caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Ash-Shura الشورى

53 አንቀጾች · መካ · የወረደበት ቅደም ተከተል 62

بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ حمٓ

Amharic Translation - Africa Academy1. ሓ፤ሚይም፤

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

عٓسٓقٓ

Amharic Translation - Africa Academy2. ዐይን፤ ሲን፤ ቃፍ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

كَذَٰلِكَ يُوحِىٓ إِلَيْكَ وَإِلَى ٱلَّذِينَ مِن قَبْلِكَ ٱللَّهُ ٱلْعَزِيزُ ٱلْحَكِيمُ

Amharic Translation - Africa Academy3. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ልክ እንደዚሁ በዚህ ምዕራፍ ውስጥ እንዳለው አሸናፊውና ጥበበኛው አላህ ወደ አንተ ያወርዳል:: ወደ እነዚያም ካንተ በፊት ወደ ነበሩት ህዝቦችም አውርዷል::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

لَهُۥ مَا فِى ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَمَا فِى ٱلْأَرْضِ وَهُوَ ٱلْعَلِىُّ ٱلْعَظِيمُ

Amharic Translation - Africa Academy4. በሰማያትና በምድር ዉስጥ ያለው ሁሉ የእርሱ ብቻ ነው:: እርሱም የበላዩ ታላቁ ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

تَكَادُ ٱلسَّمَٰوَٰتُ يَتَفَطَّرْنَ مِن فَوْقِهِنَّ وَٱلْمَلَٰٓئِكَةُ يُسَبِّحُونَ بِحَمْدِ رَبِّهِمْ وَيَسْتَغْفِرُونَ لِمَن فِى ٱلْأَرْضِ أَلَآ إِنَّ ٱللَّهَ هُوَ ٱلْغَفُورُ ٱلرَّحِيمُ

Amharic Translation - Africa Academy5. ከአላህ ፍራቻ የተነሳ ሰማያት ከበላያቸው ሊቀደዱ ይቀርባሉ፤ መላእክትም ጌታቸውን እያመሰገኑ ያጠራሉ:: በምድር ላለው ፍጡርም ምህረትን ይለምናሉ:: (ሙስሊሞች ሆይ!) አስተዉሉ:: መሀሪውና አዛኙ አላህ ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَٱلَّذِينَ ٱتَّخَذُوا۟ مِن دُونِهِۦٓ أَوْلِيَآءَ ٱللَّهُ حَفِيظٌ عَلَيْهِمْ وَمَآ أَنتَ عَلَيْهِم بِوَكِيلٍ

Amharic Translation - Africa Academy6. እነዚያም ከእርሱ ሌላ ጣዖታትን ረዳቶች አድርገው የያዙ ሁሉ አላህ በእነርሱ ላይ ተጠባባቂ ነው:: አንተም በእነርሱ ላይ ሀላፊ አይደለህም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَكَذَٰلِكَ أَوْحَيْنَآ إِلَيْكَ قُرْءَانًا عَرَبِيًّا لِّتُنذِرَ أُمَّ ٱلْقُرَىٰ وَمَنْ حَوْلَهَا وَتُنذِرَ يَوْمَ ٱلْجَمْعِ لَا رَيْبَ فِيهِ فَرِيقٌ فِى ٱلْجَنَّةِ وَفَرِيقٌ فِى ٱلسَّعِيرِ

Amharic Translation - Africa Academy7. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ልክ እንደዚሁም የከተሞች እናት የሆነችውን የመካን ሰዎችና በአካባቢዋ ያሉትን ህዝቦች ልታስፈራራ የመሰብሰቢያውንም ቀን በእርሱ ጥርጣሬ የሌለበት ሲሆን ልታስጠነቅቅ በዐረበኛ ቋንቋ የሆነን ቁርኣንን ወደ አንተ አወረድን:: ከእነርሱም ከፊሉ በገነት ውስጥ ከፊሉም ደግሞ በእሳት ውስጥ ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلَوْ شَآءَ ٱللَّهُ لَجَعَلَهُمْ أُمَّةً وَٰحِدَةً وَلَٰكِن يُدْخِلُ مَن يَشَآءُ فِى رَحْمَتِهِۦ وَٱلظَّٰلِمُونَ مَا لَهُم مِّن وَلِىٍّ وَلَا نَصِيرٍ

Amharic Translation - Africa Academy8. አላህ በፈለገ ኖሮ ሰዎችን በአንድ ሃይማኖት ላይ የሆኑ አንድ ህዝብ ባደረጋቸው ነበር:: ግን የሚፈልገውን ሰው በእዝነቱ ውስጥ ያስገባዋል:: በዳዮች ሁሉ ምንም ወዳጅና ረዳት የላቸዉም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَمِ ٱتَّخَذُوا۟ مِن دُونِهِۦٓ أَوْلِيَآءَ فَٱللَّهُ هُوَ ٱلْوَلِىُّ وَهُوَ يُحْىِ ٱلْمَوْتَىٰ وَهُوَ عَلَىٰ كُلِّ شَىْءٍ قَدِيرٌ

