ሱረቱ Faatir فاطر
45 አንቀጾች · መካ · የወረደበት ቅደም ተከተል 43
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ ٱلْحَمْدُ لِلَّهِ فَاطِرِ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِ جَاعِلِ ٱلْمَلَٰٓئِكَةِ رُسُلًا أُو۟لِىٓ أَجْنِحَةٍ مَّثْنَىٰ وَثُلَٰثَ وَرُبَٰعَ يَزِيدُ فِى ٱلْخَلْقِ مَا يَشَآءُ إِنَّ ٱللَّهَ عَلَىٰ كُلِّ شَىْءٍ قَدِيرٌ
Amharic Translation - Africa Academy1. ምስጋና ሁሉ ሰማያትንና ምድርን ፈጣሪ፤ መላእክትንም ባለ ሁለት ሁለት፤ ባለ ሶስት ሶስትና ባለ አራት አራት ክንፎች የሆኑ መላዕክተኞች አድራጊ ለሆነው አላህ ይገባው:: በፍጥረቱ ውስጥ የሚሻውን ይጨምራል:: አላህ በሁሉ ነገር ላይ ቻይ ነውና።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
مَّا يَفْتَحِ ٱللَّهُ لِلنَّاسِ مِن رَّحْمَةٍ فَلَا مُمْسِكَ لَهَا وَمَا يُمْسِكْ فَلَا مُرْسِلَ لَهُۥ مِنۢ بَعْدِهِۦ وَهُوَ ٱلْعَزِيزُ ٱلْحَكِيمُ
Amharic Translation - Africa Academy2. አላህ ለሰዎች ከችሮታ የሚከፍታትን ለእርሷ ምንም አጋጅ የላትም:: የሚያግደዉም ከእርሱ በኋላ ለእርሱ ምንም ለቃቂ የለዉም:: እርሱ ብቸኛ አሸናፊና ጥበበኛ ው ነውና።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
يَٰٓأَيُّهَا ٱلنَّاسُ ٱذْكُرُوا۟ نِعْمَتَ ٱللَّهِ عَلَيْكُمْ هَلْ مِنْ خَٰلِقٍ غَيْرُ ٱللَّهِ يَرْزُقُكُم مِّنَ ٱلسَّمَآءِ وَٱلْأَرْضِ لَآ إِلَٰهَ إِلَّا هُوَ فَأَنَّىٰ تُؤْفَكُونَ
Amharic Translation - Africa Academy3. እናንተ ሰዎች ሆይ! በእናንተ ላይ (ያለውን) የአላህን ጸጋ አስታውሱ፡፡ ከአላህ ሌላ ፈጣሪ አለን? ከሰማይና ከምድርም ሲሳይን የሚሰጣችሁ አለን? ከእርሱ በስተቀር አምላክ (ሰጪም) የለም፡፡ ታዲያ ወዴት ትዞራላችሁ፡፡
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَإِن يُكَذِّبُوكَ فَقَدْ كُذِّبَتْ رُسُلٌ مِّن قَبْلِكَ وَإِلَى ٱللَّهِ تُرْجَعُ ٱلْأُمُورُ
Amharic Translation - Africa Academy4. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ቢያስተባብሉህም ካንተ በፊት የነበሩ ነብያትም ህዝቦቻቸው አስተባብለዋቸዋል:: የሁሉ ነገር መመለሻ ወደ አላህ ብቻ ነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
يَٰٓأَيُّهَا ٱلنَّاسُ إِنَّ وَعْدَ ٱللَّهِ حَقٌّ فَلَا تَغُرَّنَّكُمُ ٱلْحَيَوٰةُ ٱلدُّنْيَا وَلَا يَغُرَّنَّكُم بِٱللَّهِ ٱلْغَرُورُ
Amharic Translation - Africa Academy5. (እናንተ ሰዎች ሆይ!) የአላህ ቀጠሮ እውነት ነው:: እናም የቅርቢቱም ህይወት አታታላችሁ:: አታላዩም (ሰይጣን) በአላህ ላይ አያታላችሁ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِنَّ ٱلشَّيْطَٰنَ لَكُمْ عَدُوٌّ فَٱتَّخِذُوهُ عَدُوًّا إِنَّمَا يَدْعُوا۟ حِزْبَهُۥ لِيَكُونُوا۟ مِنْ أَصْحَٰبِ ٱلسَّعِيرِ
