caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Al-Ahzaab الأحزاب

73 አንቀጾች · መዲና · የወረደበት ቅደም ተከተል 90

بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ يَٰٓأَيُّهَا ٱلنَّبِىُّ ٱتَّقِ ٱللَّهَ وَلَا تُطِعِ ٱلْكَٰفِرِينَ وَٱلْمُنَٰفِقِينَ إِنَّ ٱللَّهَ كَانَ عَلِيمًا حَكِيمًا

Amharic Translation - Africa Academy1. አንተ ነብይ ሆይ! አላህን ፍራ:: ከሓዲያንንና አስመሳዮችንም አትታዘዝ:: አላህ ሁሉን አዋቂና ጥበበኛ ነውና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَٱتَّبِعْ مَا يُوحَىٰٓ إِلَيْكَ مِن رَّبِّكَ إِنَّ ٱللَّهَ كَانَ بِمَا تَعْمَلُونَ خَبِيرًا

Amharic Translation - Africa Academy2. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከጌታህም ወደ አንተ የሚወረደውን ብቻ ተከተል:: አላህ በምትሰሩት ሁሉ ውስጠ አዋቂ ነውና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَتَوَكَّلْ عَلَى ٱللَّهِ وَكَفَىٰ بِٱللَّهِ وَكِيلًا

Amharic Translation - Africa Academy3. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በአላህ ላይ ተመካ:: መመኪያነትም በአላህ ብቻ በቃ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

مَّا جَعَلَ ٱللَّهُ لِرَجُلٍ مِّن قَلْبَيْنِ فِى جَوْفِهِۦ وَمَا جَعَلَ أَزْوَٰجَكُمُ ٱلَّٰٓـِٔى تُظَٰهِرُونَ مِنْهُنَّ أُمَّهَٰتِكُمْ وَمَا جَعَلَ أَدْعِيَآءَكُمْ أَبْنَآءَكُمْ ذَٰلِكُمْ قَوْلُكُم بِأَفْوَٰهِكُمْ وَٱللَّهُ يَقُولُ ٱلْحَقَّ وَهُوَ يَهْدِى ٱلسَّبِيلَ

Amharic Translation - Africa Academy4. (ሙስሊሞች ሆይ!) አላህ ለአንድ ሰው በሆዱ ውስጥ ሁለትን ልቦች አላደረገም:: እነዚያን «እንደናቶቻችን ጀርባዎች ይሁኑብን» የምትሏቸውን ሚስቶቻችሁንም እናቶቻችሁ አላደረገም:: ልጅ በማድረግ የምታስጠጓቸውንም ልጆቻችሁ አላደረገም:: ይህ በአፎቻችሁ የምትሉት ቃላችሁ ብቻ ነው:: አላህ እውነትን ይናገራል:: ትክክለኛውን መንገድም ይመራል::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ٱدْعُوهُمْ لِـَٔابَآئِهِمْ هُوَ أَقْسَطُ عِندَ ٱللَّهِ فَإِن لَّمْ تَعْلَمُوٓا۟ ءَابَآءَهُمْ فَإِخْوَٰنُكُمْ فِى ٱلدِّينِ وَمَوَٰلِيكُمْ وَلَيْسَ عَلَيْكُمْ جُنَاحٌ فِيمَآ أَخْطَأْتُم بِهِۦ وَلَٰكِن مَّا تَعَمَّدَتْ قُلُوبُكُمْ وَكَانَ ٱللَّهُ غَفُورًا رَّحِيمًا

Amharic Translation - Africa Academy5. (ሙስሊሞች ሆይ!) (ልጅ በማድረግ የምታስጠጓቸውን) በአባቶቻቸው ስም በማስጠጋት ጥሯቸው:: እርሱ አላህ ዘንድ ትክክለኛው መንገድ ነውና:: አባቶቻቸውን ባታውቁም በሃይማኖት ወንድሞቻችሁና ዘመዶቻችሁ ናቸው:: በተሳሳታችሁበት ነገርም በእናንተ ላይ ምንም ኃጢአት የለባችሁም:: ልቦቻችሁ አውቀው በሰራችሁት ስህተት ግን ኃጢአት አለባችሁ:: አላህ መሀሪና አዛኝ ነውና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ٱلنَّبِىُّ أَوْلَىٰ بِٱلْمُؤْمِنِينَ مِنْ أَنفُسِهِمْ وَأَزْوَٰجُهُۥٓ أُمَّهَٰتُهُمْ وَأُو۟لُوا۟ ٱلْأَرْحَامِ بَعْضُهُمْ أَوْلَىٰ بِبَعْضٍ فِى كِتَٰبِ ٱللَّهِ مِنَ ٱلْمُؤْمِنِينَ وَٱلْمُهَٰجِرِينَ إِلَّآ أَن تَفْعَلُوٓا۟ إِلَىٰٓ أَوْلِيَآئِكُم مَّعْرُوفًا كَانَ ذَٰلِكَ فِى ٱلْكِتَٰبِ مَسْطُورًا

Amharic Translation - Africa Academy6. ነብዩ (ሙሐመድ) ለአማኞች ከነፍሶቻቸው ይበልጥ ቀራቢ ነው:: ሚስቶቹም እናቶቻቸው ናቸው:: የዝምድና ባለቤቶችም ከፊላቸው በከፊሉ ላይ (ለውርስ) በአላህ መጽሐፍ ውስጥ ከአማኞችና ከስደተኞች ይልቅ የተገባቸው ናቸው:: ለወዳጆቻችሁ በኑዛዜ መልካም ስራን ብትሰሩ ግን ይፈቀዳል:: ይህ በአላህ መጽሐፉ ውስጥ ቀድሞውኑ የተመዘገበ ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَإِذْ أَخَذْنَا مِنَ ٱلنَّبِيِّـۧنَ مِيثَٰقَهُمْ وَمِنكَ وَمِن نُّوحٍ وَإِبْرَٰهِيمَ وَمُوسَىٰ وَعِيسَى ٱبْنِ مَرْيَمَ وَأَخَذْنَا مِنْهُم مِّيثَٰقًا غَلِيظًا

Amharic Translation - Africa Academy7. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከነብዮችም ካንተም፤ ከኑህም፤ ከኢብራሂምም፤ ከሙሳም፤ ከመርየም ልጅ ዒሳም የጠበቀ ቃልኪዳናቸውን በያዝን ጊዜ (የሆነውን አስታውስ):: ከእነርሱም የከበደን ቃል ኪዳን ያዝን::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

لِّيَسْـَٔلَ ٱلصَّٰدِقِينَ عَن صِدْقِهِمْ وَأَعَدَّ لِلْكَٰفِرِينَ عَذَابًا أَلِيمًا

Amharic Translation - Africa Academy8. አላህ እውነተኞችን ከእውነታቸው ሊጠይቃቸው (ይህንን ሰራ):: ለከሓዲያንም አሳማሚን ቅጣት አዘጋጀ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ ٱذْكُرُوا۟ نِعْمَةَ ٱللَّهِ عَلَيْكُمْ إِذْ جَآءَتْكُمْ جُنُودٌ فَأَرْسَلْنَا عَلَيْهِمْ رِيحًا وَجُنُودًا لَّمْ تَرَوْهَا وَكَانَ ٱللَّهُ بِمَا تَعْمَلُونَ بَصِيرًا

