قَالَ مَا خَطْبُكُنَّ إِذْ رَٰوَدتُّنَّ يُوسُفَ عَن نَّفْسِهِۦ قُلْنَ حَٰشَ لِلَّهِ مَا عَلِمْنَا عَلَيْهِ مِن سُوٓءٍ قَالَتِ ٱمْرَأَتُ ٱلْعَزِيزِ ٱلْـَٰٔنَ حَصْحَصَ ٱلْحَقُّ أَنَا۠ رَٰوَدتُّهُۥ عَن نَّفْسِهِۦ وَإِنَّهُۥ لَمِنَ ٱلصَّٰدِقِينَ
Amharic Translation - Africa Academy51. ንጉሡም «ዩሱፍን ከነፍሱ ባባበላችሁት ጊዜ ነገራችሁ ምንድን ነው?» አላቸው። «ለአላህ ጥራት ይገባው በእርሱ ላይ ምንም መጥፎን ነገር አላወቅንም (አላየንም)።» አሉት። የዐዚዝ ሚስትም አለች: «አሁን እውነቱ ተገለጸ እኔ አባበልኩት እርሱም ከእውነተኞቹ ነው።
Amharic Translation - Muhammad Sadiq(ንጉሡም)፡- «ዩሱፍን ከነፍሱ ባባበላችሁት ጊዜ ነገራችሁ ምንድን ነው» አላቸው፡፡ «ለአላህ ጥራት ይገባው፡፡ በእርሱ ላይ ምንም መጥፎን ነገር አላወቅንም» አሉት፡፡ የዐዚዝ ሚስት፡-«አሁን እውነቱ ተገለጸ፡፡ እኔ ከነፍሱ አባበልኩት፡፡ እርሱም ከእውነተኞቹ ነው» አለች፡፡