Amharic Translation - Africa Academy6. ሰይጣን ለእናንተ የለየለት ጠላት ነውና ስለዚህ እሱን ጠላት አድርጋችሁ ያዙት:: ሰይጣን ተከታዮቹን የሚጠራው ከእሳት ጓዶች እንዲሆኑ ብቻ ነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ لَهُمْ عَذَابٌ شَدِيدٌ وَٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ وَعَمِلُوا۟ ٱلصَّٰلِحَٰتِ لَهُم مَّغْفِرَةٌ وَأَجْرٌ كَبِيرٌ
Amharic Translation - Africa Academy7. እነዚያ በአላህ የካዱት ለእነርሱ ብርቱ ቅጣት አለባቸው:: እነዚያም በአላህ ያመኑትና በጎ ስራዎችንም የሰሩት ሁሉ ለእነርሱ በአላህ ዘንድ ምህረትና ታላቅ ምንዳ አለላቸው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَفَمَن زُيِّنَ لَهُۥ سُوٓءُ عَمَلِهِۦ فَرَءَاهُ حَسَنًا فَإِنَّ ٱللَّهَ يُضِلُّ مَن يَشَآءُ وَيَهْدِى مَن يَشَآءُ فَلَا تَذْهَبْ نَفْسُكَ عَلَيْهِمْ حَسَرَٰتٍ إِنَّ ٱللَّهَ عَلِيمٌۢ بِمَا يَصْنَعُونَ
Amharic Translation - Africa Academy8. መጥፎ ሥራው የተሸለመለትና መልካም አድርጎ ያየው ሰው (አላህ እንዳቀናው ሰው ነውን?) አላህም የሚሻውን ሰው ያጠምማል፡፡ የሚሻውንም ያቀናል፡፡ ስለዚህ በእነርሱ ላይ (ባለመቅናታቸው) ስለመቆላጨት ነፍስህ አትጥፋ፡፡ አላህ የሚሠሩትን ሁሉ ዐዋቂ ነውና፡፡
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَٱللَّهُ ٱلَّذِىٓ أَرْسَلَ ٱلرِّيَٰحَ فَتُثِيرُ سَحَابًا فَسُقْنَٰهُ إِلَىٰ بَلَدٍ مَّيِّتٍ فَأَحْيَيْنَا بِهِ ٱلْأَرْضَ بَعْدَ مَوْتِهَا كَذَٰلِكَ ٱلنُّشُورُ
Amharic Translation - Africa Academy9. አላህም ያ ንፋሶችን የላከ ነው:: ከዚያም ዳመናዎችን ትቀሰቅሳለች። ወደ ሙት (ድርቅ) አገርም እንነዳዋለን:: በእርሱም ምድርን ከሞተች በኋላ ህያው እናደርጋታለን:: ሙታንንም መቀስቀስ ልክ እነደዚሁ ነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
مَن كَانَ يُرِيدُ ٱلْعِزَّةَ فَلِلَّهِ ٱلْعِزَّةُ جَمِيعًا إِلَيْهِ يَصْعَدُ ٱلْكَلِمُ ٱلطَّيِّبُ وَٱلْعَمَلُ ٱلصَّٰلِحُ يَرْفَعُهُۥ وَٱلَّذِينَ يَمْكُرُونَ ٱلسَّيِّـَٔاتِ لَهُمْ عَذَابٌ شَدِيدٌ وَمَكْرُ أُو۟لَٰٓئِكَ هُوَ يَبُورُ
Amharic Translation - Africa Academy10. ማሸነፍን የሚፈልግ ሰው አሸናፊነት ለአላህ ብቻ ነው። (እርሱን በመገዛት ይፈልገው):: መልካም ንግግር ወደ እርሱ (ወደ አላህ) ይወጣል:: በጎ ስራም ከፍ ያደርገዋል:: እነዚያ መጥፎ ስራዎችን የሚዶልቱ ለእነርሱ ብርቱ ቅጣት አለባቸው :: የእነዚያም ተንኮል እርሱ ይጠፋል::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَٱللَّهُ خَلَقَكُم مِّن تُرَابٍ ثُمَّ مِن نُّطْفَةٍ ثُمَّ جَعَلَكُمْ أَزْوَٰجًا وَمَا تَحْمِلُ مِنْ أُنثَىٰ وَلَا تَضَعُ إِلَّا بِعِلْمِهِۦ وَمَا يُعَمَّرُ مِن مُّعَمَّرٍ وَلَا يُنقَصُ مِنْ عُمُرِهِۦٓ إِلَّا فِى كِتَٰبٍ إِنَّ ذَٰلِكَ عَلَى ٱللَّهِ يَسِيرٌ
