ሱረቱ Al-Qasas القصص
88 አንቀጾች · መካ · የወረደበት ቅደም ተከተል 49
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ طسٓمٓ
Amharic Translation - Africa Academy1.ጧ፤ ሲን፤ ሚም፤
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
تِلْكَ ءَايَٰتُ ٱلْكِتَٰبِ ٱلْمُبِينِ
Amharic Translation - Africa Academy2. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚህ አናቅጽ ገላጭ ከሆነው መጽሐፍ አናቅጽ ናቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
نَتْلُوا۟ عَلَيْكَ مِن نَّبَإِ مُوسَىٰ وَفِرْعَوْنَ بِٱلْحَقِّ لِقَوْمٍ يُؤْمِنُونَ
Amharic Translation - Africa Academy3. ከሙሳና ከፈርዖን ዜና ለሚያምኑ ህዝቦች ሁሉ ባንተ ላይ እናነባለን::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِنَّ فِرْعَوْنَ عَلَا فِى ٱلْأَرْضِ وَجَعَلَ أَهْلَهَا شِيَعًا يَسْتَضْعِفُ طَآئِفَةً مِّنْهُمْ يُذَبِّحُ أَبْنَآءَهُمْ وَيَسْتَحْىِۦ نِسَآءَهُمْ إِنَّهُۥ كَانَ مِنَ ٱلْمُفْسِدِينَ
Amharic Translation - Africa Academy4. ፈርዖን በምድር ላይ ተንበጣረረ:: ነዋሪዎቿንም የተከፋፈሉ ጓዶች አደረጋቸው:: ከእነርሱም ቡድኖችን ያዳክማል:: ወንዶች ልጆቻቸውን በብዛት ያርዳል:: ሴቶቻቸውንም ይተዋል፤ እርሱ ከሚያበላሹት ሰዎች ነበርና::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَنُرِيدُ أَن نَّمُنَّ عَلَى ٱلَّذِينَ ٱسْتُضْعِفُوا۟ فِى ٱلْأَرْضِ وَنَجْعَلَهُمْ أَئِمَّةً وَنَجْعَلَهُمُ ٱلْوَٰرِثِينَ
Amharic Translation - Africa Academy5. በእነዚያ በምድር ውስጥ በተጨቆኑት ህዝቦች ላይ ልንለግስና መሪዎችም ልናደርጋቸው ወራሾችም ልናደርጋቸው እንሻለን::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَنُمَكِّنَ لَهُمْ فِى ٱلْأَرْضِ وَنُرِىَ فِرْعَوْنَ وَهَٰمَٰنَ وَجُنُودَهُمَا مِنْهُم مَّا كَانُوا۟ يَحْذَرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy6. ለእነርሱም በምድር ላይ ልናስመች ፈርዖንን፤ ሃማንንና ሰራዊቶቻቸውንም ከእነርሱ ይፈሩት የነበሩትን ነገር ልናሳያቸው እንሻለን::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَأَوْحَيْنَآ إِلَىٰٓ أُمِّ مُوسَىٰٓ أَنْ أَرْضِعِيهِ فَإِذَا خِفْتِ عَلَيْهِ فَأَلْقِيهِ فِى ٱلْيَمِّ وَلَا تَخَافِى وَلَا تَحْزَنِىٓ إِنَّا رَآدُّوهُ إِلَيْكِ وَجَاعِلُوهُ مِنَ ٱلْمُرْسَلِينَ
Amharic Translation - Africa Academy7. ወደ ሙሳም እናት “አጥቢው፤ በእርሱም ላይ በፈራሽ ጊዜ በባህሩ ውስጥ ጣይው፤ አትፍሪም:: አትዘኝም:: እኛ ወዳንቺ መላሾቹና ከመልእክተኞቹም አድራጊዎቹ ነንና” ማለትን አመለከትን (አወረድን)::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَٱلْتَقَطَهُۥٓ ءَالُ فِرْعَوْنَ لِيَكُونَ لَهُمْ عَدُوًّا وَحَزَنًا إِنَّ فِرْعَوْنَ وَهَٰمَٰنَ وَجُنُودَهُمَا كَانُوا۟ خَٰطِـِٔينَ
Amharic Translation - Africa Academy8. የፈርዖን ቤተሰቦችም መጨረሻው ለእነርሱ ጠላት ሐዘንም ይሆን ዘንድ አነሱት:: ፈርዖንና ሃማንም ሰራዊቶቻቸዉም ኃጢአተኞች ነበሩ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَقَالَتِ ٱمْرَأَتُ فِرْعَوْنَ قُرَّتُ عَيْنٍ لِّى وَلَكَ لَا تَقْتُلُوهُ عَسَىٰٓ أَن يَنفَعَنَآ أَوْ نَتَّخِذَهُۥ وَلَدًا وَهُمْ لَا يَشْعُرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy9. የፈርዖንም ሚስት “ለእኔም ሆነ ላንተ የዓይናችን መርጊያ ነው:: አትግደሉት:: ሊጠቅመን ወይም ልጅ ልናደርገው ይከጀላልና” አለች:: እነርሱም ፍጻሜውን የማያውቁ ሆነው (አነሱት)::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَأَصْبَحَ فُؤَادُ أُمِّ مُوسَىٰ فَٰرِغًا إِن كَادَتْ لَتُبْدِى بِهِۦ لَوْلَآ أَن رَّبَطْنَا عَلَىٰ قَلْبِهَا لِتَكُونَ مِنَ ٱلْمُؤْمِنِينَ
Amharic Translation - Africa Academy10. የሙሳም እናት ልብ ባዶ ሆነ:: ከምእምናን ትሆን ዘንድ በልቧ ላይ ባላጠነከርን ኖሮ ልትገልጸው ቀርባ ነበር::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَقَالَتْ لِأُخْتِهِۦ قُصِّيهِ فَبَصُرَتْ بِهِۦ عَن جُنُبٍ وَهُمْ لَا يَشْعُرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy11. ለእህቱም “ተከታተይው” አለቻት:: (እርሱንም) እነርሱ የማያውቁ ሲሆኑ በሩቅ ሆና አየችው፤
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَحَرَّمْنَا عَلَيْهِ ٱلْمَرَاضِعَ مِن قَبْلُ فَقَالَتْ هَلْ أَدُلُّكُمْ عَلَىٰٓ أَهْلِ بَيْتٍ يَكْفُلُونَهُۥ لَكُمْ وَهُمْ لَهُۥ نَٰصِحُونَ
Amharic Translation - Africa Academy12. ወደ እናቱ ከመመለሱ በፊትም አጥቢዎችን መጥባትን በእርሱ ላይ እርም አደረግን:: እህቱም “ለእናንተ የሚያሳድግላችሁን እነርሱም ለእርሱ ቅን አገልጋዮች የሆኑን ቤተሰቦች ላመልክታችሁን?” አለችም።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَرَدَدْنَٰهُ إِلَىٰٓ أُمِّهِۦ كَىْ تَقَرَّ عَيْنُهَا وَلَا تَحْزَنَ وَلِتَعْلَمَ أَنَّ وَعْدَ ٱللَّهِ حَقٌّ وَلَٰكِنَّ أَكْثَرَهُمْ لَا يَعْلَمُونَ