Amharic Translation - Africa Academy9. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ብዙ ሰራዊት በመጣባችሁና በእነርሱ ላይ ንፋስንና በአይናችሁ ያላያችሁትን ሰራዊት በላክን ጊዜ ያደረገላችሁን ጸጋ አስታውሱ:: አላህም የምትሰሩትን ተመልካች ነው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِذْ جَآءُوكُم مِّن فَوْقِكُمْ وَمِنْ أَسْفَلَ مِنكُمْ وَإِذْ زَاغَتِ ٱلْأَبْصَٰرُ وَبَلَغَتِ ٱلْقُلُوبُ ٱلْحَنَاجِرَ وَتَظُنُّونَ بِٱللَّهِ ٱلظُّنُونَا۠

Amharic Translation - Africa Academy10. ከበላያችሁም ከናንተ በታችም በመጡባችሁ፤ ዓይኖችም በቃበዙ፤ ልቦችም ወደ ላንቃዎች በደረሱና በአላህም መጥፎ ጥርጣሬዎችን በጠረጠራችሁ ጊዜ ያደረገላችሁን ጸጋ (አስታውሱ)::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

هُنَالِكَ ٱبْتُلِىَ ٱلْمُؤْمِنُونَ وَزُلْزِلُوا۟ زِلْزَالًا شَدِيدًا

Amharic Translation - Africa Academy11. እዚያ ዘንድ አማኞች ተሞከሩ:: ብርቱን መንቀጥቀጥም ተንቀጠቀጡ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَإِذْ يَقُولُ ٱلْمُنَٰفِقُونَ وَٱلَّذِينَ فِى قُلُوبِهِم مَّرَضٌ مَّا وَعَدَنَا ٱللَّهُ وَرَسُولُهُۥٓ إِلَّا غُرُورًا

Amharic Translation - Africa Academy12. መናፍቆችና እነዚያ በልቦቻቸው ውስጥ በሽታ ያለባቸው ሰዎች ሁሉ «አላህና መልዕክተኛው ማታለልን እንጂ ሌላን አልቀጠሩንም።» በሚሉም ጊዜ ያደረገላችሁን ውለታ አስታውሱ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَإِذْ قَالَت طَّآئِفَةٌ مِّنْهُمْ يَٰٓأَهْلَ يَثْرِبَ لَا مُقَامَ لَكُمْ فَٱرْجِعُوا۟ وَيَسْتَـْٔذِنُ فَرِيقٌ مِّنْهُمُ ٱلنَّبِىَّ يَقُولُونَ إِنَّ بُيُوتَنَا عَوْرَةٌ وَمَا هِىَ بِعَوْرَةٍ إِن يُرِيدُونَ إِلَّا فِرَارًا

Amharic Translation - Africa Academy13. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከእነርሱም የሆነ ቡድን «የየስሪብ ሰዎች ሆይ! ለእናንተ ስፍራ የላችሁምና ተመለሱ።» ባሉ ጊዜ (የሆነውን አስታውሱ):: ከእነርሱም መካከል ከፊሎቹ ነውረኛ ሳይሆኑ «ቤቶቻችን ነውረኛ ናቸው።» በማለት ነብዩን ከጦሩ ለመመለስ ፈቃድን ይጠይቃሉ:: መሸሽን እንጂ ሌላን አይፈልጉም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلَوْ دُخِلَتْ عَلَيْهِم مِّنْ أَقْطَارِهَا ثُمَّ سُئِلُوا۟ ٱلْفِتْنَةَ لَـَٔاتَوْهَا وَمَا تَلَبَّثُوا۟ بِهَآ إِلَّا يَسِيرًا

Amharic Translation - Africa Academy14. በእርሱም ላይ በቤቶቻቸው ከየቀበሌዋ ከጠላት በተገባባትና ከዚያም ከኢስላም መመለስን በተጠየቁ ኖሮ በፍጥነት በሰሯት ነበር ፡፡ በእሷ ጥቂትን ጊዜ እንጂ አይቆዩም ነበር ፡፡

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلَقَدْ كَانُوا۟ عَٰهَدُوا۟ ٱللَّهَ مِن قَبْلُ لَا يُوَلُّونَ ٱلْأَدْبَٰرَ وَكَانَ عَهْدُ ٱللَّهِ مَسْـُٔولًا

Amharic Translation - Africa Academy15. ጀርባዎችንም ላያዞሩ ከዚያም በፊት በእርግጥ አላህን ቃል ኪዳን የገቡ ነበሩ:: የአላህም ቃል ኪዳን የሚጠየቁበት ትልቅ ሀላፊነት ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قُل لَّن يَنفَعَكُمُ ٱلْفِرَارُ إِن فَرَرْتُم مِّنَ ٱلْمَوْتِ أَوِ ٱلْقَتْلِ وَإِذًا لَّا تُمَتَّعُونَ إِلَّا قَلِيلًا

Amharic Translation - Africa Academy16. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ከሞት ወይም ከመገደል ብትሸሹ መሸሻችሁ ፈጽሞ አይጠቅማችሁም:: ያን ጊዜም ጥቂትን እንጂ የምትጣቀሙ አትደረጉም።» በላቸው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قُلْ مَن ذَا ٱلَّذِى يَعْصِمُكُم مِّنَ ٱللَّهِ إِنْ أَرَادَ بِكُمْ سُوٓءًا أَوْ أَرَادَ بِكُمْ رَحْمَةً وَلَا يَجِدُونَ لَهُم مِّن دُونِ ٱللَّهِ وَلِيًّا وَلَا نَصِيرًا

Amharic Translation - Africa Academy17. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) (ሙስሊምቸ ሆይ!) «አላህ በእናንተ ላይ ክፉን ነገር ቢሻ ያ ከአላህ የሚጠብቃችሁ ማን ነው? ወይም ለእናንተ እዝነትን ቢፈልግ ክፉ የሚያመጣባችሁ ማን ነው?» በላቸው። ከአላህም ሌላ ለእነርሱ ወዳጅም ሆነ ረዳት አያገኙም።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَدْ يَعْلَمُ ٱللَّهُ ٱلْمُعَوِّقِينَ مِنكُمْ وَٱلْقَآئِلِينَ لِإِخْوَٰنِهِمْ هَلُمَّ إِلَيْنَا وَلَا يَأْتُونَ ٱلْبَأْسَ إِلَّا قَلِيلًا

Amharic Translation - Africa Academy18. ከናንተ ውስጥ የሚያደናቅፉትን ለወንድሞቻቸዉም «ወደ እኛ ኑ» የሚሉትን፤ ውጊያንም ጥቂትን እንጂ የማይመጡትን በእርግጥ አላህ ያውቃቸዋል::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَشِحَّةً عَلَيْكُمْ فَإِذَا جَآءَ ٱلْخَوْفُ رَأَيْتَهُمْ يَنظُرُونَ إِلَيْكَ تَدُورُ أَعْيُنُهُمْ كَٱلَّذِى يُغْشَىٰ عَلَيْهِ مِنَ ٱلْمَوْتِ فَإِذَا ذَهَبَ ٱلْخَوْفُ سَلَقُوكُم بِأَلْسِنَةٍ حِدَادٍ أَشِحَّةً عَلَى ٱلْخَيْرِ أُو۟لَٰٓئِكَ لَمْ يُؤْمِنُوا۟ فَأَحْبَطَ ٱللَّهُ أَعْمَٰلَهُمْ وَكَانَ ذَٰلِكَ عَلَى ٱللَّهِ يَسِيرًا