Amharic Translation - Africa Academy9. ከእርሱ ሌላ ረዳቶች ያዙን? (እነርሱ ረዳቶች አይደሉም) ትክክለኛ ረዳት አላህ ብቻ ነው:: እርሱ ሙታንን ህያው ያደርጋል:: እርሱም በሁሉም ነገር ላይ ቻይ ነውና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَمَا ٱخْتَلَفْتُمْ فِيهِ مِن شَىْءٍ فَحُكْمُهُۥٓ إِلَى ٱللَّهِ ذَٰلِكُمُ ٱللَّهُ رَبِّى عَلَيْهِ تَوَكَّلْتُ وَإِلَيْهِ أُنِيبُ

Amharic Translation - Africa Academy10. (ሰዎች ሆይ!) «ያ የተለያያችሁበት ነገር ሁሉ ፍርዱ ወደ አላህ ብቻ ነው:: እርሱ (አላህ) ጌታዬ ነው:: በእርሱ ላይ ተመካሁ:: ወደ እርሱም ብቻ እመለሳለሁ» በላቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَاطِرُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِ جَعَلَ لَكُم مِّنْ أَنفُسِكُمْ أَزْوَٰجًا وَمِنَ ٱلْأَنْعَٰمِ أَزْوَٰجًا يَذْرَؤُكُمْ فِيهِ لَيْسَ كَمِثْلِهِۦ شَىْءٌ وَهُوَ ٱلسَّمِيعُ ٱلْبَصِيرُ

Amharic Translation - Africa Academy11. ሰማያትንና ምድርን የፈጠረው አላህ ከነፍሶቻችሁ ሴቶችን ከቤት እንሰሳዎችም አይነቶችን (ወንዶችና ሴቶችን) ለእናንተ ፈጠረላችሁ:: በዚህ ድርጊቱም ያባዛችኋል:: የሚመስለው ምንም ነገር የለም:: እርሱ ሁሉን ነገር ሰሚና ሁሉን ተመልካች ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

لَهُۥ مَقَالِيدُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِ يَبْسُطُ ٱلرِّزْقَ لِمَن يَشَآءُ وَيَقْدِرُ إِنَّهُۥ بِكُلِّ شَىْءٍ عَلِيمٌ

Amharic Translation - Africa Academy12. የሰማያትና የምድር (ድልቦች) መክፈቻዎች የእርሱ ብቻ ናቸው:: ሲሳይን ለሚፈልገው ሰው ያሰፋል:: ለሚፈልገዉም ያጠባል:: እርሱ ሁሉን ነገር አዋቂ ነውና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

شَرَعَ لَكُم مِّنَ ٱلدِّينِ مَا وَصَّىٰ بِهِۦ نُوحًا وَٱلَّذِىٓ أَوْحَيْنَآ إِلَيْكَ وَمَا وَصَّيْنَا بِهِۦٓ إِبْرَٰهِيمَ وَمُوسَىٰ وَعِيسَىٰٓ أَنْ أَقِيمُوا۟ ٱلدِّينَ وَلَا تَتَفَرَّقُوا۟ فِيهِ كَبُرَ عَلَى ٱلْمُشْرِكِينَ مَا تَدْعُوهُمْ إِلَيْهِ ٱللَّهُ يَجْتَبِىٓ إِلَيْهِ مَن يَشَآءُ وَيَهْدِىٓ إِلَيْهِ مَن يُنِيبُ

Amharic Translation - Africa Academy13. (ሰዎች ሆይ!) ለእናንተ ከሃይማኖት ያንን በእርሱ ኑህን ያዘዘበትን ያንንም ወደ አንተ ያወረድነውን ያንንም ኢብራሂምን፤ ሙሳንና ዒሳንም በእርሱ ያዘዝንበት የሆነውን ሃይማኖትን በትክክል አቋቁሙ በእርሱም ላይ አትለያዩ በማለት ደነገገላችሁ::(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በአላህ አጋሪዎች ያ ወደ እርሱ የምትጠራቸው ነገር (ኢስላም) ከበዳቸው:: አላህ የሚፈልገውን ሰው ወደ እርሱ እምነት ይመርጣል:: የሚመለስንም ሰው ወደ እርሱ ይመራል::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَمَا تَفَرَّقُوٓا۟ إِلَّا مِنۢ بَعْدِ مَا جَآءَهُمُ ٱلْعِلْمُ بَغْيًۢا بَيْنَهُمْ وَلَوْلَا كَلِمَةٌ سَبَقَتْ مِن رَّبِّكَ إِلَىٰٓ أَجَلٍ مُّسَمًّى لَّقُضِىَ بَيْنَهُمْ وَإِنَّ ٱلَّذِينَ أُورِثُوا۟ ٱلْكِتَٰبَ مِنۢ بَعْدِهِمْ لَفِى شَكٍّ مِّنْهُ مُرِيبٍ

