ሱረቱ As-Sajda السجدة
30 አንቀጾች · መካ · የወረደበት ቅደም ተከተል 75
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ الٓمٓ
Amharic Translation - Africa Academy1. አሊፍ፤ ላም፤ ሚይም፤
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
تَنزِيلُ ٱلْكِتَٰبِ لَا رَيْبَ فِيهِ مِن رَّبِّ ٱلْعَٰلَمِينَ
Amharic Translation - Africa Academy2. የመጽሐፉ መወረድ ጥርጥር የለበትም:: የወረደዉም ከዓለማቱ ጌታ ነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَمْ يَقُولُونَ ٱفْتَرَىٰهُ بَلْ هُوَ ٱلْحَقُّ مِن رَّبِّكَ لِتُنذِرَ قَوْمًا مَّآ أَتَىٰهُم مِّن نَّذِيرٍ مِّن قَبْلِكَ لَعَلَّهُمْ يَهْتَدُونَ
Amharic Translation - Africa Academy3. ይልቁንም «ቀጠፈው» ይላሉን? አይደለም:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እርሱ ከጌታህ የሆነ እውነት ነው:: በእርሱ ካንተ በፊት ከአስፈራሪ ነቢይ ያልመጣባቸውን ሕዝቦች በእርሱ ልታስፈራራበት ያወረደልህ ነው:: እነርሱ ሊመሩ ይከጀላልና::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ٱللَّهُ ٱلَّذِى خَلَقَ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضَ وَمَا بَيْنَهُمَا فِى سِتَّةِ أَيَّامٍ ثُمَّ ٱسْتَوَىٰ عَلَى ٱلْعَرْشِ مَا لَكُم مِّن دُونِهِۦ مِن وَلِىٍّ وَلَا شَفِيعٍ أَفَلَا تَتَذَكَّرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy4. አላህ ያ! ሰማያትንና ምድርን በመካከላቸውም ያለውን ሁሉ በስድስት ቀናት ውስጥ የፈጠረ ከዚያም ለክብሩ በሚስማማ መልኩ በዐርሹ ላይ ከፍ ያለ ነው:: ከእርሱ ሌላ ለእናንተ ወዳጅም አማላጅም ምንም የላችሁም:: አትገሰጹምን?
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
يُدَبِّرُ ٱلْأَمْرَ مِنَ ٱلسَّمَآءِ إِلَى ٱلْأَرْضِ ثُمَّ يَعْرُجُ إِلَيْهِ فِى يَوْمٍ كَانَ مِقْدَارُهُۥٓ أَلْفَ سَنَةٍ مِّمَّا تَعُدُّونَ
Amharic Translation - Africa Academy5. ነገሩን ሁሉ ከሰማይ ወደ ምድር ያዘጋጃል፤ ከዚያም ከምትቆጥሩት (ዘመን) ልኩ ሺህ ዓመት በሆነ ቀን ውስጥ ወደ እርሱ ይወጣል::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ذَٰلِكَ عَٰلِمُ ٱلْغَيْبِ وَٱلشَّهَٰدَةِ ٱلْعَزِيزُ ٱلرَّحِيمُ
Amharic Translation - Africa Academy6. ይህንን ያደረገው ሩቁንም ቅርቡንም ሁሉ አዋቂው፤ ሁሉን አሸናፊና አዛኙ ጌታ ነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ٱلَّذِىٓ أَحْسَنَ كُلَّ شَىْءٍ خَلَقَهُۥ وَبَدَأَ خَلْقَ ٱلْإِنسَٰنِ مِن طِينٍ
Amharic Translation - Africa Academy7. ያ የፈጠረውን ነገር ሁሉ ያሳመረው:: የሰውንም ፍጥረት ከጭቃ የጀመረው ነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ثُمَّ جَعَلَ نَسْلَهُۥ مِن سُلَٰلَةٍ مِّن مَّآءٍ مَّهِينٍ