Amharic Translation - Africa Academy11. አላህም ከአፈር ከዚያም ከፍትወት ጠብታ ፈጠራችሁ:: ከዚያም ዓይነቶች አደረጋችሁ:: የትኛዋም ሴት አታረግዝም አትወልድምም በእውቀቱ ቢሆን አንጂ:: እድሜው ከሚረዝምለትም አንድም አይረዘምለትም ከእድሜዉም አይጎድልበትም በመጽሀፉ ውስጥ ያለ ቢሆን እንጂ:: ይህ በአላህ ላይ ገር ነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَمَا يَسْتَوِى ٱلْبَحْرَانِ هَٰذَا عَذْبٌ فُرَاتٌ سَآئِغٌ شَرَابُهُۥ وَهَٰذَا مِلْحٌ أُجَاجٌ وَمِن كُلٍّ تَأْكُلُونَ لَحْمًا طَرِيًّا وَتَسْتَخْرِجُونَ حِلْيَةً تَلْبَسُونَهَا وَتَرَى ٱلْفُلْكَ فِيهِ مَوَاخِرَ لِتَبْتَغُوا۟ مِن فَضْلِهِۦ وَلَعَلَّكُمْ تَشْكُرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy12. ሁለቱ ባህሮች አይስተካከሉም ይህ ጣፋጭ፤ ጥምን ቆራጭ መጠጡ በገር ተዋጭ ነው:: ይህኛው ደግሞ ጨው መርጋጋ ነው:: ከሁሉም እርጥብ ስጋን ትበላላችሁ:: የምትለብሷትንም ጌጥ ታወጣላችሁ። ከችሮታው ልትፈልጉና ልታመሰግኑትም መርከቦችን በእርሱ ውስጥ ውሃውን ቀዳጆች ሆነው ሲንሻለሉ ታያለህ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
يُولِجُ ٱلَّيْلَ فِى ٱلنَّهَارِ وَيُولِجُ ٱلنَّهَارَ فِى ٱلَّيْلِ وَسَخَّرَ ٱلشَّمْسَ وَٱلْقَمَرَ كُلٌّ يَجْرِى لِأَجَلٍ مُّسَمًّى ذَٰلِكُمُ ٱللَّهُ رَبُّكُمْ لَهُ ٱلْمُلْكُ وَٱلَّذِينَ تَدْعُونَ مِن دُونِهِۦ مَا يَمْلِكُونَ مِن قِطْمِيرٍ
Amharic Translation - Africa Academy13. ሌሊትን በቀን ውስጥ ያስገባል:: ቀንንም በሌሊት ውስጥ ያስገባል:: ጸሀይንና ጨረቃንም ገራ:: ሁሉም እስከ ተወሰነለት ጊዜ ድረስ ይሮጣል :: ይህን የሚያደርገው ጌታችሁ አላህ ብቻ ነው :: ንግስናው የእሱ ብቻ ነው:: እነዚያም ከእርሱ ሌላ የምትገዟቸው የተምር ፍሬ ሽፋን ያህል እንኳን አይኖራቸዉም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِن تَدْعُوهُمْ لَا يَسْمَعُوا۟ دُعَآءَكُمْ وَلَوْ سَمِعُوا۟ مَا ٱسْتَجَابُوا۟ لَكُمْ وَيَوْمَ ٱلْقِيَٰمَةِ يَكْفُرُونَ بِشِرْكِكُمْ وَلَا يُنَبِّئُكَ مِثْلُ خَبِيرٍ
Amharic Translation - Africa Academy14. ብትጠሩዋቸው ጥሪያችሁን አይሰሙም:: ቢሰሙም ኖሮ ለእናንተ አይመልሱላችሁም:: በትንሳኤም ቀን እነርሱን በአላህ ማጋራታችሁን ይክዳሉ። እንደ ውስጠ አዋቂው አላህ ማንም አይነግርህም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
يَٰٓأَيُّهَا ٱلنَّاسُ أَنتُمُ ٱلْفُقَرَآءُ إِلَى ٱللَّهِ وَٱللَّهُ هُوَ ٱلْغَنِىُّ ٱلْحَمِيدُ
Amharic Translation - Africa Academy15. እናንተ ሰዎች ሆይ! እናንተ ሁል ጊዜ ወደ አላህ ከጃዮች ናችሁ:: አላህም እርሱ ተብቃቂውና ምስጉኑ ነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِن يَشَأْ يُذْهِبْكُمْ وَيَأْتِ بِخَلْقٍ جَدِيدٍ