Amharic Translation - Africa Academy14. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የሃይማኖት ሰዎች እውቀት ከመጣላቸው በኋላ በመካከላቸው ባለ ወሰን አላፊነት እንጂ በሌላ አልተለያዩም:: እስከተወሰነ ጊዜ በማቆየት ከጌታህ ያለፈች ቃል ባልነበረች ኖሮ በእነርሱ መካከል አሁኑኑ በተፈረደ ነበር:: እነዚያም ከኋላቸው መጽሐፍን እንዲወርሱ የተደረጉት ከእርሱ በእርግጥ ባወላዋይ ጥርጣሬ ውስጥ ናቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَلِذَٰلِكَ فَٱدْعُ وَٱسْتَقِمْ كَمَآ أُمِرْتَ وَلَا تَتَّبِعْ أَهْوَآءَهُمْ وَقُلْ ءَامَنتُ بِمَآ أَنزَلَ ٱللَّهُ مِن كِتَٰبٍ وَأُمِرْتُ لِأَعْدِلَ بَيْنَكُمُ ٱللَّهُ رَبُّنَا وَرَبُّكُمْ لَنَآ أَعْمَٰلُنَا وَلَكُمْ أَعْمَٰلُكُمْ لَا حُجَّةَ بَيْنَنَا وَبَيْنَكُمُ ٱللَّهُ يَجْمَعُ بَيْنَنَا وَإِلَيْهِ ٱلْمَصِيرُ

Amharic Translation - Africa Academy15. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ወደ እዚህ መንገድም ጋኔንንና ሰዎችን ጥራ:: ልክ እንደታዘዝከዉም ቀጥ በል:: ዝንባሌያቸውን አትከተል:: «ከመጽሐፍም አላህ ባወረደው ሁሉ አመንኩ:: በመካከላችሁ በፍርድ ላስተካክልም ታዘዝኩ:: አላህ ጌታችን ጌታችሁም ነው:: ለእኛ ስራዎቻችን አሉን:: ለእናንተም እንዲሁ ስራዎቻችሁ አሏችሁ:: በእኛና በእናንተ መካከል ክርክር የለም:: አላህ በመካከላችን ይሰበስባል:: መመለሻው ወደ እርሱ ብቻ ነው።» በላቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَٱلَّذِينَ يُحَآجُّونَ فِى ٱللَّهِ مِنۢ بَعْدِ مَا ٱسْتُجِيبَ لَهُۥ حُجَّتُهُمْ دَاحِضَةٌ عِندَ رَبِّهِمْ وَعَلَيْهِمْ غَضَبٌ وَلَهُمْ عَذَابٌ شَدِيدٌ

Amharic Translation - Africa Academy16. እነዚያም በአላህ ሃይማኖት ተቀባይነት ካገኘ በኋላ የሚከራከሩት ሰዎች ማስረጃዎቻቸው በጌታቸው ዘንድ ብልሹ (ዉድቅ) ናቸው:: በእነርሱም ላይ የአላህ ቁጣ አለባቸው (ወደቀባቸው):: ለእነርሱም ብርቱ ቅጣት አለባቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ٱللَّهُ ٱلَّذِىٓ أَنزَلَ ٱلْكِتَٰبَ بِٱلْحَقِّ وَٱلْمِيزَانَ وَمَا يُدْرِيكَ لَعَلَّ ٱلسَّاعَةَ قَرِيبٌ

Amharic Translation - Africa Academy17. አላህ ያ መጽሐፉን በእውነት ያወረደ ነው:: ሚዛንንም ልክ እንደዚሁ ያወረደ ነው:: ሰዓቲቱ ምን አልባት ቅርብ ብትሆንስ ምን አሳወቀህ?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

يَسْتَعْجِلُ بِهَا ٱلَّذِينَ لَا يُؤْمِنُونَ بِهَا وَٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ مُشْفِقُونَ مِنْهَا وَيَعْلَمُونَ أَنَّهَا ٱلْحَقُّ أَلَآ إِنَّ ٱلَّذِينَ يُمَارُونَ فِى ٱلسَّاعَةِ لَفِى ضَلَٰلٍۭ بَعِيدٍ

Amharic Translation - Africa Academy18. እነዚያ በእርሷ የማያምኑት በእርሷ ያቻኩላሉ:: እነዚያ በአላህ ያመኑት ግን ከእርሷ ፈሪዎች ናቸው:: እርሷ እውነት መሆኗንም በትክክል ያውቃሉ:: (ሙስሊሞች ሆይ!) አስተውሉ:: እነዚያ በሰዓቲቱ የሚከራከሩ ሰዎች ሁሉ በእርግጥ ከእውነት በራቀ ስህተት ውስጥ ናቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ٱللَّهُ لَطِيفٌۢ بِعِبَادِهِۦ يَرْزُقُ مَن يَشَآءُ وَهُوَ ٱلْقَوِىُّ ٱلْعَزِيزُ