Amharic Translation - Africa Academy8. ከዚያም ዘሮቹን ከተንጣለለ ከደካማ ውሃ የፈጠረ ነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ثُمَّ سَوَّىٰهُ وَنَفَخَ فِيهِ مِن رُّوحِهِۦ وَجَعَلَ لَكُمُ ٱلسَّمْعَ وَٱلْأَبْصَٰرَ وَٱلْأَفْـِٔدَةَ قَلِيلًا مَّا تَشْكُرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy9. ከዚያም ቅርጹን አስተካከለው:: በእርሱ ውስጥም ከመንፈሱ ነፍስ ዘራበት:: ለናንተም ጆሮዎችን ዓይኖችንና ልቦችንም አደረገላችሁ። በጣም ጥቂትን ብቻ ታመሰግናላችሁ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَقَالُوٓا۟ أَءِذَا ضَلَلْنَا فِى ٱلْأَرْضِ أَءِنَّا لَفِى خَلْقٍ جَدِيدٍۭ بَلْ هُم بِلِقَآءِ رَبِّهِمْ كَٰفِرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy10. «በምድርም ውስጥ በስብሰን በጠፋን ጊዜ እኛ በአዲስ መፈጠር ውስጥ እንሆናለን?» አሉ:: በእውነቱ እነርሱ በጌታቸው መገናኘት ከሓዲያን ናቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قُلْ يَتَوَفَّىٰكُم مَّلَكُ ٱلْمَوْتِ ٱلَّذِى وُكِّلَ بِكُمْ ثُمَّ إِلَىٰ رَبِّكُمْ تُرْجَعُونَ
Amharic Translation - Africa Academy11. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «በእናንተ ላይ የተወከለው መልአከ ሞት ይገድላችኋል:: ከዚያም ወደ ጌታችሁ ትመለሳላችሁ።» በላቸው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلَوْ تَرَىٰٓ إِذِ ٱلْمُجْرِمُونَ نَاكِسُوا۟ رُءُوسِهِمْ عِندَ رَبِّهِمْ رَبَّنَآ أَبْصَرْنَا وَسَمِعْنَا فَٱرْجِعْنَا نَعْمَلْ صَٰلِحًا إِنَّا مُوقِنُونَ
Amharic Translation - Africa Academy12. አመጸኞችም በጌታቸው ዘንድ ራሶቻቸውን ያቀረቀሩ ሆነው፡‐ «ጌታችን ሆይ! አየን። ሰማንም። መልካምን እንሠራለንና (ወደ ምድረ ዓለም) መልሰን እኛ አረጋጋጮች ነን» የሚሉ ሲሆኑ ብታይ ኖሮ( አስደንጋጭን ነገር ታይ ነበር)።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلَوْ شِئْنَا لَـَٔاتَيْنَا كُلَّ نَفْسٍ هُدَىٰهَا وَلَٰكِنْ حَقَّ ٱلْقَوْلُ مِنِّى لَأَمْلَأَنَّ جَهَنَّمَ مِنَ ٱلْجِنَّةِ وَٱلنَّاسِ أَجْمَعِينَ
Amharic Translation - Africa Academy13 በሻንም ኖሮ ነፍስን ሁሉ ቅንነቷን(እምነቷን) በሰጠናት ነበር:: ግን ገሀነምን ከአጋንንትና ከሰዎች የተሰበሰቡ ሆነው በእርግጥ እሞላለሁ ማለት ቃሉ ከእኔ ተረጋግጧል::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَذُوقُوا۟ بِمَا نَسِيتُمْ لِقَآءَ يَوْمِكُمْ هَٰذَآ إِنَّا نَسِينَٰكُمْ وَذُوقُوا۟ عَذَابَ ٱلْخُلْدِ بِمَا كُنتُمْ تَعْمَلُونَ
Amharic Translation - Africa Academy14. ይህንንም ቀናችሁን መገናኘትን በመርሳታችሁ ምክንያት ቅጣትን ቅመሱ! እኛ ተውናችሁ። ትሰሩት በነበራችሁትም ጥፋት ዘውታሪን ቅጣት ቅመሱ ይባላሉ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِنَّمَا يُؤْمِنُ بِـَٔايَٰتِنَا ٱلَّذِينَ إِذَا ذُكِّرُوا۟ بِهَا خَرُّوا۟ سُجَّدًا وَسَبَّحُوا۟ بِحَمْدِ رَبِّهِمْ وَهُمْ لَا يَسْتَكْبِرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy15. በአናቅጻችን የሚያምኑት እነዚያ በእርሷ በተገሰጹ ጊዜ ሰጋጆች ሆነው የሚወድቁትና እነርሱም የማይኮሩ ሆነው በጌታቸው ምስጋና (ተጎናጽፈው) የሚያወድሱት ሰዎች ብቻ ናቸው። {1}