Amharic Translation - Africa Academy19. (አማኞች ሆይ!) በእናንተ ላይ እርዳታን የነፈጉ ሆነው እንጂ የማይመጡትን፤ ሽብሩም በመጣ ጊዜ እንደዚያ ከሞት መከራ በእርሱ ላይ የሚሸፍን አደጋ እንደ ወደቀበት ዓይኖቻቸው ወዲያና ወዲህ የምትንከራተት ሆና ወደ አንተ ሲመለከቱ ታያቸዋለህ:: ሽብሩም በሄደ ጊዜ በገንዘብ ላይ የሚሳሱ ሆነው በተቡ ምላሶች ይነድፏችኋል:: እነዚያ አላመኑም:: ስለዚህ አላህ ስራዎቻቸውን አበላሸ:: ይህም በአላህ ላይ ገር ነው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

يَحْسَبُونَ ٱلْأَحْزَابَ لَمْ يَذْهَبُوا۟ وَإِن يَأْتِ ٱلْأَحْزَابُ يَوَدُّوا۟ لَوْ أَنَّهُم بَادُونَ فِى ٱلْأَعْرَابِ يَسْـَٔلُونَ عَنْ أَنۢبَآئِكُمْ وَلَوْ كَانُوا۟ فِيكُم مَّا قَٰتَلُوٓا۟ إِلَّا قَلِيلًا

Amharic Translation - Africa Academy20. (መናፍቆች) አህዛብን አልሄዱም ብለው ያስባሉ አህዛቦችም ቢመጡ እነርሱ በዘላኖች ውስጥ በገጠር የራቁ ሊሆኑ ይመኛሉ:: (ከዚያም) ከወሬዎቻችሁ ይጠይቃሉ:: በእናንተ ውስጥ በነበሩም ኖሮ ጥቂትን እንጂ አይዋጉም ነበር::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

لَّقَدْ كَانَ لَكُمْ فِى رَسُولِ ٱللَّهِ أُسْوَةٌ حَسَنَةٌ لِّمَن كَانَ يَرْجُوا۟ ٱللَّهَ وَٱلْيَوْمَ ٱلْـَٔاخِرَ وَذَكَرَ ٱللَّهَ كَثِيرًا

Amharic Translation - Africa Academy21. (አማኞች ሆይ!) ከናንተ መካከል አላህንና የመጨረሻውን ቀን የሚከጅል ለሆነና አላህንም በብዙ ለሚያወሳ ሰው ሁሉ በአላህ መልዕክተኛ መልካም መከተል አላችሁ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلَمَّا رَءَا ٱلْمُؤْمِنُونَ ٱلْأَحْزَابَ قَالُوا۟ هَٰذَا مَا وَعَدَنَا ٱللَّهُ وَرَسُولُهُۥ وَصَدَقَ ٱللَّهُ وَرَسُولُهُۥ وَمَا زَادَهُمْ إِلَّآ إِيمَٰنًا وَتَسْلِيمًا

Amharic Translation - Africa Academy22. አማኞችም አህዛብን ባዩ ጊዜ «ይህ አላህና መልዕክተኛው የቀጠሩን ነው:: አላህና መልዕክተኛዉም እውነትን ተናገሩ።» አሉ:: ይህ እምነትንና መታዘዝንም እንጂ ሌላን አልጨመረላቸዉም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

مِّنَ ٱلْمُؤْمِنِينَ رِجَالٌ صَدَقُوا۟ مَا عَٰهَدُوا۟ ٱللَّهَ عَلَيْهِ فَمِنْهُم مَّن قَضَىٰ نَحْبَهُۥ وَمِنْهُم مَّن يَنتَظِرُ وَمَا بَدَّلُوا۟ تَبْدِيلًا

Amharic Translation - Africa Academy23. ከአማኞች መካከል በእርሱ ላይ ለአላህ ቃል ኪዳን የገቡበትን በእውነት የፈጸሙ ወንዶች አሉ። ከእነርሱም ስለቱን የፈጸመ ለሃይማኖቱ የተገደለም አለ:: ከእነርሱም መካከል ገና የሚጠባበቅ አለ:: የገቡትን ቃል መለወጥንም አለወጡም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

لِّيَجْزِىَ ٱللَّهُ ٱلصَّٰدِقِينَ بِصِدْقِهِمْ وَيُعَذِّبَ ٱلْمُنَٰفِقِينَ إِن شَآءَ أَوْ يَتُوبَ عَلَيْهِمْ إِنَّ ٱللَّهَ كَانَ غَفُورًا رَّحِيمًا

Amharic Translation - Africa Academy24. አላህ እውነተኞችን በእውነተኛነታቸው ሊመነዳ፤ አስመሳዮችንም ቢፈልግ ሊቀጣ ወይም ቢመለሱ በእነርሱ ላይ ጸጸታቸቸውን ሊቀበል ይህን አደረገ:: አላህ መሃሪና አዛኝ ነውና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَرَدَّ ٱللَّهُ ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ بِغَيْظِهِمْ لَمْ يَنَالُوا۟ خَيْرًا وَكَفَى ٱللَّهُ ٱلْمُؤْمِنِينَ ٱلْقِتَالَ وَكَانَ ٱللَّهُ قَوِيًّا عَزِيزًا

Amharic Translation - Africa Academy25. እነዚያንም በአላህ የካዱትን በቁጭታቸው የተሞሉ መልካምን ነገር ያላገኙ ሆነው አላህ መለሳቸው:: አማኞቹንም አላህ መጋደልን በቃቸው:: አላህም ብርቱና ሁሉን አሸናፊ ነውና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَأَنزَلَ ٱلَّذِينَ ظَٰهَرُوهُم مِّنْ أَهْلِ ٱلْكِتَٰبِ مِن صَيَاصِيهِمْ وَقَذَفَ فِى قُلُوبِهِمُ ٱلرُّعْبَ فَرِيقًا تَقْتُلُونَ وَتَأْسِرُونَ فَرِيقًا

Amharic Translation - Africa Academy26. እነዚያንም ከመጽሐፉ ባለቤቶች አህዛቦችን የረዷቸውን (ቁረይዟን) ከምሽጎቻቸው አወረዳቸው:: በልቦቻቸዉም ውስጥ መባባትን ጣለባቸው። ከፊሉን ትገድላላችሁ፤ ከፊሉንም ትማርካላችሁ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَأَوْرَثَكُمْ أَرْضَهُمْ وَدِيَٰرَهُمْ وَأَمْوَٰلَهُمْ وَأَرْضًا لَّمْ تَطَـُٔوهَا وَكَانَ ٱللَّهُ عَلَىٰ كُلِّ شَىْءٍ قَدِيرًا

Amharic Translation - Africa Academy27. ምድራቸውንም ቤቶቻቸውንም ገንዘቦቻቸውንም ገና ያልረገጣችኋትንም ምድር አወረሳችሁ:: አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነውና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