Amharic Translation - Africa Academy13. ወደ እናቱም ዓይኗ እንድትረጋ እንዳታዝንም የአላህም የተስፋ ቃል እርግጥ መሆኑን እንድታውቅ መለስነው:: ግን አብዛኞቻቸው አያውቁም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلَمَّا بَلَغَ أَشُدَّهُۥ وَٱسْتَوَىٰٓ ءَاتَيْنَٰهُ حُكْمًا وَعِلْمًا وَكَذَٰلِكَ نَجْزِى ٱلْمُحْسِنِينَ
Amharic Translation - Africa Academy14. ብርታቱንም በደረሰና በተስተካከለ ጊዜ ጥበብንና እውቀትን ሰጠነው፤ ልክ እንደዚሁም መልካም ሰሪዎችን እንመነዳለን::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَدَخَلَ ٱلْمَدِينَةَ عَلَىٰ حِينِ غَفْلَةٍ مِّنْ أَهْلِهَا فَوَجَدَ فِيهَا رَجُلَيْنِ يَقْتَتِلَانِ هَٰذَا مِن شِيعَتِهِۦ وَهَٰذَا مِنْ عَدُوِّهِۦ فَٱسْتَغَٰثَهُ ٱلَّذِى مِن شِيعَتِهِۦ عَلَى ٱلَّذِى مِنْ عَدُوِّهِۦ فَوَكَزَهُۥ مُوسَىٰ فَقَضَىٰ عَلَيْهِ قَالَ هَٰذَا مِنْ عَمَلِ ٱلشَّيْطَٰنِ إِنَّهُۥ عَدُوٌّ مُّضِلٌّ مُّبِينٌ
Amharic Translation - Africa Academy15. ሙሳ ከተማይቱንም ሰዎቿ በዝንጋቴ ላይ ሆነው ሳሉ ገባ:: በእርሷም ውስጥ የሚጋደሉን ሁለት ሰዎች አገኘ:: ይህ (አንዱ) ከወገኑ ነው፤ ይህ (ሌላው) ደግሞ ከጠላቱ ነው፤ ያ ከወገኑ የሆነው ሰው በዚያ ከጣላት በሆነው ሰው ላይ እርዳታን ጠየቀው:: ሙሳም በጡጫ መታው:: ገደለዉም:: “ይህ ከሰይጣን ስራ ነው:: እርሱ ግልጽ አሣሣች ጠላት ነውና” አለ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالَ رَبِّ إِنِّى ظَلَمْتُ نَفْسِى فَٱغْفِرْ لِى فَغَفَرَ لَهُۥٓ إِنَّهُۥ هُوَ ٱلْغَفُورُ ٱلرَّحِيمُ
Amharic Translation - Africa Academy16. “ጌታዬ ሆይ! እኔ ነፍሴን በደልኩ ለኔም ማር” አለ ለርሱም ምህረት አደረገለት:: እርሱ መሓሪና አዛኝ ነውና::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالَ رَبِّ بِمَآ أَنْعَمْتَ عَلَىَّ فَلَنْ أَكُونَ ظَهِيرًا لِّلْمُجْرِمِينَ
Amharic Translation - Africa Academy17. “ጌታዬ ሆይ! በእኔ ላይ በመለገስህ ይሁንብኝ (ከስህተቴ እጸጸታለሁ):: ለአመጸኞችም ፈጽሞ ረዳት አልሆንም” አለ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَأَصْبَحَ فِى ٱلْمَدِينَةِ خَآئِفًا يَتَرَقَّبُ فَإِذَا ٱلَّذِى ٱسْتَنصَرَهُۥ بِٱلْأَمْسِ يَسْتَصْرِخُهُۥ قَالَ لَهُۥ مُوسَىٰٓ إِنَّكَ لَغَوِىٌّ مُّبِينٌ
Amharic Translation - Africa Academy18. በከተማይቱም ውስጥ ፈሪና የሚጠባበቅ ሆኖ አደረ:: በንጋቱም ያ ትላንት እርዳታን የጠየቀው ሰው በጩኸት እርዳታን ይጠይቀዋል:: ሙሳም ለእርሱ፡- “አንተ በእርግጥ ግልጽ ጠማማ ነህ” አለው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَلَمَّآ أَنْ أَرَادَ أَن يَبْطِشَ بِٱلَّذِى هُوَ عَدُوٌّ لَّهُمَا قَالَ يَٰمُوسَىٰٓ أَتُرِيدُ أَن تَقْتُلَنِى كَمَا قَتَلْتَ نَفْسًۢا بِٱلْأَمْسِ إِن تُرِيدُ إِلَّآ أَن تَكُونَ جَبَّارًا فِى ٱلْأَرْضِ وَمَا تُرِيدُ أَن تَكُونَ مِنَ ٱلْمُصْلِحِينَ
Amharic Translation - Africa Academy19. ሙሳ ያንን እርሱ ለሁለቱም ጠላት የሆነው ሰው በኃይል ሊይዘው በፈለገም ጊዜ “ሙሳ ሆይ በትላንትናው ቀን ነፍስን እንደ ገደልክ ልትገድለኝ ትፈልጋለህን? በምድር ላይ ጨካኝ መሆንን እንጂ ሌላ አትፈልግም ከመልካም ሰሪዎች መሆንን አትፈልግም” አለው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَجَآءَ رَجُلٌ مِّنْ أَقْصَا ٱلْمَدِينَةِ يَسْعَىٰ قَالَ يَٰمُوسَىٰٓ إِنَّ ٱلْمَلَأَ يَأْتَمِرُونَ بِكَ لِيَقْتُلُوكَ فَٱخْرُجْ إِنِّى لَكَ مِنَ ٱلنَّٰصِحِينَ
Amharic Translation - Africa Academy20. ከከተማይቱም ዳርቻ አንድ ሰው እየሮጠ መጣ “ሙሳ ሆይ! ሹማምንቶቹ ሊገድሉህ ባንተ ይመካከራሉና ውጣ እኔ ላንተ ከመካሪዎች ነኝና” አለው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَخَرَجَ مِنْهَا خَآئِفًا يَتَرَقَّبُ قَالَ رَبِّ نَجِّنِى مِنَ ٱلْقَوْمِ ٱلظَّٰلِمِينَ
Amharic Translation - Africa Academy21. የፈራና የሚጠባበቅ ሆኖም ከእርሷ ወጣ:: “ጌታዬ ሆይ! ከበደለኞች ህዝቦች አድነኝ” አለ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلَمَّا تَوَجَّهَ تِلْقَآءَ مَدْيَنَ قَالَ عَسَىٰ رَبِّىٓ أَن يَهْدِيَنِى سَوَآءَ ٱلسَّبِيلِ
Amharic Translation - Africa Academy22. ወደ መድየን አቅጣጫ ፊቱን ባዞረ ጊዜም “ጌታዬ ቀጥተኛውን መንገድ ሊመራኝ እከጅላለሁ” አለ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلَمَّا وَرَدَ مَآءَ مَدْيَنَ وَجَدَ عَلَيْهِ أُمَّةً مِّنَ ٱلنَّاسِ يَسْقُونَ وَوَجَدَ مِن دُونِهِمُ ٱمْرَأَتَيْنِ تَذُودَانِ قَالَ مَا خَطْبُكُمَا قَالَتَا لَا نَسْقِى حَتَّىٰ يُصْدِرَ ٱلرِّعَآءُ وَأَبُونَا شَيْخٌ كَبِيرٌ
Amharic Translation - Africa Academy23. ወደ መድየንም ውሃ በመጣ ጊዜ እርሱ ላይ ከሰዎች ቡድኖችን መንጋዎቻቸውን የሚያጠጡ ሆነው አገኘ:: ከእነርሱ በታችም ከውሃው መንጎቻቸውን የሚከለክሉ ሁለት ሴቶች ልጆችን አገኘ። “ነገራችሁ ምንድን ነው?” አላቸው። “እረኞች ሁሉ መንጋዎቻቸውን እስከሚመልሱ አናጠጣም። አባታችንም ትልቅ ሽማግሌ ነው።” አሉት::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَسَقَىٰ لَهُمَا ثُمَّ تَوَلَّىٰٓ إِلَى ٱلظِّلِّ فَقَالَ رَبِّ إِنِّى لِمَآ أَنزَلْتَ إِلَىَّ مِنْ خَيْرٍ فَقِيرٌ
