠች፡፡ በእነሱም ላይ «ውጣ» አለችው፡፡ ባዩትም ጊዜ አደነቁት፡፡ እጆቻቸውንም ቆረጡ፡፡ አላህም ጥራት ይገባው፡፡ ይህ ሰው አይደለም፡፡ ይህ ያማረ መልአክ እንጅ ሌላ አይደለም አሉ፡፡
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70