يَٰٓأَيُّهَا ٱلنَّبِىُّ قُل لِّأَزْوَٰجِكَ إِن كُنتُنَّ تُرِدْنَ ٱلْحَيَوٰةَ ٱلدُّنْيَا وَزِينَتَهَا فَتَعَالَيْنَ أُمَتِّعْكُنَّ وَأُسَرِّحْكُنَّ سَرَاحًا جَمِيلًا

Amharic Translation - Africa Academy28. አንተ ነብይ ሆይ! ለሚስቶችህ (እንዲህ) በላቸው: «ቅርቢቱን ህይወትና ጌጧን የምትፈልጉ እንደ ሆናችሁ ኑ:: አጣቅማችኋለሁና መልካምንም መፍታት እፈታችኋለሁና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَإِن كُنتُنَّ تُرِدْنَ ٱللَّهَ وَرَسُولَهُۥ وَٱلدَّارَ ٱلْـَٔاخِرَةَ فَإِنَّ ٱللَّهَ أَعَدَّ لِلْمُحْسِنَٰتِ مِنكُنَّ أَجْرًا عَظِيمًا

Amharic Translation - Africa Academy29. «አላህንና መልዕክተኛውን የመጨረሻይቱን አገርም የምትፈልጉ ከሆናችሁ እነሆ አላህ ከናንተ ለመልካም ሰሪዎቹ ትልቅን ምንዳ አዘጋጅቷል።»

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

يَٰنِسَآءَ ٱلنَّبِىِّ مَن يَأْتِ مِنكُنَّ بِفَٰحِشَةٍ مُّبَيِّنَةٍ يُضَٰعَفْ لَهَا ٱلْعَذَابُ ضِعْفَيْنِ وَكَانَ ذَٰلِكَ عَلَى ٱللَّهِ يَسِيرًا

Amharic Translation - Africa Academy30. እናንተ የነብዩ ሚስቶች ሆይ! ከናንተ ውስጥ ግልጽ የሆነን መጥፎ ስራ የምትሰራ ሴት ቅጣቷ ሁለት እጥፍ ሆኖ ይነባበርባታል:: ይህም በአላህ ዘንድ ገር ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَمَن يَقْنُتْ مِنكُنَّ لِلَّهِ وَرَسُولِهِۦ وَتَعْمَلْ صَٰلِحًا نُّؤْتِهَآ أَجْرَهَا مَرَّتَيْنِ وَأَعْتَدْنَا لَهَا رِزْقًا كَرِيمًا

Amharic Translation - Africa Academy31. ከናንተም መካከል ለአላህና ለመልዕክተኛው የምትታዘዝ መልካም ስራንም የምትሰራ ሴት ምንዳዋን ሁለት ጊዜ እንሰጣታለን:: ለእርሷም የከበረን ሲሳይ አዘጋጅተንላታል።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

يَٰنِسَآءَ ٱلنَّبِىِّ لَسْتُنَّ كَأَحَدٍ مِّنَ ٱلنِّسَآءِ إِنِ ٱتَّقَيْتُنَّ فَلَا تَخْضَعْنَ بِٱلْقَوْلِ فَيَطْمَعَ ٱلَّذِى فِى قَلْبِهِۦ مَرَضٌ وَقُلْنَ قَوْلًا مَّعْرُوفًا

Amharic Translation - Africa Academy32. እናንተ የነቢዩ ሚስቶች ሆይ! እንደ ማናቸዉም ሴቶች አይደላችሁም:: አላህን ብትፈሩ ትበልጣላችሁ። በልቡ ውስጥ በሽታ ያለበት እንዳይከጅል በንግግር እንኳን አትለስልሱም:: መልካምንም ንግግር ተናገሩ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَقَرْنَ فِى بُيُوتِكُنَّ وَلَا تَبَرَّجْنَ تَبَرُّجَ ٱلْجَٰهِلِيَّةِ ٱلْأُولَىٰ وَأَقِمْنَ ٱلصَّلَوٰةَ وَءَاتِينَ ٱلزَّكَوٰةَ وَأَطِعْنَ ٱللَّهَ وَرَسُولَهُۥٓ إِنَّمَا يُرِيدُ ٱللَّهُ لِيُذْهِبَ عَنكُمُ ٱلرِّجْسَ أَهْلَ ٱلْبَيْتِ وَيُطَهِّرَكُمْ تَطْهِيرًا

Amharic Translation - Africa Academy33. በቤቶቻችሁም ውስጥ እርጉ:: እንደ ፊተኛይቱ መሃይምነት ጊዜ መገላለጥም (በመጌጥ) አትገለጡ:: ሶላትንም በደንቡ ስገዱ:: ዘካንም ስጡ:: አላህንና መልክተኛውንም ታዘዙ:: የነብዩ ቤተሰቦች ሆይ! አላህ የሚሻው ከናንተ ላይ ርክሰትን ሊያስወግድና ማጥራትንም ሊያጠራችሁ ብቻ ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَٱذْكُرْنَ مَا يُتْلَىٰ فِى بُيُوتِكُنَّ مِنْ ءَايَٰتِ ٱللَّهِ وَٱلْحِكْمَةِ إِنَّ ٱللَّهَ كَانَ لَطِيفًا خَبِيرًا

Amharic Translation - Africa Academy34. ከአላህ አናቅጽና ከጥበቡም በቤቶቻችሁ የሚነበበውን አስታውሱ:: አላህ እዝነቱ ረቂቅና ውስጠ አዋቂ ነውና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّ ٱلْمُسْلِمِينَ وَٱلْمُسْلِمَٰتِ وَٱلْمُؤْمِنِينَ وَٱلْمُؤْمِنَٰتِ وَٱلْقَٰنِتِينَ وَٱلْقَٰنِتَٰتِ وَٱلصَّٰدِقِينَ وَٱلصَّٰدِقَٰتِ وَٱلصَّٰبِرِينَ وَٱلصَّٰبِرَٰتِ وَٱلْخَٰشِعِينَ وَٱلْخَٰشِعَٰتِ وَٱلْمُتَصَدِّقِينَ وَٱلْمُتَصَدِّقَٰتِ وَٱلصَّٰٓئِمِينَ وَٱلصَّٰٓئِمَٰتِ وَٱلْحَٰفِظِينَ فُرُوجَهُمْ وَٱلْحَٰفِظَٰتِ وَٱلذَّٰكِرِينَ ٱللَّهَ كَثِيرًا وَٱلذَّٰكِرَٰتِ أَعَدَّ ٱللَّهُ لَهُم مَّغْفِرَةً وَأَجْرًا عَظِيمًا

Amharic Translation - Africa Academy35. ሙስሊም ወንዶችና ሙስሊም ሴቶች፤ ምእምናንና ምዕመናትም፤ ታዛዦች ወንዶችና ታዛዦች ሴቶችም፤ እውነተኞች ወንዶችና እውነተኞች ሴቶችም፤ ታጋሽ ወንዶችና ታጋሽ ሴቶችም፤ አላህን ፈሪ ወንዶችና አላህን ፈሪ ሴቶችም፤ መጽዋች ወንዶችና መጽዋች ሴቶችም፤ ጿሚ ወንዶችና ጿሚ ሴቶችም፤ ካልተፈቀደ ስራ ብልቶቻቸውን ጠባቂ ወንዶችና ጠባቂ ሴቶችም፤ አላህን በብዙ አውሺ ወንዶችና አውሺ ሴቶችም አላህ ለእነርሱ ምህረትንና ታላቅን ምንዳ አዘጋጅቶላቸዋል::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَمَا كَانَ لِمُؤْمِنٍ وَلَا مُؤْمِنَةٍ إِذَا قَضَى ٱللَّهُ وَرَسُولُهُۥٓ أَمْرًا أَن يَكُونَ لَهُمُ ٱلْخِيَرَةُ مِنْ أَمْرِهِمْ وَمَن يَعْصِ ٱللَّهَ وَرَسُولَهُۥ فَقَدْ ضَلَّ ضَلَٰلًا مُّبِينًا