Amharic Translation - Africa Academy19. አላህ ለባሮቹ በጣም ሩህሩህ ነው:: ለሚፈልገው ሰውም ሁሉ በሰፊው ሲሳይን ይሰጣል:: እርሱም ብርቱዉ እና አሸናፊው ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

مَن كَانَ يُرِيدُ حَرْثَ ٱلْـَٔاخِرَةِ نَزِدْ لَهُۥ فِى حَرْثِهِۦ وَمَن كَانَ يُرِيدُ حَرْثَ ٱلدُّنْيَا نُؤْتِهِۦ مِنْهَا وَمَا لَهُۥ فِى ٱلْـَٔاخِرَةِ مِن نَّصِيبٍ

Amharic Translation - Africa Academy20. በስራው የኋለኛይቱን ዓለም አዝመራ የሚፈልግ ሰው ሁሉ ለእርሱ በአዝመራው ላይ ሌላን እንጨምርለታለን:: የቅርቢቱን ዓለም አዝመራ የሚፈልግ ሰው ግን በእርሷ የተወሰነለትን ብቻ እንሰጠዋለን:: ለእርሱም በኋለኛይቱ ዓለም ምንም ድርሻ የለዉም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَمْ لَهُمْ شُرَكَٰٓؤُا۟ شَرَعُوا۟ لَهُم مِّنَ ٱلدِّينِ مَا لَمْ يَأْذَنۢ بِهِ ٱللَّهُ وَلَوْلَا كَلِمَةُ ٱلْفَصْلِ لَقُضِىَ بَيْنَهُمْ وَإِنَّ ٱلظَّٰلِمِينَ لَهُمْ عَذَابٌ أَلِيمٌ

Amharic Translation - Africa Academy21. ከሓዲያን ከአላህ ያልተፈቀደውን ሃይማኖት የደነገጉ ተጋሪዎች ለእነርሱ አሏቸውን? የፍርዱ ቃል ባልነበረ ኖሮ በመካከላቸው ወዲያውኑ በተፈረደ ነበር:: በደለኞችም አሳማሚ ቅጣት በእርግጥ አለባቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

تَرَى ٱلظَّٰلِمِينَ مُشْفِقِينَ مِمَّا كَسَبُوا۟ وَهُوَ وَاقِعٌۢ بِهِمْ وَٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ وَعَمِلُوا۟ ٱلصَّٰلِحَٰتِ فِى رَوْضَاتِ ٱلْجَنَّاتِ لَهُم مَّا يَشَآءُونَ عِندَ رَبِّهِمْ ذَٰلِكَ هُوَ ٱلْفَضْلُ ٱلْكَبِيرُ

Amharic Translation - Africa Academy22. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በደለኞችን በሰሩት ስራ ዋጋ በትንሳኤ ቀን ፈሪዎች ሆነው ታያቸዋለህ:: እርሱም በእነርሱ ላይ የማይቀር ወዳቂ ነው:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚያም በአላህ ያመኑና መልካም ስራን የሰሩ ሁሉ በገነት ጨፌዎች ዉስጥ ናቸው:: ለእነርሱም በጌታቸው ዘንድ የሚፈልጉት ሁሉ አለላቸው:: ይህ ታላቅ ችሮታ ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ذَٰلِكَ ٱلَّذِى يُبَشِّرُ ٱللَّهُ عِبَادَهُ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ وَعَمِلُوا۟ ٱلصَّٰلِحَٰتِ قُل لَّآ أَسْـَٔلُكُمْ عَلَيْهِ أَجْرًا إِلَّا ٱلْمَوَدَّةَ فِى ٱلْقُرْبَىٰ وَمَن يَقْتَرِفْ حَسَنَةً نَّزِدْ لَهُۥ فِيهَا حُسْنًا إِنَّ ٱللَّهَ غَفُورٌ شَكُورٌ

Amharic Translation - Africa Academy23. (ይህ ታላቅ ችሮታ) ያ አላህ እነዚያን በትክክል ያመኑትንና መልካሞችን የሰሩት ባሮቹን የሚያበስርበት ነው::(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) መልዕክቴን በማድረሴ ላይ የዝምድና ውዴታየን እንጂ ሌላ ዋጋ አልጠይቃችሁም በላቸው:: መልካም ስራ የሚሰራ ሰው ሁሉ ለእርሱ በእርሷ ላይ መልካምን ነገርን እንጨምርለታለን:: አላህ መሀሪ እና አመስጋኝ ነውና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَمْ يَقُولُونَ ٱفْتَرَىٰ عَلَى ٱللَّهِ كَذِبًا فَإِن يَشَإِ ٱللَّهُ يَخْتِمْ عَلَىٰ قَلْبِكَ وَيَمْحُ ٱللَّهُ ٱلْبَٰطِلَ وَيُحِقُّ ٱلْحَقَّ بِكَلِمَٰتِهِۦٓ إِنَّهُۥ عَلِيمٌۢ بِذَاتِ ٱلصُّدُورِ