Amharic Translation - Africa Academy16. (አላህ) ቢሻ ያስወግዳችሁና አዲስን ፍጡር ያመጣል (ይፈጥራል)::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَمَا ذَٰلِكَ عَلَى ٱللَّهِ بِعَزِيزٍ
Amharic Translation - Africa Academy17. ይህም በአላህ ላይ ምንም አስቸጋሪ አይደለም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلَا تَزِرُ وَازِرَةٌ وِزْرَ أُخْرَىٰ وَإِن تَدْعُ مُثْقَلَةٌ إِلَىٰ حِمْلِهَا لَا يُحْمَلْ مِنْهُ شَىْءٌ وَلَوْ كَانَ ذَا قُرْبَىٰٓ إِنَّمَا تُنذِرُ ٱلَّذِينَ يَخْشَوْنَ رَبَّهُم بِٱلْغَيْبِ وَأَقَامُوا۟ ٱلصَّلَوٰةَ وَمَن تَزَكَّىٰ فَإِنَّمَا يَتَزَكَّىٰ لِنَفْسِهِۦ وَإِلَى ٱللَّهِ ٱلْمَصِيرُ
Amharic Translation - Africa Academy18. ኃጢአትን ተሸካሚም ነፍስ የሌላውን ሸክም አትሸከምም:: የራሷ ወንጀል የከበዳትም ነፍስ እርዳታ እንዲደረግላት ብትጠራ ተጠሪው የቅርብ ዝምድና ባለቤት ቢሆንም እንኳን ከእርሷ አንድን ነገር የሚሸከምላት አታገኝም:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የምታስጠነቅቀው እነዚያን ጌታቸውን፤ በሩቅ የሚፈሩትን ሶላትንም አስተካክለው የሚሰገዱትን ብቻ ነው:: ከወንጀልም የተጥራራ ሁሉ የሚጥራራው ለራሱ ብቻ ነው:: መመለሻዉም ወደ አላህ ብቻ ነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَمَا يَسْتَوِى ٱلْأَعْمَىٰ وَٱلْبَصِيرُ
Amharic Translation - Africa Academy19. እውርና የሚያይ አይሰተካከሉም፤
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلَا ٱلظُّلُمَٰتُ وَلَا ٱلنُّورُ
Amharic Translation - Africa Academy20. ጨለማዎችና ብርሃንም፤
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلَا ٱلظِّلُّ وَلَا ٱلْحَرُورُ
Amharic Translation - Africa Academy21. ጥላና ሐሩርም።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَمَا يَسْتَوِى ٱلْأَحْيَآءُ وَلَا ٱلْأَمْوَٰتُ إِنَّ ٱللَّهَ يُسْمِعُ مَن يَشَآءُ وَمَآ أَنتَ بِمُسْمِعٍ مَّن فِى ٱلْقُبُورِ
Amharic Translation - Africa Academy22. ህያውና ሙታንም አይስተካከሉም:: አላህ የሚሻውን ሰው ያሰማል:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አንተ ግን በመቃብር ውስጥ ያሉትን አሰሚ አይደለህም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِنْ أَنتَ إِلَّا نَذِيرٌ
Amharic Translation - Africa Academy23. አንተ አስጠንቃቂ እንጂ ሌላ አይደለህም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِنَّآ أَرْسَلْنَٰكَ بِٱلْحَقِّ بَشِيرًا وَنَذِيرًا وَإِن مِّنْ أُمَّةٍ إِلَّا خَلَا فِيهَا نَذِيرٌ