Amharic Translation - Africa Academy24. ለሁለቱም አጠጣላቸው ከዚያ ወደ ጥላው ዘወር አለና “ጌታዬ ሆይ! እኔ ከመልካም ነገር ወደ እኔ ለምታወርደው ፈላጊ ነኝ” አለ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَجَآءَتْهُ إِحْدَىٰهُمَا تَمْشِى عَلَى ٱسْتِحْيَآءٍ قَالَتْ إِنَّ أَبِى يَدْعُوكَ لِيَجْزِيَكَ أَجْرَ مَا سَقَيْتَ لَنَا فَلَمَّا جَآءَهُۥ وَقَصَّ عَلَيْهِ ٱلْقَصَصَ قَالَ لَا تَخَفْ نَجَوْتَ مِنَ ٱلْقَوْمِ ٱلظَّٰلِمِينَ
Amharic Translation - Africa Academy25. ከሁለቱ አንደኛይቱም ከሀፍረት ጋር የምትሄድ ሆና ወደ እርሱ መጣች፤ “አባቴ ለእኛ ያጠጣህልንን ዋጋ ሊሰጥህ ይጠራሃል” አለችው፤ ወደ እርሱ በመጣና ወሬውን በእርሱ ላይ በተረከለትም ጊዜ “አትፍራ:: ከበደለኞች ህዝቦች ድነሃል” አለው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالَتْ إِحْدَىٰهُمَا يَٰٓأَبَتِ ٱسْتَـْٔجِرْهُ إِنَّ خَيْرَ مَنِ ٱسْتَـْٔجَرْتَ ٱلْقَوِىُّ ٱلْأَمِينُ
Amharic Translation - Africa Academy26. ከሁለቱ አንደኛይቱም “አባቴ ሆይ ቅጠረው ከቀጠርከው ሰው ሁሉ በላጩ፤ ብርቱው፤ ታማኙ ነውና” አለችው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالَ إِنِّىٓ أُرِيدُ أَنْ أُنكِحَكَ إِحْدَى ٱبْنَتَىَّ هَٰتَيْنِ عَلَىٰٓ أَن تَأْجُرَنِى ثَمَٰنِىَ حِجَجٍ فَإِنْ أَتْمَمْتَ عَشْرًا فَمِنْ عِندِكَ وَمَآ أُرِيدُ أَنْ أَشُقَّ عَلَيْكَ سَتَجِدُنِىٓ إِن شَآءَ ٱللَّهُ مِنَ ٱلصَّٰلِحِينَ
Amharic Translation - Africa Academy27. “ስምንትን ዓመታት ልታገለግለኝ እኔ ከእነዚህ ሁለት ሴቶች ልጆቼ አንዲቷን ላጋባህ እሻለሁ፤ ዐስርን ብትሞላም ካንተ ነው:: ባንተ ላይ ማስቸገርንም አልሻም:: አላህ የሻ እንደሆነ ከመልካም ሰዎች ሆኜ ታገኘኛለህ” አለው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالَ ذَٰلِكَ بَيْنِى وَبَيْنَكَ أَيَّمَا ٱلْأَجَلَيْنِ قَضَيْتُ فَلَا عُدْوَٰنَ عَلَىَّ وَٱللَّهُ عَلَىٰ مَا نَقُولُ وَكِيلٌ
Amharic Translation - Africa Academy28. ሙሳም "ይህ ውለታ በእኔና ባንተ መካከል ረጊ ነው:: ከሁለት ጊዜያቶች ማንኛውንም ብፈጽም በእኔ ላይ ወሰን ማለፍ የለም:: አላህ በምንለው ላይ ሁሉ ምስክር ነው" አለ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَلَمَّا قَضَىٰ مُوسَى ٱلْأَجَلَ وَسَارَ بِأَهْلِهِۦٓ ءَانَسَ مِن جَانِبِ ٱلطُّورِ نَارًا قَالَ لِأَهْلِهِ ٱمْكُثُوٓا۟ إِنِّىٓ ءَانَسْتُ نَارًا لَّعَلِّىٓ ءَاتِيكُم مِّنْهَا بِخَبَرٍ أَوْ جَذْوَةٍ مِّنَ ٱلنَّارِ لَعَلَّكُمْ تَصْطَلُونَ
Amharic Translation - Africa Academy29. ሙሳም ጊዜውን በጨረሰና ከቤተሰቦቹ ጋር በሄደ ጊዜ ከጡር ተራራ ጎን እሳትን አየ:: ለቤተሰቡም “እዚህ ቆዩ:: እኔ እሳትን አየሁ:: ከእርሷ አጠገብ ወሬ ወይም ትሞቁ ዘንድ ከእሳት ትንታግን (ችቦን) አመጣላችኋለሁ” አለ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَلَمَّآ أَتَىٰهَا نُودِىَ مِن شَٰطِئِ ٱلْوَادِ ٱلْأَيْمَنِ فِى ٱلْبُقْعَةِ ٱلْمُبَٰرَكَةِ مِنَ ٱلشَّجَرَةِ أَن يَٰمُوسَىٰٓ إِنِّىٓ أَنَا ٱللَّهُ رَبُّ ٱلْعَٰلَمِينَ
Amharic Translation - Africa Academy30. ወደ እርሷ በመጣም ጊዜ ከሸለቆው ቀኝ ዳርቻ ከዛፊቱ በኩል በተባረከችው ስፍራ ውስጥ “ሙሳ ሆይ! እኔ የዓለማት ጌታ አላህ ነኝ” በማለት ተጠራ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَأَنْ أَلْقِ عَصَاكَ فَلَمَّا رَءَاهَا تَهْتَزُّ كَأَنَّهَا جَآنٌّ وَلَّىٰ مُدْبِرًا وَلَمْ يُعَقِّبْ يَٰمُوسَىٰٓ أَقْبِلْ وَلَا تَخَفْ إِنَّكَ مِنَ ٱلْـَٔامِنِينَ
Amharic Translation - Africa Academy31. “ብትርህንም ጣል” ተባለ:: እንደ ትንሽ እባብ ስትስለከለክ ባያትም ጊዜ ወደ ኋላ ዞሮ ሸሸ:: አልተመለሰምም፤ ተባለም: “ሙሳ ሆይ! ተመለስ አትፍራም፤ አንተ ከጥብቆቹ ነህና
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ٱسْلُكْ يَدَكَ فِى جَيْبِكَ تَخْرُجْ بَيْضَآءَ مِنْ غَيْرِ سُوٓءٍ وَٱضْمُمْ إِلَيْكَ جَنَاحَكَ مِنَ ٱلرَّهْبِ فَذَٰنِكَ بُرْهَٰنَانِ مِن رَّبِّكَ إِلَىٰ فِرْعَوْنَ وَمَلَإِي۟هِۦٓ إِنَّهُمْ كَانُوا۟ قَوْمًا فَٰسِقِينَ
Amharic Translation - Africa Academy32. "እጅህን በአንገትጌህ ውስጥ አስግባ:: ያለ ነውር ነጭ ሆና ትወጣለችና፤ ክንፍህንም ከፍርሃት ለመዳን ወደ አንተ አጣብቅ:: እነዚህም ከጌታህ የሆኑ ወደ ፈርዖንና ወደ መኳንቶች የሚደርሱ ሁለት አስረጅዎች ናቸው:: እነርሱ አመጠኞች ህዝቦች ነበሩና።“
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالَ رَبِّ إِنِّى قَتَلْتُ مِنْهُمْ نَفْسًا فَأَخَافُ أَن يَقْتُلُونِ
Amharic Translation - Africa Academy33. ሙሳ አለ: "ጌታዬ ሆይ! እኔ ከእነርሱ ነፍስን ገድያለሁ ስለዚህ እንዳይገሉኝ እፈራለሁ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَأَخِى هَٰرُونُ هُوَ أَفْصَحُ مِنِّى لِسَانًا فَأَرْسِلْهُ مَعِىَ رِدْءًا يُصَدِّقُنِىٓ إِنِّىٓ أَخَافُ أَن يُكَذِّبُونِ