Amharic Translation - Africa Academy24. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ይልቁንም «በአላህ ላይ ውሸትን ቀጠፈ» ይላሉን? አላህም ቢፈልግ በልብህ ላይ ያትማል:: አላህ ውሸትን ያብሳል:: እውነትንም በቃላቱ ያረጋግጣል:: እርሱ በይፋ የተነገሩት ቀርቶ በልቦች ውስጥ ያለውን ሁሉ አዋቂ ነውና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَهُوَ ٱلَّذِى يَقْبَلُ ٱلتَّوْبَةَ عَنْ عِبَادِهِۦ وَيَعْفُوا۟ عَنِ ٱلسَّيِّـَٔاتِ وَيَعْلَمُ مَا تَفْعَلُونَ

Amharic Translation - Africa Academy25. እርሱም አላህ ያ ሁልጊዜም ከባሮቹ ንስሀን የሚቀበል ኃጢአቶችንም ይቅር የሚል የምትሰሩትንም ሁሉ የሚያውቅ ጌታ ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَيَسْتَجِيبُ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ وَعَمِلُوا۟ ٱلصَّٰلِحَٰتِ وَيَزِيدُهُم مِّن فَضْلِهِۦ وَٱلْكَٰفِرُونَ لَهُمْ عَذَابٌ شَدِيدٌ

Amharic Translation - Africa Academy26. እነዚያም በአላህ ያመኑትና መልካም ተግባሮችን የሰሩትን ልመናቸውን ይቀበላል:: ከችሮታዉም ይጨምርላቸዋል:: ከሓዲያንም ለእነርሱ ብርቱ ቅጣት አለባቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلَوْ بَسَطَ ٱللَّهُ ٱلرِّزْقَ لِعِبَادِهِۦ لَبَغَوْا۟ فِى ٱلْأَرْضِ وَلَٰكِن يُنَزِّلُ بِقَدَرٍ مَّا يَشَآءُ إِنَّهُۥ بِعِبَادِهِۦ خَبِيرٌۢ بَصِيرٌ

Amharic Translation - Africa Academy27. አላህም ለባሮቹ ሁሉ ሲሳይን በዘረጋ ኖሮ በምድር ውስጥ ሁሉም ወሰን ባለፉ ነበር:: ግን የሚፈልገውን በልክ ያወርዳል:: እርሱ በባሮቹ ውስጠ አዋቂ፤ ተመልካች ነውና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَهُوَ ٱلَّذِى يُنَزِّلُ ٱلْغَيْثَ مِنۢ بَعْدِ مَا قَنَطُوا۟ وَيَنشُرُ رَحْمَتَهُۥ وَهُوَ ٱلْوَلِىُّ ٱلْحَمِيدُ

Amharic Translation - Africa Academy28. አላህ ያ ተስፋ ከቆረጡ በኋላ ዝናብን የሚያወርድ ችሮታውንም የሚዘረጋ ነው:: እርሱም ረዳቱና ምስጉኑ ነውና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَمِنْ ءَايَٰتِهِۦ خَلْقُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِ وَمَا بَثَّ فِيهِمَا مِن دَآبَّةٍ وَهُوَ عَلَىٰ جَمْعِهِمْ إِذَا يَشَآءُ قَدِيرٌ

Amharic Translation - Africa Academy29. ሰማያትንና ምድርን መፍጠሩ ከተንቀሳቃሽም በሁለቱ ውስጥ የበተነውን ፍጡር መፍጠሩ ከአስደናቂ ምልክቶቹ ከፊሎቹ ናቸው:: እርሱም በሚፈልግ ጊዜ እነርሱን በመሰብሰብ ላይ ቻይ ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَمَآ أَصَٰبَكُم مِّن مُّصِيبَةٍ فَبِمَا كَسَبَتْ أَيْدِيكُمْ وَيَعْفُوا۟ عَن كَثِيرٍ

Amharic Translation - Africa Academy30. (ሰዎች ሆይ!) ማንኛዉም መከራ (ያገኛችሁ ነገር) እጆቻችሁ በሰሩት ኃጢአት ምክንያት ብቻ ነው:: ብዙውንም ይቅር ይላል::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَمَآ أَنتُم بِمُعْجِزِينَ فِى ٱلْأَرْضِ وَمَا لَكُم مِّن دُونِ ٱللَّهِ مِن وَلِىٍّ وَلَا نَصِيرٍ

Amharic Translation - Africa Academy31. (ሰዎች ሆይ!) እናንተ በምድር ውስጥ የምትሳኑን (አምላጮች) አይደላችሁም:: ለእናንተም ከአላህ ሌላ ወዳጅም ሆነ ረዳት ምንም የላችሁም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَمِنْ ءَايَٰتِهِ ٱلْجَوَارِ فِى ٱلْبَحْرِ كَٱلْأَعْلَٰمِ