Amharic Translation - Africa Academy24. እኛ አብሳሪና አስፈራሪ አድርገን በእውነቱ መምሪያ ላክንህ:: ማንኛይቱም ህዝብ በውስጧ አስፈራሪ ያላለፈባት የለችም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَإِن يُكَذِّبُوكَ فَقَدْ كَذَّبَ ٱلَّذِينَ مِن قَبْلِهِمْ جَآءَتْهُمْ رُسُلُهُم بِٱلْبَيِّنَٰتِ وَبِٱلزُّبُرِ وَبِٱلْكِتَٰبِ ٱلْمُنِيرِ
Amharic Translation - Africa Academy25. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ቢያስተባብሉህም ከእነዚህ ከበፊታቸው የነበሩትም ህዝቦች በእርግጥ ነብያትን አስተባብለዋል:: መልዕክተኞቻቸው በግልጽ ማስረጃዎች፣ በጹሁፎችም አብራሪ በሆነ መጽሐፍም መጥተዋቸዋል::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ثُمَّ أَخَذْتُ ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ فَكَيْفَ كَانَ نَكِيرِ
Amharic Translation - Africa Academy26. ከዚያም እነዚያን የካዱትን ቀጣኋቸው:: ቅጣቴም እንዴት ነበር! (በስፍራው ነው ተገቢ ነው)።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَلَمْ تَرَ أَنَّ ٱللَّهَ أَنزَلَ مِنَ ٱلسَّمَآءِ مَآءً فَأَخْرَجْنَا بِهِۦ ثَمَرَٰتٍ مُّخْتَلِفًا أَلْوَٰنُهَا وَمِنَ ٱلْجِبَالِ جُدَدٌۢ بِيضٌ وَحُمْرٌ مُّخْتَلِفٌ أَلْوَٰنُهَا وَغَرَابِيبُ سُودٌ
Amharic Translation - Africa Academy27. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አላህ ከሰማይ ውሃን ማውረዱን አላየህምን? በእርሱም ዓይነቶቻቸው የተለያዩ ፍሬዎችን አወጣን:: ከጋራዎችም መልካቸው የተለያዩ ነጮችም፤ ቀዮችም፤ በጣም ጥቁሮችም የሆኑ መንገዶች አሉ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَمِنَ ٱلنَّاسِ وَٱلدَّوَآبِّ وَٱلْأَنْعَٰمِ مُخْتَلِفٌ أَلْوَٰنُهُۥ كَذَٰلِكَ إِنَّمَا يَخْشَى ٱللَّهَ مِنْ عِبَادِهِ ٱلْعُلَمَٰٓؤُا۟ إِنَّ ٱللَّهَ عَزِيزٌ غَفُورٌ
Amharic Translation - Africa Academy28. ከሰዎችም፤ ከተንቀሳቃሾችም፤ ከቤት እንስሳዎችም እንደዚሁ መልኮቻቸው የተለያዩ አሉ:: አላህን ከባሮቹ ውስጥ የሚፈሩት አዋቂዎቹ ብቻ ናቸው:: አላህ አሸናፊና መሃሪ ነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِنَّ ٱلَّذِينَ يَتْلُونَ كِتَٰبَ ٱللَّهِ وَأَقَامُوا۟ ٱلصَّلَوٰةَ وَأَنفَقُوا۟ مِمَّا رَزَقْنَٰهُمْ سِرًّا وَعَلَانِيَةً يَرْجُونَ تِجَٰرَةً لَّن تَبُورَ
Amharic Translation - Africa Academy29. እነዚያ የአላህን መጽሐፍ የሚያነቡ፣ ሶላትን አስተካክለው የሰገዱ፤ ከሰጠናቸዉም ሲሳይ በምስጢርም ሆነ በግልጽ የለገሱ የማትከስርን ንግድ ተስፋ ያደርጋሉ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
لِيُوَفِّيَهُمْ أُجُورَهُمْ وَيَزِيدَهُم مِّن فَضْلِهِۦٓ إِنَّهُۥ غَفُورٌ شَكُورٌ