Amharic Translation - Africa Academy34. "ወንድሜንም ሃሩን እርሱ ምላሱ ከእኔ የተባ (የተሻለ) ነው:: እውነተኛነቴንም የሚያረጋግጥልኝ ረዳት ሆኖ ከእኔ ጋር ላከው እኔ ሊያስተባብሉኝ እፈራለሁና።”
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالَ سَنَشُدُّ عَضُدَكَ بِأَخِيكَ وَنَجْعَلُ لَكُمَا سُلْطَٰنًا فَلَا يَصِلُونَ إِلَيْكُمَا بِـَٔايَٰتِنَآ أَنتُمَا وَمَنِ ٱتَّبَعَكُمَا ٱلْغَٰلِبُونَ
Amharic Translation - Africa Academy35. (አላህም)፡- “ጡንቻህን በወንድምህ በእርግጥ እናበረታለን:: ለሁለታችሁም ስልጣንን እናደርጋለን:: ወደ እናንተም በመጥፎ አይደርሱም:: በታዓምራታችን ሂዱ:: እናንተና የተከተላችሁ ሁሉ አሸናፊዎች ናችሁ” አላቸው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَلَمَّا جَآءَهُم مُّوسَىٰ بِـَٔايَٰتِنَا بَيِّنَٰتٍ قَالُوا۟ مَا هَٰذَآ إِلَّا سِحْرٌ مُّفْتَرًى وَمَا سَمِعْنَا بِهَٰذَا فِىٓ ءَابَآئِنَا ٱلْأَوَّلِينَ
Amharic Translation - Africa Academy36. ሙሳም ተዓምራቶቻችንም ግልጽ ሆነው በመጣባቸው ጊዜ “ይህ የተቀጠፈ ድግምት እንጅ ሌላ አይደለም:: ይህንንም በመጀመሪያዎች አባቶቻችን ውስጥ አልሰማንም” አሉ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَقَالَ مُوسَىٰ رَبِّىٓ أَعْلَمُ بِمَن جَآءَ بِٱلْهُدَىٰ مِنْ عِندِهِۦ وَمَن تَكُونُ لَهُۥ عَٰقِبَةُ ٱلدَّارِ إِنَّهُۥ لَا يُفْلِحُ ٱلظَّٰلِمُونَ
Amharic Translation - Africa Academy37. ሙሳም “ጌታዬ ከእርሱ ዘንድ በቀጥታው መንገድ የመጣውን ምስጉኒትም አገር ለእርሱ የምትሆንለትን ሰው አዋቂ ነው:: እነሆ በደለኞች አይድኑም” አለ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَقَالَ فِرْعَوْنُ يَٰٓأَيُّهَا ٱلْمَلَأُ مَا عَلِمْتُ لَكُم مِّنْ إِلَٰهٍ غَيْرِى فَأَوْقِدْ لِى يَٰهَٰمَٰنُ عَلَى ٱلطِّينِ فَٱجْعَل لِّى صَرْحًا لَّعَلِّىٓ أَطَّلِعُ إِلَىٰٓ إِلَٰهِ مُوسَىٰ وَإِنِّى لَأَظُنُّهُۥ مِنَ ٱلْكَٰذِبِينَ
Amharic Translation - Africa Academy38. ፈርዖንም “እናንተ ቡድኖች ሆይ! ከእኔ ሌላ ለእናንተ አምላክን ምንም አላውቅም:: ሃማን ሆይ! ጭቃ ለእኔ አቃጥልልኝ:: ጡብ ስራልኝ:: ለእኔም ከፍተኛ ህንጻን ስራልኝ:: ወደ ሙሳ አምላክ ልወጣ እከጅላለሁና:: እኔም ከውሸታሞች መሆኑን እጠረጥረዋለሁ” አለ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَٱسْتَكْبَرَ هُوَ وَجُنُودُهُۥ فِى ٱلْأَرْضِ بِغَيْرِ ٱلْحَقِّ وَظَنُّوٓا۟ أَنَّهُمْ إِلَيْنَا لَا يُرْجَعُونَ
Amharic Translation - Africa Academy39. እርሱም ሰራዊቶቹም በምድር ላይ ያለ አግባብ ኮሩ:: እነርሱም ወደእኛ የማይመለሱ መሆናቸውን ጠረጠሩ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَأَخَذْنَٰهُ وَجُنُودَهُۥ فَنَبَذْنَٰهُمْ فِى ٱلْيَمِّ فَٱنظُرْ كَيْفَ كَانَ عَٰقِبَةُ ٱلظَّٰلِمِينَ
Amharic Translation - Africa Academy40. እርሱንም ሰራዊቱንም በጥብቅ ያዝናቸው:: በባህርም ውስጥ ጣልናቸው:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የበደለኞች መጨረሻም እንዴት እንደነበረ ተመልከት::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَجَعَلْنَٰهُمْ أَئِمَّةً يَدْعُونَ إِلَى ٱلنَّارِ وَيَوْمَ ٱلْقِيَٰمَةِ لَا يُنصَرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy41. ወደ እሳት የሚጠሩ መሪዎችም አደረግናቸው:: በትንሳኤም ቀን አይረዱም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَأَتْبَعْنَٰهُمْ فِى هَٰذِهِ ٱلدُّنْيَا لَعْنَةً وَيَوْمَ ٱلْقِيَٰمَةِ هُم مِّنَ ٱلْمَقْبُوحِينَ
Amharic Translation - Africa Academy42. በዚችም በቅርቢቱ ዓለም ውስጥ እርግማንን አስከተልናቸው:: በትንሳኤም ቀን እነርሱ ከሚባረሩት ናቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلَقَدْ ءَاتَيْنَا مُوسَى ٱلْكِتَٰبَ مِنۢ بَعْدِ مَآ أَهْلَكْنَا ٱلْقُرُونَ ٱلْأُولَىٰ بَصَآئِرَ لِلنَّاسِ وَهُدًى وَرَحْمَةً لَّعَلَّهُمْ يَتَذَكَّرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy43. የፊተኞቹን የክፍለ ዘመናት ህዝቦችንም ከአጠፋን በኋላ ለሰዎች የልብ ብርሃን መሪም እዝነትም ሲሆን ይገሠጹ ዘንድ ለሙሳ መጽሐፉን በእርግጥ ሰጠነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَمَا كُنتَ بِجَانِبِ ٱلْغَرْبِىِّ إِذْ قَضَيْنَآ إِلَىٰ مُوسَى ٱلْأَمْرَ وَمَا كُنتَ مِنَ ٱلشَّٰهِدِينَ
Amharic Translation - Africa Academy44. ወደ ሙሳም ትዕዛዝን ባወረድንለት ጊዜ ከተራራው በምዕራባዊው ጎን አልነበርክም:: ከተጣዱትም አልነበርክም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلَٰكِنَّآ أَنشَأْنَا قُرُونًا فَتَطَاوَلَ عَلَيْهِمُ ٱلْعُمُرُ وَمَا كُنتَ ثَاوِيًا فِىٓ أَهْلِ مَدْيَنَ تَتْلُوا۟ عَلَيْهِمْ ءَايَٰتِنَا وَلَٰكِنَّا كُنَّا مُرْسِلِينَ