Amharic Translation - Africa Academy36. አላህና መልዕክተኛው በአንድ ነገር ላይ በወሰኑ ጊዜ ለምዕምናንና ለምዕመናት ከተነገራቸው ከመቀበል ዉጭ ምንም ምርጫ ሊኖራቸው አይገባም:: የአላህንና የመልክተኛውን ትእዛዝ የጣሰ ሰው ሁሉ ግልጽ የሆነን መሳሳት በእርግጥ ተሳሳተ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَإِذْ تَقُولُ لِلَّذِىٓ أَنْعَمَ ٱللَّهُ عَلَيْهِ وَأَنْعَمْتَ عَلَيْهِ أَمْسِكْ عَلَيْكَ زَوْجَكَ وَٱتَّقِ ٱللَّهَ وَتُخْفِى فِى نَفْسِكَ مَا ٱللَّهُ مُبْدِيهِ وَتَخْشَى ٱلنَّاسَ وَٱللَّهُ أَحَقُّ أَن تَخْشَىٰهُ فَلَمَّا قَضَىٰ زَيْدٌ مِّنْهَا وَطَرًا زَوَّجْنَٰكَهَا لِكَىْ لَا يَكُونَ عَلَى ٱلْمُؤْمِنِينَ حَرَجٌ فِىٓ أَزْوَٰجِ أَدْعِيَآئِهِمْ إِذَا قَضَوْا۟ مِنْهُنَّ وَطَرًا وَكَانَ أَمْرُ ٱللَّهِ مَفْعُولًا

Amharic Translation - Africa Academy37. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ለዚያም አላህ በእርሱ ላይ ለለገሰለትና አንተም (ነጻ በማውጣት) በእርሱ ላይ ለለገስክለት ሰው አላህ ገላጩ የሆነን ነገር በነፍስህ ውስጥ የምትደብቅና አላህን ልትፈራው ይልቅ የተገባው ሲሆን ሰዎችን የምትፈራ ሆነህ «ሚስትህን ያዝ:: አላህንም ፍራ» በምትል ጊዜ (የሆነዉን አስታውስ):: ዘይድም ከእርሷ ጉዳዩን በፈጸመ ጊዜ በምዕመኖች ላይ ልጅ አድርገው ባስጠጓቸው ሰዎች ሚስቶች ከእነርሱ ጉዳይን በፈጸሙ ጊዜ በማግባት ችግር እንዳይደርስባቸው እርሷን አጋባንህ (ዳርንህ):: የአላህም ትእዛዝ ተፈጻሚ ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

مَّا كَانَ عَلَى ٱلنَّبِىِّ مِنْ حَرَجٍ فِيمَا فَرَضَ ٱللَّهُ لَهُۥ سُنَّةَ ٱللَّهِ فِى ٱلَّذِينَ خَلَوْا۟ مِن قَبْلُ وَكَانَ أَمْرُ ٱللَّهِ قَدَرًا مَّقْدُورًا

Amharic Translation - Africa Academy38. በነብዩ ላይ አላህ ለእርሱ በፈረደው ነገር ምንም ችግር ሊኖርበት አይገባም:: በእነዚያ ከዚያ በፊት ባለፉት ነብያት አላህ ደነገገው። የአላህም ትእዛዝ የተፈረደ ፍርድ ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ٱلَّذِينَ يُبَلِّغُونَ رِسَٰلَٰتِ ٱللَّهِ وَيَخْشَوْنَهُۥ وَلَا يَخْشَوْنَ أَحَدًا إِلَّا ٱللَّهَ وَكَفَىٰ بِٱللَّهِ حَسِيبًا

Amharic Translation - Africa Academy39. ለእነዚያ የአላህን መልዕክቶች ለሚያደርሱና ለሚፈሩት ከአላህ በስተቀርም አንድንም ለማይፈሩት ተደነገገ። ተቆጣጣሪነትም በአላህ በቃ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

مَّا كَانَ مُحَمَّدٌ أَبَآ أَحَدٍ مِّن رِّجَالِكُمْ وَلَٰكِن رَّسُولَ ٱللَّهِ وَخَاتَمَ ٱلنَّبِيِّـۧنَ وَكَانَ ٱللَّهُ بِكُلِّ شَىْءٍ عَلِيمًا

Amharic Translation - Africa Academy40. (እናንተ ያመናችሁ ሆይ!) ሙሐመድ ከወንዶቻችሁ የአንዱም ሰው አባት አይደለም:: ግን የአላህ መልዕክተኛና የነብያት መደምደሚያ ነው:: አላህ በነገሩ ሁሉ አዋቂ ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ ٱذْكُرُوا۟ ٱللَّهَ ذِكْرًا كَثِيرًا

Amharic Translation - Africa Academy41. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ብዙ ማውሳትን አውሱት::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَسَبِّحُوهُ بُكْرَةً وَأَصِيلًا

Amharic Translation - Africa Academy42. በቀኑ መጀመሪያና መጨረሻም አጥሩት::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

هُوَ ٱلَّذِى يُصَلِّى عَلَيْكُمْ وَمَلَٰٓئِكَتُهُۥ لِيُخْرِجَكُم مِّنَ ٱلظُّلُمَٰتِ إِلَى ٱلنُّورِ وَكَانَ بِٱلْمُؤْمِنِينَ رَحِيمًا

Amharic Translation - Africa Academy43. እርሱ ያ በእናንተ ላይ እዝነትን የሚያወርድ ነው:: መላእክቶችም እንደዚሁ ምህረትን የሚለምኑላችሁ ናቸው:: ከጨለማዎች ወደ ብርሃን ያወጣችሁ ዘንድ (ያዝንላችኋል):: ለትክክለኛ አማኞችም በጣም አዛኝ ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

تَحِيَّتُهُمْ يَوْمَ يَلْقَوْنَهُۥ سَلَٰمٌ وَأَعَدَّ لَهُمْ أَجْرًا كَرِيمًا

Amharic Translation - Africa Academy44. በሚገናኙበት ቀን መከባበሪያቸው ሰላም መባባል ነው:: ለእነርሱም የከበረን ምንዳ አዘጋጅቶላቸዋል::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

يَٰٓأَيُّهَا ٱلنَّبِىُّ إِنَّآ أَرْسَلْنَٰكَ شَٰهِدًا وَمُبَشِّرًا وَنَذِيرًا

Amharic Translation - Africa Academy45. አንተ ነብይ ሆይ! እኛ መስካሪ አብሳሪና አስፈራሪ አድርገን ላክንህ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَدَاعِيًا إِلَى ٱللَّهِ بِإِذْنِهِۦ وَسِرَاجًا مُّنِيرًا