Amharic Translation - Africa Academy30. ምንዳዎቻቸውን ሊሞላላቸው ከችሮታዉም ሊጨምርላቸው ተስፋ ያደርጋሉ:: እርሱ በጣም መሃሪና አመስጋኝ ነውና::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَٱلَّذِىٓ أَوْحَيْنَآ إِلَيْكَ مِنَ ٱلْكِتَٰبِ هُوَ ٱلْحَقُّ مُصَدِّقًا لِّمَا بَيْنَ يَدَيْهِ إِنَّ ٱللَّهَ بِعِبَادِهِۦ لَخَبِيرٌۢ بَصِيرٌ
Amharic Translation - Africa Academy31. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ያ ከመጽሐፉ ወደ አንተ ያወረድነው ከበፊቱ ላለው አረጋጋጭ ሲሆን እርሱ እውነት ነው:: አላህ በእርግጥ በባሮቹ ውስጥ አዋቂና ተመልካች ነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ثُمَّ أَوْرَثْنَا ٱلْكِتَٰبَ ٱلَّذِينَ ٱصْطَفَيْنَا مِنْ عِبَادِنَا فَمِنْهُمْ ظَالِمٌ لِّنَفْسِهِۦ وَمِنْهُم مُّقْتَصِدٌ وَمِنْهُمْ سَابِقٌۢ بِٱلْخَيْرَٰتِ بِإِذْنِ ٱللَّهِ ذَٰلِكَ هُوَ ٱلْفَضْلُ ٱلْكَبِيرُ
Amharic Translation - Africa Academy32. ከዚያ እነዚያ ከባሮቻችን የመረጥናቸውን መጽሐፉን አወረስናቸው :: ከእነርሱም ነፍሱን በዳይ አለ:: ከእነርሱም መካከለኛ አለ:: ከእነርሱም በአላህ ፈቃድ በበጎ ስራዎች ቀዳሚ አለ:: ያንኑ ማውረስ እርሱ ታላቅ ችሮታ ነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
جَنَّٰتُ عَدْنٍ يَدْخُلُونَهَا يُحَلَّوْنَ فِيهَا مِنْ أَسَاوِرَ مِن ذَهَبٍ وَلُؤْلُؤًا وَلِبَاسُهُمْ فِيهَا حَرِيرٌ
Amharic Translation - Africa Academy33. የመኖሪያ ገነቶችን በውስጧ የወርቅ አንባሮችን ሉልንም የሚሸለሙ ሆነው ይገቡበታል:: በእርሷ ውስጥ አልባሳታቸዉም ሀር ነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَقَالُوا۟ ٱلْحَمْدُ لِلَّهِ ٱلَّذِىٓ أَذْهَبَ عَنَّا ٱلْحَزَنَ إِنَّ رَبَّنَا لَغَفُورٌ شَكُورٌ
Amharic Translation - Africa Academy34. ይላሉም «ምስጋና ሁሉ ለዚያ ከእኛ ላይ ሐዘንን ላስወገደልን ይገባው። ጌታችን በጣም መሃሪና አመስጋኝ ነውና።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ٱلَّذِىٓ أَحَلَّنَا دَارَ ٱلْمُقَامَةِ مِن فَضْلِهِۦ لَا يَمَسُّنَا فِيهَا نَصَبٌ وَلَا يَمَسُّنَا فِيهَا لُغُوبٌ
Amharic Translation - Africa Academy35. እርሱም ያ ከችሮታው የዘላለም መኖሪያን አገር ያሰፈረን ነው:: በእርሷም ውስጥ መከራ አይነካንም:: በእርሷም ውስጥ ድካም አይነካንም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ لَهُمْ نَارُ جَهَنَّمَ لَا يُقْضَىٰ عَلَيْهِمْ فَيَمُوتُوا۟ وَلَا يُخَفَّفُ عَنْهُم مِّنْ عَذَابِهَا كَذَٰلِكَ نَجْزِى كُلَّ كَفُورٍ