Amharic Translation - Africa Academy32. በባህር ላይ እንደ ጋራዎች ሆነው ተንሻላዮቹ መርከቦችም ከአስደናቂ ምልክቶቹ ናቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِن يَشَأْ يُسْكِنِ ٱلرِّيحَ فَيَظْلَلْنَ رَوَاكِدَ عَلَىٰ ظَهْرِهِۦٓ إِنَّ فِى ذَٰلِكَ لَـَٔايَٰتٍ لِّكُلِّ صَبَّارٍ شَكُورٍ

Amharic Translation - Africa Academy33. ቢፈልግ ንፋሱን የረጋ ያደርገዋል:: ከዚያም መርከቦች በባህሩ ጀርባ ላይ የረጉ ይሆናሉ:: በዚህ ውስጥ በጣም ታጋሽ፤ አመስጋኝ ለሆኑ ሁሉ በእርግጥም ብዙ ተዓምራት አሉ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَوْ يُوبِقْهُنَّ بِمَا كَسَبُوا۟ وَيَعْفُ عَن كَثِيرٍ

Amharic Translation - Africa Academy34. ወይም ተሳፋሪዎች በሰሩት ኃጢአት ምክንያት እነርሱን በባህሩ በማስመጥ ያጠፋቸዋል:: ከብዙ ጥፋቶችም ይቅርታ ያደርጋል።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَيَعْلَمَ ٱلَّذِينَ يُجَٰدِلُونَ فِىٓ ءَايَٰتِنَا مَا لَهُم مِّن مَّحِيصٍ

Amharic Translation - Africa Academy35. ከእነርሱ መካከል እነዚያን በአናቅጻችን የሚከራከሩትን ሰዎች ለማወቅ (ያጠፋቸዋል):: ለእነርሱም ከእርሱ ሌላ ምንም መሸሻ የላቸዉም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَمَآ أُوتِيتُم مِّن شَىْءٍ فَمَتَٰعُ ٱلْحَيَوٰةِ ٱلدُّنْيَا وَمَا عِندَ ٱللَّهِ خَيْرٌ وَأَبْقَىٰ لِلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ وَعَلَىٰ رَبِّهِمْ يَتَوَكَّلُونَ

Amharic Translation - Africa Academy36. (ሰዎች ሆይ!) የተሰጣችሁት ነገር ሁሉ የቅርቢቱ ሕይወት መጠቃቀሚያ ብቻ ነው:: በአላህ ዘንድ ያለው ምንዳ ግን ለእነዚያ በትክክል በእሱ ላመኑትና በጌታቸው ላይ ብቻ ለሚመኩት ሁሉ በላጭና ሁልጊዜ ነዋሪ ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَٱلَّذِينَ يَجْتَنِبُونَ كَبَٰٓئِرَ ٱلْإِثْمِ وَٱلْفَوَٰحِشَ وَإِذَا مَا غَضِبُوا۟ هُمْ يَغْفِرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy37. ለእነዚያም ታላላቅ ሃጢያቶችንና ዝሙትን የሚርቁ፤ በተቆጡም ጊዜ የሚምሩ ለሆኑት፤

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَٱلَّذِينَ ٱسْتَجَابُوا۟ لِرَبِّهِمْ وَأَقَامُوا۟ ٱلصَّلَوٰةَ وَأَمْرُهُمْ شُورَىٰ بَيْنَهُمْ وَمِمَّا رَزَقْنَٰهُمْ يُنفِقُونَ

Amharic Translation - Africa Academy38. ለእነዚያም የጌታቸውን ጥሪ ለተቀበሉት፤ ሶላትንም ላዘወተሩት፤ በነገራቸው ላይም በመካከላቸው መመካከር ልምዳቸው ለሆነው፤ ከሰጠናቸዉም ሲሳይ ለሚለግሱት፤

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَٱلَّذِينَ إِذَآ أَصَابَهُمُ ٱلْبَغْىُ هُمْ يَنتَصِرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy39. ለእነዚያም በደል በደረሰባቸው ጊዜ በመሰሉ የሚመልሱ ለሆኑት (በላጭና ነዋሪ ነው)::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَجَزَٰٓؤُا۟ سَيِّئَةٍ سَيِّئَةٌ مِّثْلُهَا فَمَنْ عَفَا وَأَصْلَحَ فَأَجْرُهُۥ عَلَى ٱللَّهِ إِنَّهُۥ لَا يُحِبُّ ٱلظَّٰلِمِينَ