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
تَتَجَافَىٰ جُنُوبُهُمْ عَنِ ٱلْمَضَاجِعِ يَدْعُونَ رَبَّهُمْ خَوْفًا وَطَمَعًا وَمِمَّا رَزَقْنَٰهُمْ يُنفِقُونَ
Amharic Translation - Africa Academy16. ጌታቸውን ለመፍራትና ለመከጀል የሚጠሩት ሆነው ጎኖቻቸው ከመጋደሚያ ቦታዎቻቸው ይርቃሉ:: ከሰጠናቸዉም ጸጋ ይለግሳሉ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَلَا تَعْلَمُ نَفْسٌ مَّآ أُخْفِىَ لَهُم مِّن قُرَّةِ أَعْيُنٍ جَزَآءًۢ بِمَا كَانُوا۟ يَعْمَلُونَ
Amharic Translation - Africa Academy17. ይሰሩት በነበሩት ለመመንዳት ከዓይኖች መርጊያ ለእነርሱ የተደበቀላቸውን ጸጋ ማንኛይቱም ነፍስ አታውቅም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَفَمَن كَانَ مُؤْمِنًا كَمَن كَانَ فَاسِقًا لَّا يَسْتَوُۥنَ
Amharic Translation - Africa Academy18. አማኝ የሆነ ሰው አመጸኛ እንደሆነ ሰው ነውን? አይስተካከሉም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَمَّا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ وَعَمِلُوا۟ ٱلصَّٰلِحَٰتِ فَلَهُمْ جَنَّٰتُ ٱلْمَأْوَىٰ نُزُلًۢا بِمَا كَانُوا۟ يَعْمَلُونَ
Amharic Translation - Africa Academy19. እነዚያ ያመኑና መልካሞችን የሰሩማ ለነሱ ይሰሩት በነበሩት ምክንያት መስተንግዶ ሲሆኑ መኖሪያ ገነቶች አሏቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَأَمَّا ٱلَّذِينَ فَسَقُوا۟ فَمَأْوَىٰهُمُ ٱلنَّارُ كُلَّمَآ أَرَادُوٓا۟ أَن يَخْرُجُوا۟ مِنْهَآ أُعِيدُوا۟ فِيهَا وَقِيلَ لَهُمْ ذُوقُوا۟ عَذَابَ ٱلنَّارِ ٱلَّذِى كُنتُم بِهِۦ تُكَذِّبُونَ
Amharic Translation - Africa Academy20. እነዚያ ያመጹትማ መኖሪያቸው እሳት ናት:: ከእርሷ መውጣትን በፈለጉ ቁጥር በእርሷ ውስጥ ይመለሳሉ ለእነርሱም «ያንን በእርሱ ታስተባብሉበት የነበራችሁትን የእሳት ቅጣት ቅመሱ» ይባላሉ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلَنُذِيقَنَّهُم مِّنَ ٱلْعَذَابِ ٱلْأَدْنَىٰ دُونَ ٱلْعَذَابِ ٱلْأَكْبَرِ لَعَلَّهُمْ يَرْجِعُونَ
Amharic Translation - Africa Academy21. ይመለሱ ዘንድ ከትልቁ ቅጣት በፊት (በዚህ ዓለም) ትንሹን ቅጣት በእርግጥ እናቀምሳቸዋለን::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَمَنْ أَظْلَمُ مِمَّن ذُكِّرَ بِـَٔايَٰتِ رَبِّهِۦ ثُمَّ أَعْرَضَ عَنْهَآ إِنَّا مِنَ ٱلْمُجْرِمِينَ مُنتَقِمُونَ
Amharic Translation - Africa Academy22. በጌታዉም አናቅጽ ከተገሰጸና ከዚያም ከተዋት ሰው ይበልጥ በደለኛ ማነው? (የለም) እኛ ከተንኮለኞቹ ሁሉ ተበቃዮች ነን::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلَقَدْ ءَاتَيْنَا مُوسَى ٱلْكِتَٰبَ فَلَا تَكُن فِى مِرْيَةٍ مِّن لِّقَآئِهِۦ وَجَعَلْنَٰهُ هُدًى لِّبَنِىٓ إِسْرَٰٓءِيلَ
