ሱረቱ Luqman لقمان
34 አንቀጾች · መካ · የወረደበት ቅደም ተከተል 57
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ الٓمٓ
Amharic Translation - Africa Academy1. አሊፍ፤ ላም፤ ሚይም፤
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
تِلْكَ ءَايَٰتُ ٱلْكِتَٰبِ ٱلْحَكِيمِ
Amharic Translation - Africa Academy2. እነዚህ አናቅጽ ጥበብ ከተሞላው መጽሐፍ ናቸው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
هُدًى وَرَحْمَةً لِّلْمُحْسِنِينَ
Amharic Translation - Africa Academy3. ለበጎ አድራጊዎች ሁሉ መሪ፣ እዝነት ሲሆን፤
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ٱلَّذِينَ يُقِيمُونَ ٱلصَّلَوٰةَ وَيُؤْتُونَ ٱلزَّكَوٰةَ وَهُم بِٱلْـَٔاخِرَةِ هُمْ يُوقِنُونَ
Amharic Translation - Africa Academy4. ለእነዚያ ሶላትን አስተካክለው ለሚሰግዱ፤ ዘካንም ለሚሰጡት፤ በመጨረሻይቱም ዓለም የሚያረጋግጡ ለሆኑት፤
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أُو۟لَٰٓئِكَ عَلَىٰ هُدًى مِّن رَّبِّهِمْ وَأُو۟لَٰٓئِكَ هُمُ ٱلْمُفْلِحُونَ
Amharic Translation - Africa Academy5. እነዚያ (የተጠቀሱትን ባህሪያት የሚላበሱ ሰዎች ሁሉ) በጌታቸው መመሪያ ላይ የሚጓዙ ናቸው። እነዚያ ፍላጎታቸውንም ያገኙትም እነርሱ ብቻ ናቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَمِنَ ٱلنَّاسِ مَن يَشْتَرِى لَهْوَ ٱلْحَدِيثِ لِيُضِلَّ عَن سَبِيلِ ٱللَّهِ بِغَيْرِ عِلْمٍ وَيَتَّخِذَهَا هُزُوًا أُو۟لَٰٓئِكَ لَهُمْ عَذَابٌ مُّهِينٌ
Amharic Translation - Africa Academy6. ከሰዎች መካከል ያለ ምንም እውቀት ሰዎችን ከአላህ መንገድ ሊያሳስትና የአላህን መንገድ ማላገጫ ሊያደርግ አታላይ ወሬን የሚገዛ አለ:: እነዚያ ይህን የሚያደርጉ ሁሉ ለእነርሱ አዋራጅ ቅጣት አለባቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَإِذَا تُتْلَىٰ عَلَيْهِ ءَايَٰتُنَا وَلَّىٰ مُسْتَكْبِرًا كَأَن لَّمْ يَسْمَعْهَا كَأَنَّ فِىٓ أُذُنَيْهِ وَقْرًا فَبَشِّرْهُ بِعَذَابٍ أَلِيمٍ
Amharic Translation - Africa Academy7. አናቅጻችን በእርሱ ላይ በሚነበቡ ጊዜ እንዳልሰማትና በጆሮቹ ድንቁርና እንዳለበት የኮራ ሆኖ ይዞራል:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ይህን ሰው በአሳማሚ ቅጣት አብስረው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِنَّ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ وَعَمِلُوا۟ ٱلصَّٰلِحَٰتِ لَهُمْ جَنَّٰتُ ٱلنَّعِيمِ