Amharic Translation - Africa Academy40. የመጥፎ ነገሮች ሁሉ ዋጋው ተመሳሳዩ መጥፎ ነው:: ይቅር ያለና ያሳመረ ሰው ደግሞ ምንዳው በአላህ ላይ ብቻ ነው:: እርሱ በደለኞችን አይወድምና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلَمَنِ ٱنتَصَرَ بَعْدَ ظُلْمِهِۦ فَأُو۟لَٰٓئِكَ مَا عَلَيْهِم مِّن سَبِيلٍ

Amharic Translation - Africa Academy41. እነዚያ ከተበደሉ በኋላ በመሰሉ የተበቀሉ በእነርሱ ላይ ምንም የወቀሳ መንገድ የለባቸዉም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّمَا ٱلسَّبِيلُ عَلَى ٱلَّذِينَ يَظْلِمُونَ ٱلنَّاسَ وَيَبْغُونَ فِى ٱلْأَرْضِ بِغَيْرِ ٱلْحَقِّ أُو۟لَٰٓئِكَ لَهُمْ عَذَابٌ أَلِيمٌ

Amharic Translation - Africa Academy42. የወቀሳ መንገዱ በእነዚያ ሰዎችን በሚበድሉት እና በምድር ውስጥም ያለ ህግ ወሰንን በሚያልፉት ሰዎች ላይ ብቻ ነው:: እነዚያ ለእነርሱ አሳማሚ ቅጣት አለባቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلَمَن صَبَرَ وَغَفَرَ إِنَّ ذَٰلِكَ لَمِنْ عَزْمِ ٱلْأُمُورِ

Amharic Translation - Africa Academy43. የታገሰና ምህረት ያደረገ፤ ይህ ተግባር በእጅጉን ተፈላጊ ከሆኑ ነገሮች አንዱ ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَمَن يُضْلِلِ ٱللَّهُ فَمَا لَهُۥ مِن وَلِىٍّ مِّنۢ بَعْدِهِۦ وَتَرَى ٱلظَّٰلِمِينَ لَمَّا رَأَوُا۟ ٱلْعَذَابَ يَقُولُونَ هَلْ إِلَىٰ مَرَدٍّ مِّن سَبِيلٍ

Amharic Translation - Africa Academy44. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አላህ የሚያጠመውን ሰው ከእርሱ ማጥመም በኋላ ለእርሱ ምንም ወዳጅ የለዉም:: በደለኞችም ቅጣትን ባዩ ጊዜ «ለመመለስ መንገድ አለን?» የሚሉ ሲሆኑ ታያቸዋለህ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَتَرَىٰهُمْ يُعْرَضُونَ عَلَيْهَا خَٰشِعِينَ مِنَ ٱلذُّلِّ يَنظُرُونَ مِن طَرْفٍ خَفِىٍّ وَقَالَ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓا۟ إِنَّ ٱلْخَٰسِرِينَ ٱلَّذِينَ خَسِرُوٓا۟ أَنفُسَهُمْ وَأَهْلِيهِمْ يَوْمَ ٱلْقِيَٰمَةِ أَلَآ إِنَّ ٱلظَّٰلِمِينَ فِى عَذَابٍ مُّقِيمٍ

Amharic Translation - Africa Academy45. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከውርደት የተነሳ ፈሪዎች ሆነው በዓይን ስርቆት ወደ እሳት እያስተዋሉ በእርሷ ላይ የሚቀርቡ ሁነው ታያቸዋለህ:: እነዚያም በአላህ ያመኑት፡- «በእርግጥ ከሳሪዎች ማለት እነዚያ ነፍሶቻቸውንና ቤተሰቦቻቸውን በትንሳኤ ቀን የከሰሩት ናቸው» ይላሉ:: (ሙስሊሞች ሆይ!) አስተዉሉ:: በደለኞች በእርግጥ ዘወታሪ ስቃይ ውስጥ ናቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَمَا كَانَ لَهُم مِّنْ أَوْلِيَآءَ يَنصُرُونَهُم مِّن دُونِ ٱللَّهِ وَمَن يُضْلِلِ ٱللَّهُ فَمَا لَهُۥ مِن سَبِيلٍ

Amharic Translation - Africa Academy46. ለእነርሱም ከአላህ ሌላ የሚረዷቸው ረዳቶች ምንም አልነበሯቸዉም:: አላህ የሚያጠመው ሰው ሁሉ ለእርሱ ወደ እውነት የሚመለስበት ምንም መንገድ የለዉም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ٱسْتَجِيبُوا۟ لِرَبِّكُم مِّن قَبْلِ أَن يَأْتِىَ يَوْمٌ لَّا مَرَدَّ لَهُۥ مِنَ ٱللَّهِ مَا لَكُم مِّن مَّلْجَإٍ يَوْمَئِذٍ وَمَا لَكُم مِّن نَّكِيرٍ