Amharic Translation - Africa Academy36. እነዚያ በአላህ የካዱት ለእነርሱ የገሀነም እሳት አለላቸው:: ይሞቱ ዘንድም በእነርሱ ላይ ሞት አይፈረድም:: ከቅጣቷም ከእነርሱ አይቀለልላቸዉም:: ልክ እንደዚሁ ከሓዲያንን ሁሉ እንመነዳለን::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَهُمْ يَصْطَرِخُونَ فِيهَا رَبَّنَآ أَخْرِجْنَا نَعْمَلْ صَٰلِحًا غَيْرَ ٱلَّذِى كُنَّا نَعْمَلُ أَوَلَمْ نُعَمِّرْكُم مَّا يَتَذَكَّرُ فِيهِ مَن تَذَكَّرَ وَجَآءَكُمُ ٱلنَّذِيرُ فَذُوقُوا۟ فَمَا لِلظَّٰلِمِينَ مِن نَّصِيرٍ
Amharic Translation - Africa Academy37. እነርሱም በእርሷ ውስጥ እርዳታን በመፈለግ በኃይል ይጮሃሉ:: «ጌታችን ሆይ! ከእዚያ እንሠራው ከነበርነው ሌላ በጎ ሥራን እንሠራ ዘንድ አውጣን» (ይላሉ)፡፡ «በእርሱ ውስጥ ያስታወሰ ሰው የሚገሰጽበትን እድሜ አላቆየናችሁምን? አስጠንቃቂዉም መጥቶላችኋል:: አስተባብላችኋልም:: ስለዚህ ቅመሱ:: ለበደለኞችም ምንም ረዳት የላቸዉም» ይባላሉ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِنَّ ٱللَّهَ عَٰلِمُ غَيْبِ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِ إِنَّهُۥ عَلِيمٌۢ بِذَاتِ ٱلصُّدُورِ
Amharic Translation - Africa Academy38. አላህ የሰማያትንና የምድርን ምስጢር በእርግጥ አዋቂ ነው:: እርሱ በልቦች ውስጥ ያለን ሁሉ እንኳ አዋቂ ነውና::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
هُوَ ٱلَّذِى جَعَلَكُمْ خَلَٰٓئِفَ فِى ٱلْأَرْضِ فَمَن كَفَرَ فَعَلَيْهِ كُفْرُهُۥ وَلَا يَزِيدُ ٱلْكَٰفِرِينَ كُفْرُهُمْ عِندَ رَبِّهِمْ إِلَّا مَقْتًا وَلَا يَزِيدُ ٱلْكَٰفِرِينَ كُفْرُهُمْ إِلَّا خَسَارًا
Amharic Translation - Africa Academy39. (ሰዎች ሆይ!) እርሱ ያ በምድር ውስጥ ምትኮች ያደረጋችሁ ነው:: የካደም ክህደቱ በእርሱው ላይ ብቻ ነው:: ከሓዲያንም ክህደታቸው ከጌታቸው ዘንድ መጠላትን እንጂ ሌላ አይጨምርላቸዉም:: ከሓዲያንም ክህደታቸው ክስረትን እንጂ ሌላ አይጨምርላቸዉም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قُلْ أَرَءَيْتُمْ شُرَكَآءَكُمُ ٱلَّذِينَ تَدْعُونَ مِن دُونِ ٱللَّهِ أَرُونِى مَاذَا خَلَقُوا۟ مِنَ ٱلْأَرْضِ أَمْ لَهُمْ شِرْكٌ فِى ٱلسَّمَٰوَٰتِ أَمْ ءَاتَيْنَٰهُمْ كِتَٰبًا فَهُمْ عَلَىٰ بَيِّنَتٍ مِّنْهُ بَلْ إِن يَعِدُ ٱلظَّٰلِمُونَ بَعْضُهُم بَعْضًا إِلَّا غُرُورًا
Amharic Translation - Africa Academy40. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «እነዚያን ከአላህ ሌላ የምትገዟቸውን ተጋሪዎቻችሁ አያችሁን? ከምድር ምንን እንደ ፈጠሩ አሳዩኝ? ወይስ ለእነርሱ በሰማያት ውስጥ ሽርክና አላቸውን? ወይስ ለእነርሱ መፅሀፍ ሰጠናቸውና ከእርሱ በግልፅ አስረጂ ላይ ናቸውን? አይደለም በደለኞች ከፊላቸው ከፊሉን ማታለልን እንጂ አይቀጥሩም» በላቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِنَّ ٱللَّهَ يُمْسِكُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضَ أَن تَزُولَا وَلَئِن زَالَتَآ إِنْ أَمْسَكَهُمَا مِنْ أَحَدٍ مِّنۢ بَعْدِهِۦٓ إِنَّهُۥ كَانَ حَلِيمًا غَفُورًا