Amharic Translation - Africa Academy8. እነዚያ ያመኑና መልካሞችን ተግባራት የሰሩ ሁሉ ለእነርሱ የጸጋ ገነቶች አሏቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
خَٰلِدِينَ فِيهَا وَعْدَ ٱللَّهِ حَقًّا وَهُوَ ٱلْعَزِيزُ ٱلْحَكِيمُ
Amharic Translation - Africa Academy9. በእርሷ ውስጥ ዘውታሪዎች ሲሆኑ አላህ እውነተኛን የተስፋ ቃል ገባላቸው:: እርሱም ሁሉንም አሸናፊና ጥበበኛ ነውና::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
خَلَقَ ٱلسَّمَٰوَٰتِ بِغَيْرِ عَمَدٍ تَرَوْنَهَا وَأَلْقَىٰ فِى ٱلْأَرْضِ رَوَٰسِىَ أَن تَمِيدَ بِكُمْ وَبَثَّ فِيهَا مِن كُلِّ دَآبَّةٍ وَأَنزَلْنَا مِنَ ٱلسَّمَآءِ مَآءً فَأَنۢبَتْنَا فِيهَا مِن كُلِّ زَوْجٍ كَرِيمٍ
Amharic Translation - Africa Academy10. ሰማያትን የምታዮዋት ምሰሶ ሳያደርግላት ፈጠረ:: በምድርም ውስጥ በእናንተ እንዳታረገርግ ተራራዎችን ጣለ:: በእርሷም ላይ ከተንቀሳቃሽ ነገሮች ሁሉ በተነ:: ከሰማይም ውሃን አወረድን:: በእርሷ ውስጥ ከመልካም ዓይነት ሁሉ አበቀልን::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
هَٰذَا خَلْقُ ٱللَّهِ فَأَرُونِى مَاذَا خَلَقَ ٱلَّذِينَ مِن دُونِهِۦ بَلِ ٱلظَّٰلِمُونَ فِى ضَلَٰلٍ مُّبِينٍ
Amharic Translation - Africa Academy11. ይህ ሁሉ የአላህ ፍጡር ነው:: እነዚያ ከእርሱ ሌላ ያሉት ምንን እንደ ፈጠሩ እስኪ አሳዩኝ:: በዳዮች በእውነት በግልጽ ጥመት ውስጥ ናቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلَقَدْ ءَاتَيْنَا لُقْمَٰنَ ٱلْحِكْمَةَ أَنِ ٱشْكُرْ لِلَّهِ وَمَن يَشْكُرْ فَإِنَّمَا يَشْكُرُ لِنَفْسِهِۦ وَمَن كَفَرَ فَإِنَّ ٱللَّهَ غَنِىٌّ حَمِيدٌ
Amharic Translation - Africa Academy12. ለሉቅማንም ጥበብን በእርግጥ ሰጠነው:: አላህን አመስግን አልነዉም:: ያመሰገነም ሁሉ የሚያመሰግነው ለራሱ ብቻ ነው:: የካደም ሰውም (በራሱ ላይ ነው::) አላህ ተብቃቂና ምስጉን ነውና::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَإِذْ قَالَ لُقْمَٰنُ لِٱبْنِهِۦ وَهُوَ يَعِظُهُۥ يَٰبُنَىَّ لَا تُشْرِكْ بِٱللَّهِ إِنَّ ٱلشِّرْكَ لَظُلْمٌ عَظِيمٌ
Amharic Translation - Africa Academy13. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ሉቅማንም ለልጁ እርሱ የሚገስጸው ሲሆን «ልጄ ሆይ! በአላህ አታጋራ። ማጋራት ታላቅ በደል ነውና።» ያለውን አስታውስ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَوَصَّيْنَا ٱلْإِنسَٰنَ بِوَٰلِدَيْهِ حَمَلَتْهُ أُمُّهُۥ وَهْنًا عَلَىٰ وَهْنٍ وَفِصَٰلُهُۥ فِى عَامَيْنِ أَنِ ٱشْكُرْ لِى وَلِوَٰلِدَيْكَ إِلَىَّ ٱلْمَصِيرُ
