قَالَ ٱلَّذِى عِندَهُۥ عِلْمٌ مِّنَ ٱلْكِتَٰبِ أَنَا۠ ءَاتِيكَ بِهِۦ قَبْلَ أَن يَرْتَدَّ إِلَيْكَ طَرْفُكَ فَلَمَّا رَءَاهُ مُسْتَقِرًّا عِندَهُۥ قَالَ هَٰذَا مِن فَضْلِ رَبِّى لِيَبْلُوَنِىٓ ءَأَشْكُرُ أَمْ أَكْفُرُ وَمَن شَكَرَ فَإِنَّمَا يَشْكُرُ لِنَفْسِهِۦ وَمَن كَفَرَ فَإِنَّ رَبِّى غَنِىٌّ كَرِيمٌ
Amharic Translation - Africa Academy40. ያ እርሱ ዘንድ ከመጽሐፉ ጥልቅ ዕውቀት ያለው ሰው «የተገለጸው ዓይንህ ወደ አንተ ከመመለሱ በፊት እኔ እርሱን አመጣልሃለሁ።» አለ:: እንደዚሁም አደረገ:: እርሱ ዘንድ ረግቶ ባየዉም ጊዜ «ይህ ከጌታዬ ችሮታ ነው። የማመሰግን ወይም የምክድ መሆኔን ሊሞክረኝ ቸረልኝ:: አላህን ያመሰገነ ሁሉ የሚያመሰግነው ለራሱ ነው:: አላህን የካደም ሰው ሁሉ ጌታዬ ከእርሱ ተብቃቂ፤ ቸር ነው።» አለ::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqያ እርሱ ዘንድ ከመጽሐፉ ዕውቀት ያለው ሰው (የተገለጸው) «ዓይንህ ወደ አንተ ከመመለሱ በፊት እኔ እርሱን አመጣልሃለሁ» አለ፤ (እንደዚሁም አደረገ)፡፡ እርሱ ዘንድ ረግቶ ባየውም ጊዜ «ይህ ከጌታዬ ችሮታ ነው፡፡ የማመሰግን ወይም የምክድ መኾኔን ሊሞክረኝ (ቸረልኝ)፡፡ ያመሰገነም ሰው የሚያመሰግነው ለራሱ ነው፡፡ የካደም ሰው ጌታዬ (ከእርሱ) ተብቃቂ ቸር ነው» አለ፡፡