فَبَدَأَ بِأَوْعِيَتِهِمْ قَبْلَ وِعَآءِ أَخِيهِ ثُمَّ ٱسْتَخْرَجَهَا مِن وِعَآءِ أَخِيهِ كَذَٰلِكَ كِدْنَا لِيُوسُفَ مَا كَانَ لِيَأْخُذَ أَخَاهُ فِى دِينِ ٱلْمَلِكِ إِلَّآ أَن يَشَآءَ ٱللَّهُ نَرْفَعُ دَرَجَٰتٍ مَّن نَّشَآءُ وَفَوْقَ كُلِّ ذِى عِلْمٍ عَلِيمٌ
Amharic Translation - Africa Academy76. ምርመራውን ከወንድሙ እቃ በፊትም በእቃዎቻቸው ጀመረ:: ከዚያ ዋንጫይቱን ከወንድሙ እቃ ውስጥ አወጣት። ልክ እንደዚሁ ለዩሱፍ ብልሃትን አስተማርነው:: አላህ ባልሻ ኖሮ በንጉሱ ሕግ ወንድሙን ሊይዝ አይገባዉም ነበር:: የምንሻውን ሰው በደረጃዎች ከፍ እናደርጋለን። ከእውቀት ባለቤቶች ሁሉ በላይም አዋቂ አለ::
Amharic Translation - Muhammad Sadiq(ምርመራውን) ከወንድሙም ዕቃ በፊት በዕቃዎቻቸው ጀመረ፡፡ ከዚያም (ዋንጫይቱን) ከወንድሙ ዕቃ ውስጥ አወጣት፡፡ እንደዚሁ ለዩሱፍ ብልሃትን አስተማርነው፡፡ አላህ ባልሻ ኖሮ በንጉሡ ሕግ ወንድሙን ሊይዝ አይገባውም ነበር፡፡ የምንሻውን ሰው በደረጃዎች ከፍ እናደርጋለን፡፡ ከዕውቀት ባለቤቶች ሁሉ በላይም ዐዋቂ አልለ፡፡