Amharic Translation - Africa Academy45. እኛ ግን ከእርሱ ኋላ አያሌ የክፍለ ዘመናትን ሰዎች አስገኘን:: በእነርሱም ላይ ዕድሜዎች ተራዘሙ:: በመድየንም ሰዎች ውስጥ ተቀማጭና በእነርሱ ላይ አናቅጻችንን የምታነብ አልነበርክም:: እኛ ግን ላኪዎችህ ሆንን::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَمَا كُنتَ بِجَانِبِ ٱلطُّورِ إِذْ نَادَيْنَا وَلَٰكِن رَّحْمَةً مِّن رَّبِّكَ لِتُنذِرَ قَوْمًا مَّآ أَتَىٰهُم مِّن نَّذِيرٍ مِّن قَبْلِكَ لَعَلَّهُمْ يَتَذَكَّرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy46. በጠራነዉም ጊዜ በጡሩ (ጋራ) ጎን አልነበርክም፤ ግን ካንተ በፊት ምንም አስፈራሪ ያልመጣባቸውን ህዝቦች ታስፈራራ ዘንድ ከጌታህ በሆነ ችሮታ ላክንህ ሊገሠጹ ይከጅላልና።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلَوْلَآ أَن تُصِيبَهُم مُّصِيبَةٌۢ بِمَا قَدَّمَتْ أَيْدِيهِمْ فَيَقُولُوا۟ رَبَّنَا لَوْلَآ أَرْسَلْتَ إِلَيْنَا رَسُولًا فَنَتَّبِعَ ءَايَٰتِكَ وَنَكُونَ مِنَ ٱلْمُؤْمِنِينَ
Amharic Translation - Africa Academy47. እጆቻቸዉም ባሳለፉት ምክንያት መከራ የምትነካቸውና “ጌታችን ሆይ! አናቅጽህን እንድንከተል ከትክክለኛ አማኞችም እንድንሆን ወደ እኛ መልዕክተኛን አትልክም ኖሯልን? ይህ ሁሉ የሚሉ ባልሆኑ ኖሮ” አንልክም ነበር።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَلَمَّا جَآءَهُمُ ٱلْحَقُّ مِنْ عِندِنَا قَالُوا۟ لَوْلَآ أُوتِىَ مِثْلَ مَآ أُوتِىَ مُوسَىٰٓ أَوَلَمْ يَكْفُرُوا۟ بِمَآ أُوتِىَ مُوسَىٰ مِن قَبْلُ قَالُوا۟ سِحْرَانِ تَظَٰهَرَا وَقَالُوٓا۟ إِنَّا بِكُلٍّ كَٰفِرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy48. እውነቱም ከኛ ዘንድ በመጣላቸው ጊዜ “ለሙሳ የተሰጠው ብጤ አይሰጠዉም ኖሯልን?” አሉ፤ ከዚህ በፊት ሙሳ በተሰጠው አልካዱምን? “ሁለት የተረዳዱ ድግምቶች ናቸው። እኛ በሁሉም ከሓዲያን ነን” አሉ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قُلْ فَأْتُوا۟ بِكِتَٰبٍ مِّنْ عِندِ ٱللَّهِ هُوَ أَهْدَىٰ مِنْهُمَآ أَتَّبِعْهُ إِن كُنتُمْ صَٰدِقِينَ
Amharic Translation - Africa Academy49. “ከአላህ ዘንድ የሆነን መጽሐፍ እርሱ ከሁለቱም ይበልጥ ቅን የሆነን አምጡ፤ እውነተኞች እንደ ሆናችሁ ብታመጡት እከተለዋለሁ” በላቸው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَإِن لَّمْ يَسْتَجِيبُوا۟ لَكَ فَٱعْلَمْ أَنَّمَا يَتَّبِعُونَ أَهْوَآءَهُمْ وَمَنْ أَضَلُّ مِمَّنِ ٱتَّبَعَ هَوَىٰهُ بِغَيْرِ هُدًى مِّنَ ٱللَّهِ إِنَّ ٱللَّهَ لَا يَهْدِى ٱلْقَوْمَ ٱلظَّٰلِمِينَ
Amharic Translation - Africa Academy50. እሺ ባይሉህም የሚከተሉት ዝንባሌዎቻቸውን ብቻ መሆኑን ዕወቅ፤ ከአላህም የሆነ መምሪያ ሳይኖረው ዝንባሌውን ብቻ ከተከተለ ይበልጥ የጠመመ አንድም የለም፤ አላህ በደለኞች ህዝቦችን አይመራምና::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلَقَدْ وَصَّلْنَا لَهُمُ ٱلْقَوْلَ لَعَلَّهُمْ يَتَذَكَّرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy51. ይገሠጹም ዘንድ ቃልን (ቁርኣንን በያይነቱ) ለእነርሱ በእርግጥ አስከታተልን::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ٱلَّذِينَ ءَاتَيْنَٰهُمُ ٱلْكِتَٰبَ مِن قَبْلِهِۦ هُم بِهِۦ يُؤْمِنُونَ
Amharic Translation - Africa Academy52. እነዚያም ከእርሱ በፊት መጽሐፍን የሰጠናቸው እነርሱ በእርሱ ያምናሉ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَإِذَا يُتْلَىٰ عَلَيْهِمْ قَالُوٓا۟ ءَامَنَّا بِهِۦٓ إِنَّهُ ٱلْحَقُّ مِن رَّبِّنَآ إِنَّا كُنَّا مِن قَبْلِهِۦ مُسْلِمِينَ
Amharic Translation - Africa Academy53. በእነርሱ ላይ በሚነበብላቸዉም ጊዜ «በእርሱ አምነናል:: እርሱ ከጌታችን የሆነ እውነት ነው እኛ ከእርሱ በፊት ሙስሊሞች ነበርን።» ይላሉ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أُو۟لَٰٓئِكَ يُؤْتَوْنَ أَجْرَهُم مَّرَّتَيْنِ بِمَا صَبَرُوا۟ وَيَدْرَءُونَ بِٱلْحَسَنَةِ ٱلسَّيِّئَةَ وَمِمَّا رَزَقْنَٰهُمْ يُنفِقُونَ
Amharic Translation - Africa Academy54. እነዚያ በመታገሳቸው ምክኒያት ዋጋቸውን ሁለት ጊዜ ይሰጣሉ:: ክፉውንም ነገር በበጎ ምግባር ይገፈትራሉ፤ ከሰጠናቸዉም ሲሳይ ይለግሳሉ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَإِذَا سَمِعُوا۟ ٱللَّغْوَ أَعْرَضُوا۟ عَنْهُ وَقَالُوا۟ لَنَآ أَعْمَٰلُنَا وَلَكُمْ أَعْمَٰلُكُمْ سَلَٰمٌ عَلَيْكُمْ لَا نَبْتَغِى ٱلْجَٰهِلِينَ
Amharic Translation - Africa Academy55. ውድቅንም ቃል በሰሙ ጊዜ ከእርሱ ይርቃሉ። «ለእኛ ስራዎቻችን አሉን:: ለእናንተም ስራዎቻችሁ አሉላችሁ:: ሰላም በእናንተ ላይ ይሁን ባለጌዎችን አንፈልግም።» ይላሉ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِنَّكَ لَا تَهْدِى مَنْ أَحْبَبْتَ وَلَٰكِنَّ ٱللَّهَ يَهْدِى مَن يَشَآءُ وَهُوَ أَعْلَمُ بِٱلْمُهْتَدِينَ