Amharic Translation - Africa Academy14. ሰውንም በወላጆቹ በጎ እንዲያደርግ በጥብቅ አዘዝነው:: እናቱ ከድካም በላይ በሆነ ድካም አረገዘችው:: ጡት መጣያዉም በሁለት ዓመት ውስጥ ነው:: «ለእኔም ለወላጆችህም አመስግን" በማለትም አዘዝነው። መመለሻው ወደ እኔ ብቻ ነው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَإِن جَٰهَدَاكَ عَلَىٰٓ أَن تُشْرِكَ بِى مَا لَيْسَ لَكَ بِهِۦ عِلْمٌ فَلَا تُطِعْهُمَا وَصَاحِبْهُمَا فِى ٱلدُّنْيَا مَعْرُوفًا وَٱتَّبِعْ سَبِيلَ مَنْ أَنَابَ إِلَىَّ ثُمَّ إِلَىَّ مَرْجِعُكُمْ فَأُنَبِّئُكُم بِمَا كُنتُمْ تَعْمَلُونَ
Amharic Translation - Africa Academy15. ላንተ በእርሱ እውቀት የሌለህን ነገር በእኔ እንድታጋራ ቢያስገድዱህ አትታዘዛቸው:: በቅርቢቱም ዓለም በመልካም ስራ ተወዳጃቸው:: ወደ እኔም የተመለሰን ሰው መንገድ ተከተል:: ከዚያ መመለሻችሁ ወደ እኔ ነው:: ትሰሩት የነበራችሁትንም ሁሉ እነግራችኋለሁ (አልነው)።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
يَٰبُنَىَّ إِنَّهَآ إِن تَكُ مِثْقَالَ حَبَّةٍ مِّنْ خَرْدَلٍ فَتَكُن فِى صَخْرَةٍ أَوْ فِى ٱلسَّمَٰوَٰتِ أَوْ فِى ٱلْأَرْضِ يَأْتِ بِهَا ٱللَّهُ إِنَّ ٱللَّهَ لَطِيفٌ خَبِيرٌ
Amharic Translation - Africa Academy16. (ሉቅማንም አለ:) «ልጄ ሆይ! የእርሷ (መጥፎም ይሁን በጎ) የሰናፍጭ ቅንጣት ክብደት ያህል እንኳን ብትሆንና በቋጥኝ ውስጥ ወይም በሰማያት ውስጥ ወይም በምድር ውስጥ ብትሆን አላህ ያመጣታል:: አላህ ሩህሩህና ውስጠ አዋቂ ነውና።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
يَٰبُنَىَّ أَقِمِ ٱلصَّلَوٰةَ وَأْمُرْ بِٱلْمَعْرُوفِ وَٱنْهَ عَنِ ٱلْمُنكَرِ وَٱصْبِرْ عَلَىٰ مَآ أَصَابَكَ إِنَّ ذَٰلِكَ مِنْ عَزْمِ ٱلْأُمُورِ
Amharic Translation - Africa Academy17. «ልጄ ሆይ! ሶላትን አስተካክለህ ስገድ፤ በበጎ ነገርም እዘዝ ከሚጠላም ሁሉ ከልክል፤ በሚያገኝህም መከራ ላይ ታገስ ይህ በምር ከሚያዙ ወሳኝ ነገሮች ነው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلَا تُصَعِّرْ خَدَّكَ لِلنَّاسِ وَلَا تَمْشِ فِى ٱلْأَرْضِ مَرَحًا إِنَّ ٱللَّهَ لَا يُحِبُّ كُلَّ مُخْتَالٍ فَخُورٍ
Amharic Translation - Africa Academy18. «ጉንጭህንም በኩራት ከሰዎች አታዙር:: በምድርም ላይ ተንበጥርረህ አትሂድ:: አላህ ተንበጥራሪን (ኮራተኛ) ጉረኛን ሁሉ አይወድምና::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَٱقْصِدْ فِى مَشْيِكَ وَٱغْضُضْ مِن صَوْتِكَ إِنَّ أَنكَرَ ٱلْأَصْوَٰتِ لَصَوْتُ ٱلْحَمِيرِ