Amharic Translation - Africa Academy46. ወደ አላህም በፈቃዱ ጠሪ፣ አብሪና ብርሃን አድርገን ላክንህ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَبَشِّرِ ٱلْمُؤْمِنِينَ بِأَنَّ لَهُم مِّنَ ٱللَّهِ فَضْلًا كَبِيرًا

Amharic Translation - Africa Academy47. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አማኞችንም ከአላህ ዘንድ ለእነርሱ ታላቅ ችሮታ ያላቸው መሆኑን አብስራቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلَا تُطِعِ ٱلْكَٰفِرِينَ وَٱلْمُنَٰفِقِينَ وَدَعْ أَذَىٰهُمْ وَتَوَكَّلْ عَلَى ٱللَّهِ وَكَفَىٰ بِٱللَّهِ وَكِيلًا

Amharic Translation - Africa Academy48. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከሓዲያንና አስመሳዮችንም አትታዘዛቸው ማሰቃየታቸውንም (ለአላህ) ተው:: በአላህም ላይ ተጠጋ:: በመጠጊያነትም አላህ በቃ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓا۟ إِذَا نَكَحْتُمُ ٱلْمُؤْمِنَٰتِ ثُمَّ طَلَّقْتُمُوهُنَّ مِن قَبْلِ أَن تَمَسُّوهُنَّ فَمَا لَكُمْ عَلَيْهِنَّ مِنْ عِدَّةٍ تَعْتَدُّونَهَا فَمَتِّعُوهُنَّ وَسَرِّحُوهُنَّ سَرَاحًا جَمِيلًا

Amharic Translation - Africa Academy49. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ምዕመናትን ባገባችሁና ከዚያም ሳትነኳቸው በፊት በፈታችኋቸው ጊዜ ለናንተ በእነርሱ ላይ የምትቆጥሩዋት ዒዳ ምንም የላችሁም:: ሆኖም አጣቅሟቸው (ጉርሻ ስጧቸው):: መልካም ማሰናበትንም አሰናብቷቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

يَٰٓأَيُّهَا ٱلنَّبِىُّ إِنَّآ أَحْلَلْنَا لَكَ أَزْوَٰجَكَ ٱلَّٰتِىٓ ءَاتَيْتَ أُجُورَهُنَّ وَمَا مَلَكَتْ يَمِينُكَ مِمَّآ أَفَآءَ ٱللَّهُ عَلَيْكَ وَبَنَاتِ عَمِّكَ وَبَنَاتِ عَمَّٰتِكَ وَبَنَاتِ خَالِكَ وَبَنَاتِ خَٰلَٰتِكَ ٱلَّٰتِى هَاجَرْنَ مَعَكَ وَٱمْرَأَةً مُّؤْمِنَةً إِن وَهَبَتْ نَفْسَهَا لِلنَّبِىِّ إِنْ أَرَادَ ٱلنَّبِىُّ أَن يَسْتَنكِحَهَا خَالِصَةً لَّكَ مِن دُونِ ٱلْمُؤْمِنِينَ قَدْ عَلِمْنَا مَا فَرَضْنَا عَلَيْهِمْ فِىٓ أَزْوَٰجِهِمْ وَمَا مَلَكَتْ أَيْمَٰنُهُمْ لِكَيْلَا يَكُونَ عَلَيْكَ حَرَجٌ وَكَانَ ٱللَّهُ غَفُورًا رَّحِيمًا

Amharic Translation - Africa Academy50. አንተ ነብይ ሆይ! እነዚያን መህሮቻቸውን የሰጠሃቸውን ሚስቶችህን፤ አላህ ባንተ ላይ ከመለሰልህም ሴቶች መካከል እነዚያን እጅህ የጨበጠቻቸውን ምርኮኞች ሴቶች፤ እነዚያን ካንተ ጋር የተሰደዱትን የአጎቶችህንና፤ የአክስቶችህን ሴት ልጆች (እንደዚሁም) የእናትህ ወንድም ሴት ልጆችና የእናትህ እህት ሴት ልጆች ማግባትን ላንተ ፈቅደንልሃል:: ማንኛዋም በአላህ ያመነች ሴት ራሷን ለነብዩ ብትሰጥ ነብዩ ሊያገባት የፈለገ እንደ ሆነ ከአማኞች ሌላ ላንተ ብቻ የተሰጠ መብት ሲሆን ፈቀድንልህ:: በአማኞች ላይ በሚስቶቻቸውና እጆቻቸው በጨበጧቸው ባሮች ነገር ግዴታ ያደረግንባቸውን በእርግጥ አውቀናል:: ባንተ ላይ ችግር እንዳይኖር ያለፉትን ፈቀድንልህ:: አላህ መሃሪና አዛኝ ነውና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

تُرْجِى مَن تَشَآءُ مِنْهُنَّ وَتُـْٔوِىٓ إِلَيْكَ مَن تَشَآءُ وَمَنِ ٱبْتَغَيْتَ مِمَّنْ عَزَلْتَ فَلَا جُنَاحَ عَلَيْكَ ذَٰلِكَ أَدْنَىٰٓ أَن تَقَرَّ أَعْيُنُهُنَّ وَلَا يَحْزَنَّ وَيَرْضَيْنَ بِمَآ ءَاتَيْتَهُنَّ كُلُّهُنَّ وَٱللَّهُ يَعْلَمُ مَا فِى قُلُوبِكُمْ وَكَانَ ٱللَّهُ عَلِيمًا حَلِيمًا

Amharic Translation - Africa Academy51. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከእነርሱ መካከል የምትፈልጋትን ታቆያለህ :: የምትፈልጋትንም ወደ አንተ ታስጠጋለህ:: በመፍታት ከአራቅሃትም የፈለግሃትን በመመለስ ብታስጠጋ ባንተ ላይ ኃጢአት የለብህም:: ይህ ዓይኖቻቸው ወደ መርጋት ወደ አለማዘናቸዉም ለሁሉም በሰጠሃቸው ነገር ወደ መውደዳቸዉም በጣም የቀረበ ነው:: አላህም በልቦቻችሁ ውስጥ ያለውን ሁሉ ያውቃል:: አላህ ሁሉን አዋቂና ታጋሽ ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

لَّا يَحِلُّ لَكَ ٱلنِّسَآءُ مِنۢ بَعْدُ وَلَآ أَن تَبَدَّلَ بِهِنَّ مِنْ أَزْوَٰجٍ وَلَوْ أَعْجَبَكَ حُسْنُهُنَّ إِلَّا مَا مَلَكَتْ يَمِينُكَ وَكَانَ ٱللَّهُ عَلَىٰ كُلِّ شَىْءٍ رَّقِيبًا