Amharic Translation - Africa Academy56. አንተ የወደድከውን ሰው ፈጽሞ አታቀናም:: ግን አላህ የሚሻውን ሰው ያቀናል:: እርሱም ቅኖቹን አዋቂ ነው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَقَالُوٓا۟ إِن نَّتَّبِعِ ٱلْهُدَىٰ مَعَكَ نُتَخَطَّفْ مِنْ أَرْضِنَآ أَوَلَمْ نُمَكِّن لَّهُمْ حَرَمًا ءَامِنًا يُجْبَىٰٓ إِلَيْهِ ثَمَرَٰتُ كُلِّ شَىْءٍ رِّزْقًا مِّن لَّدُنَّا وَلَٰكِنَّ أَكْثَرَهُمْ لَا يَعْلَمُونَ
Amharic Translation - Africa Academy57. «ካንተ ጋር ቅንን መንገድ ብንከተል ከምድራችን እንባረራለን።» አሉም:: ከእኛ ዘንድ የተሰጠ ሲሳይ ሲሆን የነገሩ ሁሉ ፍሬዎች ወደ እርሱ የሚሄዱበትን ጸጥተኛ ክልል (መካን) እነርሱ አላስመቸናቸዉምን? ግን አብዛኞቻቸው አያውቁም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَكَمْ أَهْلَكْنَا مِن قَرْيَةٍۭ بَطِرَتْ مَعِيشَتَهَا فَتِلْكَ مَسَٰكِنُهُمْ لَمْ تُسْكَن مِّنۢ بَعْدِهِمْ إِلَّا قَلِيلًا وَكُنَّا نَحْنُ ٱلْوَٰرِثِينَ
Amharic Translation - Africa Academy58. ከከተማም ኑሮዋን ምቾትዋን የካደችን ከተማ ያጠፋናት ብዙ ናት፤ እነዚህም ከእነርሱ በኋላ ጥቂት ጊዜ እንጂ ያልተኖረባቸው ሲሆኑ መኖሪያዎቻቸው ናቸው:: እኛም ከእነርሱ ወራሾች ነበርን።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَمَا كَانَ رَبُّكَ مُهْلِكَ ٱلْقُرَىٰ حَتَّىٰ يَبْعَثَ فِىٓ أُمِّهَا رَسُولًا يَتْلُوا۟ عَلَيْهِمْ ءَايَٰتِنَا وَمَا كُنَّا مُهْلِكِى ٱلْقُرَىٰٓ إِلَّا وَأَهْلُهَا ظَٰلِمُونَ
Amharic Translation - Africa Academy59. ጌታህም ከተሞችን በዋናዋ ከተማ ውስጥ አናቅጻችንን በእነርሱ ላይ የሚያነብ መልዕክተኛን እስከሚልክ ድረስ አጥፊ አልነበረም:: ከተሞችንም ባለቤቶችዋ በዳዮች ሆነው እንጂ አጥፊዎች አልነበርንም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَمَآ أُوتِيتُم مِّن شَىْءٍ فَمَتَٰعُ ٱلْحَيَوٰةِ ٱلدُّنْيَا وَزِينَتُهَا وَمَا عِندَ ٱللَّهِ خَيْرٌ وَأَبْقَىٰٓ أَفَلَا تَعْقِلُونَ
Amharic Translation - Africa Academy60. ሰዎች ሆይ! በማንኛዉም ነገር የተሰጣችሁት የቅርቢቱ ሂይወት ጥቅምና ጌጣ ጌጥ ነው:: አላህ ዘንድ ያለዉም ምንዳ በጣም በላጭና ዘውታሪ ነው:: አታውቁምን?
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَفَمَن وَعَدْنَٰهُ وَعْدًا حَسَنًا فَهُوَ لَٰقِيهِ كَمَن مَّتَّعْنَٰهُ مَتَٰعَ ٱلْحَيَوٰةِ ٱلدُّنْيَا ثُمَّ هُوَ يَوْمَ ٱلْقِيَٰمَةِ مِنَ ٱلْمُحْضَرِينَ
Amharic Translation - Africa Academy61. መልካምን ተስፋ ቃል የገባንለትና እርሱም አግኚው የሆነ ሰው የቅርቢቱን ህይወት ጥቅም እንዳስመቸነውና ከዚያ እርሱ በትንሳኤ ቀን ለእሳት ከሚቀረቡት እንደ ሆነው ሰው ነውን?
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَيَوْمَ يُنَادِيهِمْ فَيَقُولُ أَيْنَ شُرَكَآءِىَ ٱلَّذِينَ كُنتُمْ تَزْعُمُونَ
Amharic Translation - Africa Academy62. (አላህ) የሚጠራባቸውንና «እነዚያ ተጋሪዎቼ ትሏቸው የነበራችሁት የት ናቸው?» የሚልበትን ቀን (አስታውስ)::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالَ ٱلَّذِينَ حَقَّ عَلَيْهِمُ ٱلْقَوْلُ رَبَّنَا هَٰٓؤُلَآءِ ٱلَّذِينَ أَغْوَيْنَآ أَغْوَيْنَٰهُمْ كَمَا غَوَيْنَا تَبَرَّأْنَآ إِلَيْكَ مَا كَانُوٓا۟ إِيَّانَا يَعْبُدُونَ
Amharic Translation - Africa Academy63. እነዚያ በእነርሱ ላይ ቅጣቱ የተረጋገጠባቸው ይላሉ «ጌታችን ሆይ እነዚህ እነዚያ ያጠመምናቸው ናቸው፤ እንደጠመምን አጠመምናቸው (ከእነርሱ) ወደ አንተ ተጥራራን:: እኛን ይገዙ አልነበሩም።»
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَقِيلَ ٱدْعُوا۟ شُرَكَآءَكُمْ فَدَعَوْهُمْ فَلَمْ يَسْتَجِيبُوا۟ لَهُمْ وَرَأَوُا۟ ٱلْعَذَابَ لَوْ أَنَّهُمْ كَانُوا۟ يَهْتَدُونَ
Amharic Translation - Africa Academy64. «ለአላህ የምታጋሯቸውንም ጥሩ» ይባላሉ:: ይጠሩዋቸዋልም ግን ለእነርሱ አይመልሱላቸዉም:: ቅጣትንም ያያሉ፤ እነርሱ ይመሩ በነበሩ ኖሮ (አያዩትም ነበር)::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَيَوْمَ يُنَادِيهِمْ فَيَقُولُ مَاذَآ أَجَبْتُمُ ٱلْمُرْسَلِينَ
Amharic Translation - Africa Academy65. የሚጠራባቸውንና «ለመልዕክተኞች ምንን መለሳችሁ?» የሚልበትን ቀን አስታውስ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَعَمِيَتْ عَلَيْهِمُ ٱلْأَنۢبَآءُ يَوْمَئِذٍ فَهُمْ لَا يَتَسَآءَلُونَ
Amharic Translation - Africa Academy66. በዚያም ቀን ወሬዎች ሁሉ በእነርሱ ላይ ይሰወሩባቸዋል፤ እነርሱም አይጠያየቁም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَأَمَّا مَن تَابَ وَءَامَنَ وَعَمِلَ صَٰلِحًا فَعَسَىٰٓ أَن يَكُونَ مِنَ ٱلْمُفْلِحِينَ
Amharic Translation - Africa Academy67. የተጸጸተና ያመነማ መልካምንም የሰራ ከሚድኑት ሊሆን ይከጀላል::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَرَبُّكَ يَخْلُقُ مَا يَشَآءُ وَيَخْتَارُ مَا كَانَ لَهُمُ ٱلْخِيَرَةُ سُبْحَٰنَ ٱللَّهِ وَتَعَٰلَىٰ عَمَّا يُشْرِكُونَ
Amharic Translation - Africa Academy68. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጌታህም የሚፈልገውን ይፈጥራል:: ይመርጣልም:: ለእነርሱ ምርጫ የላቸዉም:: አላህ ከማይገባው ሁሉ ጠራ ከሚያጋሯቸዉም ላቀ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَرَبُّكَ يَعْلَمُ مَا تُكِنُّ صُدُورُهُمْ وَمَا يُعْلِنُونَ