Amharic Translation - Africa Academy19. «በአካሄድህም መካከለኛ ሁን:: ከድምጽህም ዝቅ አድርግ:: ከድምፆች ሁሉ አስከፊው የአህዮች ድምጽ ነውና።»
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَلَمْ تَرَوْا۟ أَنَّ ٱللَّهَ سَخَّرَ لَكُم مَّا فِى ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَمَا فِى ٱلْأَرْضِ وَأَسْبَغَ عَلَيْكُمْ نِعَمَهُۥ ظَٰهِرَةً وَبَاطِنَةً وَمِنَ ٱلنَّاسِ مَن يُجَٰدِلُ فِى ٱللَّهِ بِغَيْرِ عِلْمٍ وَلَا هُدًى وَلَا كِتَٰبٍ مُّنِيرٍ
Amharic Translation - Africa Academy20. (ሰዎች ሆይ!) አላህ በሰማያት እና በምድር ውስጥ ያለውን ነገር ሁሉ ለእናንተ ያገራላችሁ፤ ጸጋዎችንም ግልጽም ይሁኑ ድብቅ የሞላላችሁ መሆኑን አታዩምን? ከስሞች መካከል ያለ በቂ እውቀትና ያለ መሪ፤ ያለ ግልጽ መጽሀፍም፤ ስለ አላህ የሚከራከር አለ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَإِذَا قِيلَ لَهُمُ ٱتَّبِعُوا۟ مَآ أَنزَلَ ٱللَّهُ قَالُوا۟ بَلْ نَتَّبِعُ مَا وَجَدْنَا عَلَيْهِ ءَابَآءَنَآ أَوَلَوْ كَانَ ٱلشَّيْطَٰنُ يَدْعُوهُمْ إِلَىٰ عَذَابِ ٱلسَّعِيرِ
Amharic Translation - Africa Academy21. ለእነርሱም «አላህ ያወረደውን ተከተሉ።» በተባሉ ጊዜ «አይደለም በእርሱ ላይ አባቶቻችንን ያገኘንበትን እንከተላለን።» ይላሉ:: ሰይጣን (ይህን ተግባር በማስዋብ) ወደ እሳት ቅጣት የሚጠራቸው ቢሆንም ይከተሏቸዋልን?
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَمَن يُسْلِمْ وَجْهَهُۥٓ إِلَى ٱللَّهِ وَهُوَ مُحْسِنٌ فَقَدِ ٱسْتَمْسَكَ بِٱلْعُرْوَةِ ٱلْوُثْقَىٰ وَإِلَى ٱللَّهِ عَٰقِبَةُ ٱلْأُمُورِ
Amharic Translation - Africa Academy22. መልካም ሰሪ ሆኖ ፊቱን ወደ አላህ የሚሰጥ ሁሉ ጠንካራ ገመድን በእርግጥ ጨበጠ:: የነገሩ ሁሉ ፍጻሜ ወደ አላህ ብቻ ነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَمَن كَفَرَ فَلَا يَحْزُنكَ كُفْرُهُۥٓ إِلَيْنَا مَرْجِعُهُمْ فَنُنَبِّئُهُم بِمَا عَمِلُوٓا۟ إِنَّ ٱللَّهَ عَلِيمٌۢ بِذَاتِ ٱلصُّدُورِ
Amharic Translation - Africa Academy23. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በአላህ የካደም ሁሉ ክህደቱ አያሳዝንህ። መመለሻቸው ወደ እኛ ብቻ ነውና:: ከዚያም የሰሩትንም ሁሉ እንነግራቸዋለን:: አላህ በልቦች ውስጥ ያለን ሁሉ ያውቃልና፡፡
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
نُمَتِّعُهُمْ قَلِيلًا ثُمَّ نَضْطَرُّهُمْ إِلَىٰ عَذَابٍ غَلِيظٍ