Amharic Translation - Africa Academy23.ሙሳን መጽሐፍን በእርግጥ ሰጠነው:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እርሱን ከመገናኘትህም በመጠራጠር ውስጥ አትሁን:: ለኢስራኢል ልጆችም መሪ አደረግነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَجَعَلْنَا مِنْهُمْ أَئِمَّةً يَهْدُونَ بِأَمْرِنَا لَمَّا صَبَرُوا۟ وَكَانُوا۟ بِـَٔايَٰتِنَا يُوقِنُونَ
Amharic Translation - Africa Academy24. በታገሱና በተዓምራታችን የሚያረጋግጡ በሆኑም ጊዜ ከእነርሱ በትዕዛዛችን የሚመሩ መሪዎችን አደረግን::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِنَّ رَبَّكَ هُوَ يَفْصِلُ بَيْنَهُمْ يَوْمَ ٱلْقِيَٰمَةِ فِيمَا كَانُوا۟ فِيهِ يَخْتَلِفُونَ
Amharic Translation - Africa Academy25. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጌታህ በዚያ ይለያዩበት በነበሩት ነገር ሁሉ በትንሳኤ ቀን በመካከላቸው በፍርድ ይለያል::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَوَلَمْ يَهْدِ لَهُمْ كَمْ أَهْلَكْنَا مِن قَبْلِهِم مِّنَ ٱلْقُرُونِ يَمْشُونَ فِى مَسَٰكِنِهِمْ إِنَّ فِى ذَٰلِكَ لَـَٔايَٰتٍ أَفَلَا يَسْمَعُونَ
Amharic Translation - Africa Academy26. ከክፍለ ዘመናት ሰዎች ብዙዎችን ያጠፋን መሆናችን በመኖሪያዎቻቸው የሚሄዱ ሲሆኑ እነርሱ አልተገለጸላቸዉምን? በዚህ ውስጥ አያሌ ምልክቶች አሉበት:: አይሰሙምን?
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَوَلَمْ يَرَوْا۟ أَنَّا نَسُوقُ ٱلْمَآءَ إِلَى ٱلْأَرْضِ ٱلْجُرُزِ فَنُخْرِجُ بِهِۦ زَرْعًا تَأْكُلُ مِنْهُ أَنْعَٰمُهُمْ وَأَنفُسُهُمْ أَفَلَا يُبْصِرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy27. እኛ ውሃን ወደ ደረቅ ምድር የምንነዳ እንስሶቻቸውና ነፍሶቻቸው ከእርሱ የሚበሉለትንም አዝመራ በእርሱ የምናወጣ መሆናችንን አያዩምን? አይመለከቱምን?
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَيَقُولُونَ مَتَىٰ هَٰذَا ٱلْفَتْحُ إِن كُنتُمْ صَٰدِقِينَ
Amharic Translation - Africa Academy28. «ከእውነተኞችም እንደ ሆናችሁ ይህ ፍርድ መቼ ነው።» ይላሉ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قُلْ يَوْمَ ٱلْفَتْحِ لَا يَنفَعُ ٱلَّذِينَ كَفَرُوٓا۟ إِيمَٰنُهُمْ وَلَا هُمْ يُنظَرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy29. «በፍርዱ ቀን እነዚያን የካዱትን ሰዎች እምነታቸው አይጠቅማቸዉም:: እነርሱም ጊዜን አይሰጡም።» በላቸው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَأَعْرِضْ عَنْهُمْ وَٱنتَظِرْ إِنَّهُم مُّنتَظِرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy30. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነርሱን ተዋቸው:: ተጠባበቅም:: እነርሱም ተጠባባቂዎች ናቸውና::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
→