Amharic Translation - Africa Academy69. ጌታህም ልቦቻቸው የሚደብቁትንና የሚገልጹትን ሁሉ ያውቃል።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَهُوَ ٱللَّهُ لَآ إِلَٰهَ إِلَّا هُوَ لَهُ ٱلْحَمْدُ فِى ٱلْأُولَىٰ وَٱلْـَٔاخِرَةِ وَلَهُ ٱلْحُكْمُ وَإِلَيْهِ تُرْجَعُونَ
Amharic Translation - Africa Academy70. እርሱም አላህ ነው። ከእርሱ ሌላ አምላክ የለም:: ምስጋና ሁሉ በመጀመሪያም በመጨረሻይቱም ዓለም ለእርሱ ብቻ ነው:: ፍርዱም የእርሱ ብቻ ነው፤ ወደ እርሱም ትመለሳላችሁ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قُلْ أَرَءَيْتُمْ إِن جَعَلَ ٱللَّهُ عَلَيْكُمُ ٱلَّيْلَ سَرْمَدًا إِلَىٰ يَوْمِ ٱلْقِيَٰمَةِ مَنْ إِلَٰهٌ غَيْرُ ٱللَّهِ يَأْتِيكُم بِضِيَآءٍ أَفَلَا تَسْمَعُونَ
Amharic Translation - Africa Academy71. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «አያችሁን? (እስቲ ንገሩኝ) አላህ በእናንተ ላይ ሌሊትን እስከ ትንሳኤ ቀን ድረስ ዘውታሪ ቢያደርገው ከአላህ ሌላ ብርሃንን የሚያመጣላችሁ አምላክ ማነው? አትሰሙምን?» በላቸው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قُلْ أَرَءَيْتُمْ إِن جَعَلَ ٱللَّهُ عَلَيْكُمُ ٱلنَّهَارَ سَرْمَدًا إِلَىٰ يَوْمِ ٱلْقِيَٰمَةِ مَنْ إِلَٰهٌ غَيْرُ ٱللَّهِ يَأْتِيكُم بِلَيْلٍ تَسْكُنُونَ فِيهِ أَفَلَا تُبْصِرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy72. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «አያችሁን? አላህ በእናንተ ላይ ቀንን እስከ ትንሳኤ ቀን ድረስ ዘውታሪ ቢያደርገው ከአላህ ሌላ በውስጡ የምታርፉበትን ሌሊት የሚያመጣላችሁ አምላክ ማን ነው? አታስተውሉምን?» በላቸው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَمِن رَّحْمَتِهِۦ جَعَلَ لَكُمُ ٱلَّيْلَ وَٱلنَّهَارَ لِتَسْكُنُوا۟ فِيهِ وَلِتَبْتَغُوا۟ مِن فَضْلِهِۦ وَلَعَلَّكُمْ تَشْكُرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy73. ከችሮታዉም ለእናንተ ሌሊትንና ቀንን በውስጡ ልታርፉበት ከትሩፋቱም ልትፈልጉበት አመስጋኞችም ልትሆኑ አደረገላችሁ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَيَوْمَ يُنَادِيهِمْ فَيَقُولُ أَيْنَ شُرَكَآءِىَ ٱلَّذِينَ كُنتُمْ تَزْعُمُونَ
Amharic Translation - Africa Academy74. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የሚጠራባቸውንም ቀንና «እነዚያ ተጋሪዎቼ ትሉዋቸው የነበራችሁት የት ናቸው?» የሚልበትን ቀን አስታውስ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَنَزَعْنَا مِن كُلِّ أُمَّةٍ شَهِيدًا فَقُلْنَا هَاتُوا۟ بُرْهَٰنَكُمْ فَعَلِمُوٓا۟ أَنَّ ٱلْحَقَّ لِلَّهِ وَضَلَّ عَنْهُم مَّا كَانُوا۟ يَفْتَرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy75. ከህዝቦችም ሁሉ መስካሪን እናወጣና «ማስረጃችሁን አምጡ» እንላለን። ያን ጊዜ እውነተኛዉም አምላክነት ለአላህ ብቻ መሆኑን ያውቃሉ:: ይቀጣጥፉት የነበሩትም ከእነርሱ ይጠፋባቸዋል::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِنَّ قَٰرُونَ كَانَ مِن قَوْمِ مُوسَىٰ فَبَغَىٰ عَلَيْهِمْ وَءَاتَيْنَٰهُ مِنَ ٱلْكُنُوزِ مَآ إِنَّ مَفَاتِحَهُۥ لَتَنُوٓأُ بِٱلْعُصْبَةِ أُو۟لِى ٱلْقُوَّةِ إِذْ قَالَ لَهُۥ قَوْمُهُۥ لَا تَفْرَحْ إِنَّ ٱللَّهَ لَا يُحِبُّ ٱلْفَرِحِينَ
Amharic Translation - Africa Academy76. ቃሩን ከሙሳ ነገዶች አንዱ ነበር:: በእነርሱም ላይ አመጸ:: ከድልቦችም ያንን መክፈቻዎቹ ብቻ የኃይል ባለቤቶች የሆኑ ቡድኖችን ሸክሙ የሚከብድን ሰጠነው:: ወገኖቹ ለእርሱ ባሉትም ጊዜ አስታውስ: «አትኩራ አላህ ኩራተኞችን አይወድምና።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَٱبْتَغِ فِيمَآ ءَاتَىٰكَ ٱللَّهُ ٱلدَّارَ ٱلْـَٔاخِرَةَ وَلَا تَنسَ نَصِيبَكَ مِنَ ٱلدُّنْيَا وَأَحْسِن كَمَآ أَحْسَنَ ٱللَّهُ إِلَيْكَ وَلَا تَبْغِ ٱلْفَسَادَ فِى ٱلْأَرْضِ إِنَّ ٱللَّهَ لَا يُحِبُّ ٱلْمُفْسِدِينَ
Amharic Translation - Africa Academy77. «አላህም በሰጠህ ሀብት የመጨረሻይቱን አገር ፈልግ:: ሆኖም ከቅርቢቱ አለምም ፈንታህን አትርሳ:: አላህ ወደ አንተ መልካምን እንዳደረገልህ መልካምን አድርግ:: በምድርም ውስጥ ማጥፋትን አትፈልግ:: አላህ አጥፊዎችን አይወድምና።» አሉት።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالَ إِنَّمَآ أُوتِيتُهُۥ عَلَىٰ عِلْمٍ عِندِىٓ أَوَلَمْ يَعْلَمْ أَنَّ ٱللَّهَ قَدْ أَهْلَكَ مِن قَبْلِهِۦ مِنَ ٱلْقُرُونِ مَنْ هُوَ أَشَدُّ مِنْهُ قُوَّةً وَأَكْثَرُ جَمْعًا وَلَا يُسْـَٔلُ عَن ذُنُوبِهِمُ ٱلْمُجْرِمُونَ