Amharic Translation - Africa Academy47. ያ ከአላህ ከመጣ መላሽ የሌለለው ቀን ከመምጣቱ በፊት ለጌታችሁ ታዘዙ:: በዚያ ቀን ለእናንተ ምንም መጠጊያም ሆነ መቃወም የላችሁም።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَإِنْ أَعْرَضُوا۟ فَمَآ أَرْسَلْنَٰكَ عَلَيْهِمْ حَفِيظًا إِنْ عَلَيْكَ إِلَّا ٱلْبَلَٰغُ وَإِنَّآ إِذَآ أَذَقْنَا ٱلْإِنسَٰنَ مِنَّا رَحْمَةً فَرِحَ بِهَا وَإِن تُصِبْهُمْ سَيِّئَةٌۢ بِمَا قَدَّمَتْ أَيْدِيهِمْ فَإِنَّ ٱلْإِنسَٰنَ كَفُورٌ

Amharic Translation - Africa Academy48. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ቢዞሩም (ወቀሳ የለብህም::) በእነርሱ ላይ ጠባቂ አድረገን አላክንህምና:: ባንተ ላይ ማድረስ እንጂ ሌላ የለብህም:: እኛም ሰውን ከእኛ የሆነን ጸጋ ባቀመስነው ጊዜ በእርሷ ይደሰታል:: እጆቻቸው ባስቀደሙት ኃጢአት ምክንያት መከራ ብትደርስባቸው ደግሞ ተስፋ ይቆርጣሉ:: ሰው በጣም ውለታን ከሓዲ ነውና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

لِّلَّهِ مُلْكُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِ يَخْلُقُ مَا يَشَآءُ يَهَبُ لِمَن يَشَآءُ إِنَٰثًا وَيَهَبُ لِمَن يَشَآءُ ٱلذُّكُورَ

Amharic Translation - Africa Academy49. የሰማያትና የምድር ንግስና የአላህ ብቻ ነው:: የሚፈልገውን ይፈጥራል:: ለሚፈልገው ሴቶችን ልጆች ይሰጣል:: ለሚፈልገዉም ወንዶችን ይሰጣል::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَوْ يُزَوِّجُهُمْ ذُكْرَانًا وَإِنَٰثًا وَيَجْعَلُ مَن يَشَآءُ عَقِيمًا إِنَّهُۥ عَلِيمٌ قَدِيرٌ

Amharic Translation - Africa Academy50. ወይም ወንዶችንና ሴቶችን አድርጎ ያጠናዳቸዋል:: የሚፈልገውንም መካን ያደርገዋል:: እርሱ ሁሉን አዋቂና ሁሉን ቻይ ነውና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَمَا كَانَ لِبَشَرٍ أَن يُكَلِّمَهُ ٱللَّهُ إِلَّا وَحْيًا أَوْ مِن وَرَآئِ حِجَابٍ أَوْ يُرْسِلَ رَسُولًا فَيُوحِىَ بِإِذْنِهِۦ مَا يَشَآءُ إِنَّهُۥ عَلِىٌّ حَكِيمٌ

Amharic Translation - Africa Academy51. ሰውን አላህ በራዕይ ወይም ከግርዶሹ ወዲያ ወይም መልዕከተኛን በመላክና በፈቃዱ የሚፈልገውን ነገር የሚያወርድለት ቢሆን እንጂ በገሀድ ሊያናግረው ተገቢው አይደለም:: እርሱ የበላይና ጥበበኛ ነውና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَكَذَٰلِكَ أَوْحَيْنَآ إِلَيْكَ رُوحًا مِّنْ أَمْرِنَا مَا كُنتَ تَدْرِى مَا ٱلْكِتَٰبُ وَلَا ٱلْإِيمَٰنُ وَلَٰكِن جَعَلْنَٰهُ نُورًا نَّهْدِى بِهِۦ مَن نَّشَآءُ مِنْ عِبَادِنَا وَإِنَّكَ لَتَهْدِىٓ إِلَىٰ صِرَٰطٍ مُّسْتَقِيمٍ

Amharic Translation - Africa Academy52. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ልክ እንደዚሁ ወደ አንተ ከትዕዛዛችን ሲሆን ሂወት የሆነውን (ቁርአን) አወረድነው:: መጽሐፉም ሆነ እምነቱ ምን እንደሆነ የምታውቅ አልነበርክም:: ግን ቁርኣንን ከባሮቻችን የምንሻውን ሰው በእርሱ የምንመራበት ብርሃን አደረግነው:: አንተም ወደ ቀጥተኛው መንገድ በእርግጥ ትመራለህ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

صِرَٰطِ ٱللَّهِ ٱلَّذِى لَهُۥ مَا فِى ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَمَا فِى ٱلْأَرْضِ أَلَآ إِلَى ٱللَّهِ تَصِيرُ ٱلْأُمُورُ

Amharic Translation - Africa Academy53. ወደዚያ በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ የእርሱ ወደ ሆነው ወደ አላህ መንገድ (ትመራለህ):: ሙስሊሞች ሆይ! አስተውሉ:: ነገሮች ሁሉ ወደ አላህ ብቻ ይመለሳሉ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70