Amharic Translation - Africa Academy52. ከእነዚህ በኋላ እጅህ ከጨበጠቻቸው ባሮች በስተቀር ሴቶች ላንተ አይፈቅዱልህም ከሚስቶችም መልካቸው ቢደንቅህም እንኳን በእነርሱ ልትለውጥ አይፈቀድልህም። አላህ በነገሩ ሁሉ ተጠባባቂ ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ لَا تَدْخُلُوا۟ بُيُوتَ ٱلنَّبِىِّ إِلَّآ أَن يُؤْذَنَ لَكُمْ إِلَىٰ طَعَامٍ غَيْرَ نَٰظِرِينَ إِنَىٰهُ وَلَٰكِنْ إِذَا دُعِيتُمْ فَٱدْخُلُوا۟ فَإِذَا طَعِمْتُمْ فَٱنتَشِرُوا۟ وَلَا مُسْتَـْٔنِسِينَ لِحَدِيثٍ إِنَّ ذَٰلِكُمْ كَانَ يُؤْذِى ٱلنَّبِىَّ فَيَسْتَحْىِۦ مِنكُمْ وَٱللَّهُ لَا يَسْتَحْىِۦ مِنَ ٱلْحَقِّ وَإِذَا سَأَلْتُمُوهُنَّ مَتَٰعًا فَسْـَٔلُوهُنَّ مِن وَرَآءِ حِجَابٍ ذَٰلِكُمْ أَطْهَرُ لِقُلُوبِكُمْ وَقُلُوبِهِنَّ وَمَا كَانَ لَكُمْ أَن تُؤْذُوا۟ رَسُولَ ٱللَّهِ وَلَآ أَن تَنكِحُوٓا۟ أَزْوَٰجَهُۥ مِنۢ بَعْدِهِۦٓ أَبَدًا إِنَّ ذَٰلِكُمْ كَانَ عِندَ ٱللَّهِ عَظِيمًا

Amharic Translation - Africa Academy53. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! መድረሱን የማትጠባበቁ ስትሆኑ ወደ ምግብ ካልተፈቀደላችሁ በስተቀር የነብዩን ቤቶች በምንም ጊዜ አትግቡ ግን በተጠራችሁ ጊዜ ግቡ በተመገባችሁም ጊዜ ወዲያውኑ ተበተኑ:: ለወግ የምትጫወቱ ሆናችሁም አትቆዩ:: ይሃችሁ ነብዩን በእርግጥ ያስቸግራል:: ከናንተም ያፍራል። ግን አላህ ከእውነት አያፍርም:: እቃንም ለመዋስ በጠየቃችኋቸው ጊዜ ከመጋረጃ ኋላ ሆናችሁ ጠይቋቸው። ይሃችሁ ለልቦቻችሁም ለልቦቻቸዉም የበለጠ ንጽህና ነው:: የአላህንም መልክተኛ ልታስቸግሩ ሚስቶቹንም ከእርሱ በኋላ ምንጊዜም ልታገቡ ለእናንተ አይገባችሁም። ይሃችሁ አላህ ዘንድ ከባድ ኃጢአት ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِن تُبْدُوا۟ شَيْـًٔا أَوْ تُخْفُوهُ فَإِنَّ ٱللَّهَ كَانَ بِكُلِّ شَىْءٍ عَلِيمًا

Amharic Translation - Africa Academy54. ማንኛውንም ነገር ብትገልጹ ወይም ብትደብቁት በእርሱ ይመነዳችኋል:: አላህ ነገሩን ሁሉ አዋቂ ነውና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

لَّا جُنَاحَ عَلَيْهِنَّ فِىٓ ءَابَآئِهِنَّ وَلَآ أَبْنَآئِهِنَّ وَلَآ إِخْوَٰنِهِنَّ وَلَآ أَبْنَآءِ إِخْوَٰنِهِنَّ وَلَآ أَبْنَآءِ أَخَوَٰتِهِنَّ وَلَا نِسَآئِهِنَّ وَلَا مَا مَلَكَتْ أَيْمَٰنُهُنَّ وَٱتَّقِينَ ٱللَّهَ إِنَّ ٱللَّهَ كَانَ عَلَىٰ كُلِّ شَىْءٍ شَهِيدًا

Amharic Translation - Africa Academy55. (የነብዩ ሚስቶች) በአባቶቻቸው፣ በወንዶች ልጆቻቸዉም፣ በወንድሞቻቸውም፣ በወንድሞቻቸው ወንዶች ልጆችም፣ በእኅቶቻቸው ወንዶች ልጆችም፣ ምዕመናት በሆኑት በሴቶቻቸዉም በጨበጧቸዉም ባሮች (አጠገብ ቢገለጡ) በእነርሱ ላይ ምንም ኃጢአት የለባቸዉም:: (ሴቶች ሆይ!) (ታዘዙ):: አላህን ፍሩ:: አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ መስካሪ ነውና፡

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّ ٱللَّهَ وَمَلَٰٓئِكَتَهُۥ يُصَلُّونَ عَلَى ٱلنَّبِىِّ يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ صَلُّوا۟ عَلَيْهِ وَسَلِّمُوا۟ تَسْلِيمًا

Amharic Translation - Africa Academy56. አላህና መላዕክቱ በነብዩ (ሙሐመድ) ላይ የአክብሮት እዝነትን ያወርዳሉ:: እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በእርሱ ላይ የአክብሮት እዝነትን አውርዱ:: የማክበርን ሰላምታንም ሰላም በሉ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّ ٱلَّذِينَ يُؤْذُونَ ٱللَّهَ وَرَسُولَهُۥ لَعَنَهُمُ ٱللَّهُ فِى ٱلدُّنْيَا وَٱلْـَٔاخِرَةِ وَأَعَدَّ لَهُمْ عَذَابًا مُّهِينًا

Amharic Translation - Africa Academy57. እነዚያ አላህንና መልክተኛውን የሚያስከፉ በቅርቢቱ ዓለምም ሆነ በመጨረሻይቱ ዓለም አላህ ረግሟቸዋል:: ለእነርሱም አዋራጅን ቅጣት ደግሶላቸዋል::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَٱلَّذِينَ يُؤْذُونَ ٱلْمُؤْمِنِينَ وَٱلْمُؤْمِنَٰتِ بِغَيْرِ مَا ٱكْتَسَبُوا۟ فَقَدِ ٱحْتَمَلُوا۟ بُهْتَٰنًا وَإِثْمًا مُّبِينًا

Amharic Translation - Africa Academy58. እነዚያም አማኞችና ምዕመናትን ባልሰሩት ነገር በመዝለፍ የሚያሰቃዩ ዕብለትንና ግልጽ ኃጢአትን በእርግጥ ተሸከሙ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

يَٰٓأَيُّهَا ٱلنَّبِىُّ قُل لِّأَزْوَٰجِكَ وَبَنَاتِكَ وَنِسَآءِ ٱلْمُؤْمِنِينَ يُدْنِينَ عَلَيْهِنَّ مِن جَلَٰبِيبِهِنَّ ذَٰلِكَ أَدْنَىٰٓ أَن يُعْرَفْنَ فَلَا يُؤْذَيْنَ وَكَانَ ٱللَّهُ غَفُورًا رَّحِيمًا

Amharic Translation - Africa Academy59. አንተ ነብይ ሆይ ! ለሚስቶችህ ለሴቶች ልጆችህም ለትክክለኛ አማኞች ሚስቶችም ከመከናነቢያዎቻቸው በላያቸው ላይ እንዲለቁ ንገራቸው። ይህ እንዳይታወቁና በባለጌዎች እንዳይደፈሩ ለመሆን በጣም የቀረበ ነው:: አላህ መሃሪና አዛኝ ነውና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

لَّئِن لَّمْ يَنتَهِ ٱلْمُنَٰفِقُونَ وَٱلَّذِينَ فِى قُلُوبِهِم مَّرَضٌ وَٱلْمُرْجِفُونَ فِى ٱلْمَدِينَةِ لَنُغْرِيَنَّكَ بِهِمْ ثُمَّ لَا يُجَاوِرُونَكَ فِيهَآ إِلَّا قَلِيلًا