Amharic Translation - Africa Academy78. «(ሀብትን) የተሰጠሁት እኔ ዘንድ ባለው እውቀት ነው።» አለ። አላህ ከእርሱ በፊት ከክፍለ ዘመናት ሰዎች በኃይል ከእርሱ ይበልጥ የበረቱትን ሀብትን በመሰብሰብም ይበልጥ የበዙትን በእርግጥ ያጠፋ መሆኑን አያውቅምን? አመጸኞችም ከኃጢአቶቻቸው ጥያቄ አይጠየቁም።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَخَرَجَ عَلَىٰ قَوْمِهِۦ فِى زِينَتِهِۦ قَالَ ٱلَّذِينَ يُرِيدُونَ ٱلْحَيَوٰةَ ٱلدُّنْيَا يَٰلَيْتَ لَنَا مِثْلَ مَآ أُوتِىَ قَٰرُونُ إِنَّهُۥ لَذُو حَظٍّ عَظِيمٍ
Amharic Translation - Africa Academy79. በህዝቦቹም ላይ በጌጡ ውስጥ ሆኖ ወጣ:: እነዚያ ቅርቢቱን ህይወት የሚፈልጉት «ወይ ምኞታችን! ቃሩን የተሰጠው ቢጤ ምነው ለእኛ በኖረን፤ እርሱ የታላቅ ዕድል ባለቤት ነውና።» አሉ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَقَالَ ٱلَّذِينَ أُوتُوا۟ ٱلْعِلْمَ وَيْلَكُمْ ثَوَابُ ٱللَّهِ خَيْرٌ لِّمَنْ ءَامَنَ وَعَمِلَ صَٰلِحًا وَلَا يُلَقَّىٰهَآ إِلَّا ٱلصَّٰبِرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy80. እነዚያም ዕውቀትን የተሰጡት «ወዮላችሁ! የአላህ ምንዳ ላመነ ሰው መልካምንም ለሰራ በላጭ ነው:: ታጋሾችም እንጂ ሌላው አያገኛትም።» አሉ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَخَسَفْنَا بِهِۦ وَبِدَارِهِ ٱلْأَرْضَ فَمَا كَانَ لَهُۥ مِن فِئَةٍ يَنصُرُونَهُۥ مِن دُونِ ٱللَّهِ وَمَا كَانَ مِنَ ٱلْمُنتَصِرِينَ
Amharic Translation - Africa Academy81. በእርሱም በቤትም ምድርን ደረባን (አሰጠምን):: ለእርሱም ከአላህ ሌላ የሚረዱት ቡድኖች ምንም አልነበሩትም:: ከሚረዱትም አልነበረም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَأَصْبَحَ ٱلَّذِينَ تَمَنَّوْا۟ مَكَانَهُۥ بِٱلْأَمْسِ يَقُولُونَ وَيْكَأَنَّ ٱللَّهَ يَبْسُطُ ٱلرِّزْقَ لِمَن يَشَآءُ مِنْ عِبَادِهِۦ وَيَقْدِرُ لَوْلَآ أَن مَّنَّ ٱللَّهُ عَلَيْنَا لَخَسَفَ بِنَا وَيْكَأَنَّهُۥ لَا يُفْلِحُ ٱلْكَٰفِرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy82. እነዚያም በትላንትናው ቀን ስፍራውን ይመኙ የነበሩት «ወይ ጉድ! ለካ አላህ ከባሮቹ ለሚሻው ሰው ሲሳይን ያሰፋል:: ያጠባልም:: አላህ በእኛ ላይ በእምነት ባልለገሰልን ኖሮ ምድርን በእኛ ላይ በገለበጠብን ነበር:: ወይ ጉድ! ከሓዲያን አይድኑም።» የሚሉ ሆነው አነጉ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
تِلْكَ ٱلدَّارُ ٱلْـَٔاخِرَةُ نَجْعَلُهَا لِلَّذِينَ لَا يُرِيدُونَ عُلُوًّا فِى ٱلْأَرْضِ وَلَا فَسَادًا وَٱلْعَٰقِبَةُ لِلْمُتَّقِينَ
Amharic Translation - Africa Academy83. ይህች የመጨረሻይቱ አገር ናት:: ለእነዚያ በምድር ውስጥ ኩራትንና ማመጽን ለማይፈልጉት ሁሉ እናደርጋታለን:: ምስጉኒቱም መጨረሻ ለጥንቁቆቹ ብቻ ናት::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
مَن جَآءَ بِٱلْحَسَنَةِ فَلَهُۥ خَيْرٌ مِّنْهَا وَمَن جَآءَ بِٱلسَّيِّئَةِ فَلَا يُجْزَى ٱلَّذِينَ عَمِلُوا۟ ٱلسَّيِّـَٔاتِ إِلَّا مَا كَانُوا۟ يَعْمَلُونَ
Amharic Translation - Africa Academy84. በደግ ስራ የመጣ ለእርሱ ከእርሷ በላጭ ምንዳ አለው:: በክፉም ስራ የመጡ እነዚህ መጥፎዎችን የሰሩ ይሰሩት የነበሩትን እንጂ አይመነዱም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِنَّ ٱلَّذِى فَرَضَ عَلَيْكَ ٱلْقُرْءَانَ لَرَآدُّكَ إِلَىٰ مَعَادٍ قُل رَّبِّىٓ أَعْلَمُ مَن جَآءَ بِٱلْهُدَىٰ وَمَنْ هُوَ فِى ضَلَٰلٍ مُّبِينٍ
Amharic Translation - Africa Academy85. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ያ ቁርኣንን የተከፋፈለ ሆኖ ባንተ ላይ ያወረደውና ህግጋቱን እንድትትገበር ግድ ያደረግብህ አምላክ ወደ መመለሻ (ወደ መካ) በእርግጥ መላሽህ ነው። «ጌታዬ በቅን መንገድ የመጣውንና እርሱም በግልጽ ስህተት ውስጥ የሆነውን አዋቂ ነው» በላቸው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَمَا كُنتَ تَرْجُوٓا۟ أَن يُلْقَىٰٓ إِلَيْكَ ٱلْكِتَٰبُ إِلَّا رَحْمَةً مِّن رَّبِّكَ فَلَا تَكُونَنَّ ظَهِيرًا لِّلْكَٰفِرِينَ
Amharic Translation - Africa Academy86.(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) መጽሐፉ ወደ አንተ መወረዱን ተስፋ የምታደርግ አልነበርክም :: ግን ከጌታህ ችሮታ ተወረደልህ:: ለከሓዲያን በፍጹም ረዳት አትሁን::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلَا يَصُدُّنَّكَ عَنْ ءَايَٰتِ ٱللَّهِ بَعْدَ إِذْ أُنزِلَتْ إِلَيْكَ وَٱدْعُ إِلَىٰ رَبِّكَ وَلَا تَكُونَنَّ مِنَ ٱلْمُشْرِكِينَ
Amharic Translation - Africa Academy87.(መልዕክተኛችንሙሐመድ ሆይ!) ከአላህም አናቅጽ ወደ አንተ ከተወረዱ በኋላ አያግዱህ:: ወደ ጌታህም ሰዎችን ጥራ:: ከአጋሪዎችም አትሁን::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلَا تَدْعُ مَعَ ٱللَّهِ إِلَٰهًا ءَاخَرَ لَآ إِلَٰهَ إِلَّا هُوَ كُلُّ شَىْءٍ هَالِكٌ إِلَّا وَجْهَهُۥ لَهُ ٱلْحُكْمُ وَإِلَيْهِ تُرْجَعُونَ
Amharic Translation - Africa Academy88. ከአላህም ጋር ሌላን አምላክ አትገዛ:: ከእርሱም በቀር አምላክ የለም። ከእርሱ በስተቀር ሁሉም ጠፊ ነው:: ፍርዱ የእርሱ ብቻ ነው:: ሁላችሁም ወደ እርሱ ትመለሳላችሁ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
→