caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ An-Naml፣ አንቀጽ 60

መካ · የወረደበት ቅደም ተከተል 48 · 27:60

أَمَّنْ خَلَقَ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضَ وَأَنزَلَ لَكُم مِّنَ ٱلسَّمَآءِ مَآءً فَأَنۢبَتْنَا بِهِۦ حَدَآئِقَ ذَاتَ بَهْجَةٍ مَّا كَانَ لَكُمْ أَن تُنۢبِتُوا۟ شَجَرَهَآ أَءِلَٰهٌ مَّعَ ٱللَّهِ بَلْ هُمْ قَوْمٌ يَعْدِلُونَ

Amharic Translation - Africa Academy60. ወይስ ያ ሰማያትንና ምድርን የፈጠረና ከሰማይም ለእናንተ ውሃን ያወረደው ማን ሆነና? በእርሱም ባለ ውበት የሆኑትን የታጠሩ አትክልቶችን ዛፍዋን ልታበቅሉ ለእናንተ ችሎታ ሳይኖራችሁ እኛ ብቻችንን አበቀልን:: ከአላህ ጋር ሌላ አምላክ አለን? (የለም) ግን እነርሱ ከእውነት የሚያዘነብሉ ህዝቦች ናቸው።
Amharic Translation - Muhammad Sadiqወይም ያ ሰማያትንና ምድርን የፈጠረና ከሰማይም ለእናንተ ውሃን ያወረደው (ይበልጣል ወይስ የሚያጋሩት?) በእርሱም ባለውበት የኾኑትን የታጠሩ አትክልቶችን ዛፍዋን ልታበቅሉ ለናንተ ችሎታ ያልነበራችሁን አበቀልን፡፡ ከአላህ ጋር ሌላ አምላክ አለን? (የለም)፡፡ ግን እነርሱ (ከእውነት) የሚያዘነብሉ ሕዝቦች ናቸው፡፡
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70