Amharic Translation - Africa Academy41. አላህ ሰማያትንና ምድርን እንዳይወገዱ ይይዛቸዋል:: ቢወገዱም ከእርሱ ሌላ አንድም የሚይዛቸው የለም:: እነሆ እርሱ ታጋሽና መሃሪ ነውና::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَأَقْسَمُوا۟ بِٱللَّهِ جَهْدَ أَيْمَٰنِهِمْ لَئِن جَآءَهُمْ نَذِيرٌ لَّيَكُونُنَّ أَهْدَىٰ مِنْ إِحْدَى ٱلْأُمَمِ فَلَمَّا جَآءَهُمْ نَذِيرٌ مَّا زَادَهُمْ إِلَّا نُفُورًا
Amharic Translation - Africa Academy42. አስፈራሪም ቢመጣላቸው ከህዝቦች ሁሉ ከአንደኛዋ ይበልጥ የተመሩ ሊሆኑ የመሃላቸውን ዲካ አድርሰው በአላህ ማሉ:: አስፈራሪም በመጣላቸው ጊዜ መበርገግን እንጂ ሌላ አልጨመረላቸዉም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ٱسْتِكْبَارًا فِى ٱلْأَرْضِ وَمَكْرَ ٱلسَّيِّئِ وَلَا يَحِيقُ ٱلْمَكْرُ ٱلسَّيِّئُ إِلَّا بِأَهْلِهِۦ فَهَلْ يَنظُرُونَ إِلَّا سُنَّتَ ٱلْأَوَّلِينَ فَلَن تَجِدَ لِسُنَّتِ ٱللَّهِ تَبْدِيلًا وَلَن تَجِدَ لِسُنَّتِ ٱللَّهِ تَحْوِيلًا
Amharic Translation - Africa Academy43. በምድር ላይ ኩራትንና በክፉ ተንኮል መዶለትንም እንጂ አልጨመረላቸዉም:: ክፉ ተንኮልም በባለቤቱ ላይ እንጂ በሌላ ላይ አይሰፍርም:: የቀድሞዎቹን ደንብ እንጂ ይጠብቃሉን? በመሆኑም ለአላህ ደንብ መለወጥን አታገኝም፤ ለአላህ ደንብም መዛወርን (መቀየር) አታገኝም።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَوَلَمْ يَسِيرُوا۟ فِى ٱلْأَرْضِ فَيَنظُرُوا۟ كَيْفَ كَانَ عَٰقِبَةُ ٱلَّذِينَ مِن قَبْلِهِمْ وَكَانُوٓا۟ أَشَدَّ مِنْهُمْ قُوَّةً وَمَا كَانَ ٱللَّهُ لِيُعْجِزَهُۥ مِن شَىْءٍ فِى ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَلَا فِى ٱلْأَرْضِ إِنَّهُۥ كَانَ عَلِيمًا قَدِيرًا
Amharic Translation - Africa Academy44. በምድር ላይ አይሄዱምና የእነዚያን ከእነርሱ በፊት የነበሩትን ሰዎች መጨረሻ እንዴት እንደ ነበረ አይመለከቱምን? ከእነርሱም በኃይል የበረቱ ነበሩ:: አላህም በሰማያትም ሆነ በምድር ውስጥ ምንም ነገር የሚያቅተው አይደለም:: እርሱ ሁሉን አዋቂና በሁሉ ላይ ቻይ ነውና::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلَوْ يُؤَاخِذُ ٱللَّهُ ٱلنَّاسَ بِمَا كَسَبُوا۟ مَا تَرَكَ عَلَىٰ ظَهْرِهَا مِن دَآبَّةٍ وَلَٰكِن يُؤَخِّرُهُمْ إِلَىٰٓ أَجَلٍ مُّسَمًّى فَإِذَا جَآءَ أَجَلُهُمْ فَإِنَّ ٱللَّهَ كَانَ بِعِبَادِهِۦ بَصِيرًۢا
Amharic Translation - Africa Academy45. አላህ ሰዎችን በሰሩት ኃጢአት ሁሉ ቢቀጣ ኖሮ በምድር ወለል ላይ ምንንም ተንቀሳቃሽ ባልተወ ነበር:: ግን እስከ ተወሰነ ጊዜ ድረስ ያቆያቸዋል:: ጊዜያቸዉም በመጣ ወቅት በኃጢአታቸው ይቀጣቸዋል:: አላህ በባሮቹ ሁኔታ ሁሉ ተመልካች ነውና::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
→