Amharic Translation - Africa Academy24. ጥቂትን ጊዜ እናጣቅማቸዋለን:: ከዚያም ወደ ብርቱ ቅጣት እናስገድዳቸዋለን::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلَئِن سَأَلْتَهُم مَّنْ خَلَقَ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضَ لَيَقُولُنَّ ٱللَّهُ قُلِ ٱلْحَمْدُ لِلَّهِ بَلْ أَكْثَرُهُمْ لَا يَعْلَمُونَ
Amharic Translation - Africa Academy25. ሰማያትንና ምድርን የፈጠረ ማን እንደሆነ ብትጠይቃቸው «በእርግጥ አላህ ነው።» ይላሉ። «ምስጋና ሁሉ ለአላህ ብቻ ይገባው።» በላቸው:: ይልቁንም አብዛኞቹ አያውቁም።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
لِلَّهِ مَا فِى ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِ إِنَّ ٱللَّهَ هُوَ ٱلْغَنِىُّ ٱلْحَمِيدُ
Amharic Translation - Africa Academy26. በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ የአላህ ብቻ ነው:: አላህ በራሱ ተብቃቂዉና ምስጉኑ ነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلَوْ أَنَّمَا فِى ٱلْأَرْضِ مِن شَجَرَةٍ أَقْلَٰمٌ وَٱلْبَحْرُ يَمُدُّهُۥ مِنۢ بَعْدِهِۦ سَبْعَةُ أَبْحُرٍ مَّا نَفِدَتْ كَلِمَٰتُ ٱللَّهِ إِنَّ ٱللَّهَ عَزِيزٌ حَكِيمٌ
Amharic Translation - Africa Academy27. በምድር ያሉ ሁሉ ዛፎች ብዕሮች ቢሆኑ ኖሮ ባህሩም ከእርሱ ማለቅ በኋላ ሰባት ባህሮች የሚጨመሩለት ሆኖ ቀለም ቢሆንና ቢጻፍባቸው የአላህ ቃላት ባላለቀች ነበር:: አላህ ሁሉን አሸናፊና ጥበበኛ ነውና::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
مَّا خَلْقُكُمْ وَلَا بَعْثُكُمْ إِلَّا كَنَفْسٍ وَٰحِدَةٍ إِنَّ ٱللَّهَ سَمِيعٌۢ بَصِيرٌ
Amharic Translation - Africa Academy28. (ሰዎች ሆይ!) እናንተን መፍጠርና እናንተን መቀስቀስ እንደ አንዲት ነፍስ እንጂ ሌላ አይደለም:: አላህ ሁሉን ሰሚና ሁሉን ተመልካች ነውና::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَلَمْ تَرَ أَنَّ ٱللَّهَ يُولِجُ ٱلَّيْلَ فِى ٱلنَّهَارِ وَيُولِجُ ٱلنَّهَارَ فِى ٱلَّيْلِ وَسَخَّرَ ٱلشَّمْسَ وَٱلْقَمَرَ كُلٌّ يَجْرِىٓ إِلَىٰٓ أَجَلٍ مُّسَمًّى وَأَنَّ ٱللَّهَ بِمَا تَعْمَلُونَ خَبِيرٌ
Amharic Translation - Africa Academy29. (የሰው ልጅ ሆይ) አላህ ሌሊትን በቀን ውስጥ የሚያስገባ ቀንንም በሌሊት ውስጥ የሚያስገባ ጸሀይንና ጨረቃንም የገራ መሆኑን አታይምን? ሁሉም እስከ ተወሰነ ጊዜ ድረስ ይሮጣሉ:: አላህም በምትሰሩት ሁሉ ውስጠ አዋቂ ነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ذَٰلِكَ بِأَنَّ ٱللَّهَ هُوَ ٱلْحَقُّ وَأَنَّ مَا يَدْعُونَ مِن دُونِهِ ٱلْبَٰطِلُ وَأَنَّ ٱللَّهَ هُوَ ٱلْعَلِىُّ ٱلْكَبِيرُ