Amharic Translation - Africa Academy60. አስመሳዮችና እነዚያ በልቦቻቸው ውስጥ (የአመንዝራነት) በሽታ ያለባቸው በመዲናም ውስጥ (በወሬ) አሸባሪዎቹ ከዚህ ስራቸው ባይከለከሉ በእነርሱ ላይ በእርግጥ እንቀሰቅስሃለን ከዚያ በእርሷ ውስጥ ጥቂትን እንጂ አይጎራበቱህም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

مَّلْعُونِينَ أَيْنَمَا ثُقِفُوٓا۟ أُخِذُوا۟ وَقُتِّلُوا۟ تَقْتِيلًا

Amharic Translation - Africa Academy61. የተረገሙ ሆነው እንጂ አይጎራበቱህም:: በየትም ስፍራ ቢገኙ ይያዛሉ:: መገደልንም ይገደላሉ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

سُنَّةَ ٱللَّهِ فِى ٱلَّذِينَ خَلَوْا۟ مِن قَبْلُ وَلَن تَجِدَ لِسُنَّةِ ٱللَّهِ تَبْدِيلًا

Amharic Translation - Africa Academy62. እነዚህ ህጎች በእነዚያ ከዚህ በፊት ባለፉት ህዝቦች ላይ የደነገጋቸው የአላህ ድንጋጌ ናቸው:: ለአላህም ድንጋጌዎች ደግሞ ፈጽሞ መለወጥን አታገኝም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

يَسْـَٔلُكَ ٱلنَّاسُ عَنِ ٱلسَّاعَةِ قُلْ إِنَّمَا عِلْمُهَا عِندَ ٱللَّهِ وَمَا يُدْرِيكَ لَعَلَّ ٱلسَّاعَةَ تَكُونُ قَرِيبًا

Amharic Translation - Africa Academy63. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ሰዎች ከሰዓቲቱ ይጠይቁሃል:: «እውቀቷ አላህ ዘንድ ብቻ ነው።» በላቸው:: የሚያሳውቅህም ምንድን ነው! ሰዓቲቱ በቅርብ ጊዜ ልትሆን ይከጀላል::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّ ٱللَّهَ لَعَنَ ٱلْكَٰفِرِينَ وَأَعَدَّ لَهُمْ سَعِيرًا

Amharic Translation - Africa Academy64. አላህ ከሓዲያንን በእርግጥ ረግሟቸዋል። ለነርሱም የተጋገመችን እሳት አዘጋጅቷል::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

خَٰلِدِينَ فِيهَآ أَبَدًا لَّا يَجِدُونَ وَلِيًّا وَلَا نَصِيرًا

Amharic Translation - Africa Academy65. በእርሷ ውስጥ ዘለዓለም ዘውታሪዎች ሲሆኑ ወዳጅም ረዳትም አያገኙም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

يَوْمَ تُقَلَّبُ وُجُوهُهُمْ فِى ٱلنَّارِ يَقُولُونَ يَٰلَيْتَنَآ أَطَعْنَا ٱللَّهَ وَأَطَعْنَا ٱلرَّسُولَا۠

Amharic Translation - Africa Academy66. ፊቶቻቸው በእሳት ውስጥ በሚገለባበጡ ቀን «ዋ ምኞታችን! አላህን በተገዛን መልክተኛውንም በታዘዝን ኖሮ» እያሉ ይጸጸታሉ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَقَالُوا۟ رَبَّنَآ إِنَّآ أَطَعْنَا سَادَتَنَا وَكُبَرَآءَنَا فَأَضَلُّونَا ٱلسَّبِيلَا۠

Amharic Translation - Africa Academy67. ይላሉም «ጌታችን ሆይ! እኛ ጌቶቻችንንና ታላላቆቻችንን ታዘዝን መንገዱንም አሳሳቱን።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

رَبَّنَآ ءَاتِهِمْ ضِعْفَيْنِ مِنَ ٱلْعَذَابِ وَٱلْعَنْهُمْ لَعْنًا كَبِيرًا

Amharic Translation - Africa Academy68. «ጌታችን ሆይ! ከቅጣቱ እጥፍን ስጣቸው ታላቅን እርግማንም እርገማቸው::»

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ لَا تَكُونُوا۟ كَٱلَّذِينَ ءَاذَوْا۟ مُوسَىٰ فَبَرَّأَهُ ٱللَّهُ مِمَّا قَالُوا۟ وَكَانَ عِندَ ٱللَّهِ وَجِيهًا

Amharic Translation - Africa Academy69. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! እንደ እነዚያ ሙሳን እንዳሰቃዩት ሰዎች አትሁኑ ካሉትም ነገር ሁሉ አላህ አጠራው:: አላህም ዘንድ ባለሞገስ ነበር::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ ٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَ وَقُولُوا۟ قَوْلًا سَدِيدًا

Amharic Translation - Africa Academy70. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ፍሩ:: ትክክለኛን ንግግርም ተናገሩ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

يُصْلِحْ لَكُمْ أَعْمَٰلَكُمْ وَيَغْفِرْ لَكُمْ ذُنُوبَكُمْ وَمَن يُطِعِ ٱللَّهَ وَرَسُولَهُۥ فَقَدْ فَازَ فَوْزًا عَظِيمًا

Amharic Translation - Africa Academy71. ስራዎቻችሁን ለእናንተ ያበጅላችኋልና ኃጢአቶቻችሁንም ለእናንተ ይምርላችኋል:: አላህንና መልዕክተኛውን የሚታዘዝ ሁሉ በእርግጥ ታላቅን እድል አገኘ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّا عَرَضْنَا ٱلْأَمَانَةَ عَلَى ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِ وَٱلْجِبَالِ فَأَبَيْنَ أَن يَحْمِلْنَهَا وَأَشْفَقْنَ مِنْهَا وَحَمَلَهَا ٱلْإِنسَٰنُ إِنَّهُۥ كَانَ ظَلُومًا جَهُولًا

Amharic Translation - Africa Academy72. እኛ አደራን በሰማያት በምድር እና በተራራዎች ላይ አቀረብናት:: መሸከሟንም እንቢ አሉ ከእርሷም ፈሩ። ሰው ግን ተሸከማት እርሱ በጣም በደለኛና ተሳሳች ነውና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

لِّيُعَذِّبَ ٱللَّهُ ٱلْمُنَٰفِقِينَ وَٱلْمُنَٰفِقَٰتِ وَٱلْمُشْرِكِينَ وَٱلْمُشْرِكَٰتِ وَيَتُوبَ ٱللَّهُ عَلَى ٱلْمُؤْمِنِينَ وَٱلْمُؤْمِنَٰتِ وَكَانَ ٱللَّهُ غَفُورًا رَّحِيمًۢا

Amharic Translation - Africa Academy73. ወንዶች አስመሳዮችንና ሴቶች አስመሳዮችን ወንዶች አጋሪዎችንና ሴቶች አጋሪዎችንም አላህ ሊቀጣ በምዕምናንና በምዕመናትም ላይ አላህ ንስሃን ሊቀበል (አደራዋን ሰው ተሸከማት):: አላህ መሃሪና አዛኝ ነውና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70