Amharic Translation - Africa Academy30. ይህም የእርሱ (የአላህ) ብቸኛ አምላክነት እውነት በመሆኑ፤ ከእርሱ ሌላ የሚገዙት ጣዖት ሁሉ ውሸት በመሆኑና አላህ የበላይ ታላቅ በመሆኑ ነው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَلَمْ تَرَ أَنَّ ٱلْفُلْكَ تَجْرِى فِى ٱلْبَحْرِ بِنِعْمَتِ ٱللَّهِ لِيُرِيَكُم مِّنْ ءَايَٰتِهِۦٓ إِنَّ فِى ذَٰلِكَ لَـَٔايَٰتٍ لِّكُلِّ صَبَّارٍ شَكُورٍ
Amharic Translation - Africa Academy31. (የሰው ልጅ ሆይ!) ከአስደናቂ ምልክቶቹ ሊያሳያችሁ መርከቦች በአላህ ችሮታ በባህር ውስጥ የሚንሻለሉ መሆናቸውን አታይምን? በዚህ ውስጥ በጣም ታጋሽ አመስጋኝ ለሆኑ ሁሉ አያሌ ተዓምራት አሉበት::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَإِذَا غَشِيَهُم مَّوْجٌ كَٱلظُّلَلِ دَعَوُا۟ ٱللَّهَ مُخْلِصِينَ لَهُ ٱلدِّينَ فَلَمَّا نَجَّىٰهُمْ إِلَى ٱلْبَرِّ فَمِنْهُم مُّقْتَصِدٌ وَمَا يَجْحَدُ بِـَٔايَٰتِنَآ إِلَّا كُلُّ خَتَّارٍ كَفُورٍ
Amharic Translation - Africa Academy32. እንደ ጥላዎች የሆነ ማዕበል በሸፈናቸው ጊዜ ሃይማኖትን ለእርሱ ብቻ ያጠሩ ሆነው አላህን ይጠሩታል:: ወደ የብስ ባዳናቸው ጊዜ ግን ከእነርሱ መካከል ትክክለኛም አለ:: (ከእነርሱም መካከል የሚክድ አለ):: በአናቅጻችንም አታላይና ከዳተኛ የሆነ ሁሉ እንጂ ሌላው አይክድም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
يَٰٓأَيُّهَا ٱلنَّاسُ ٱتَّقُوا۟ رَبَّكُمْ وَٱخْشَوْا۟ يَوْمًا لَّا يَجْزِى وَالِدٌ عَن وَلَدِهِۦ وَلَا مَوْلُودٌ هُوَ جَازٍ عَن وَالِدِهِۦ شَيْـًٔا إِنَّ وَعْدَ ٱللَّهِ حَقٌّ فَلَا تَغُرَّنَّكُمُ ٱلْحَيَوٰةُ ٱلدُّنْيَا وَلَا يَغُرَّنَّكُم بِٱللَّهِ ٱلْغَرُورُ
Amharic Translation - Africa Academy33. እናንተ ሰዎች ሆይ! ጌታችሁን ፍሩ:: ወላጅ ከልጁ በምንም የማይጠቅምበት ልጅም ወላጅን በምንም ጠቃሚ የማይሆንበትን ቀን ፍሩ:: የአላህ ቀጠሮ እውነት ነውና:: ቅርቢቱም ህይወት አትሸንግላችሁ:: በአላህ (መታገስም) አታላዩ (ሰይጣን) አያታልላችሁ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِنَّ ٱللَّهَ عِندَهُۥ عِلْمُ ٱلسَّاعَةِ وَيُنَزِّلُ ٱلْغَيْثَ وَيَعْلَمُ مَا فِى ٱلْأَرْحَامِ وَمَا تَدْرِى نَفْسٌ مَّاذَا تَكْسِبُ غَدًا وَمَا تَدْرِى نَفْسٌۢ بِأَىِّ أَرْضٍ تَمُوتُ إِنَّ ٱللَّهَ عَلِيمٌ خَبِيرٌۢ
Amharic Translation - Africa Academy34. አላህ የሰዓቲቱ እውቀት እርሱ ዘንድ ብቻ ነው:: ዝናብንም ያወርዳል:: በማህጸኖችም ውስጥ ያለን ሁሉ ያውቃል። ማንኛይቱም ነፍስ ነገ የምትሰራውን አታውቅም:: ማንኛይቱም ነፍስ በየትኛው ምድር እንደምትሞትም አታውቅም:: አላህ አዋቂና ውስጠ አዋቂ ነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
→