caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Az-Zumar፣ አንቀጽ 71

መካ · የወረደበት ቅደም ተከተል 59 · 39:71

وَسِيقَ ٱلَّذِينَ كَفَرُوٓا۟ إِلَىٰ جَهَنَّمَ زُمَرًا حَتَّىٰٓ إِذَا جَآءُوهَا فُتِحَتْ أَبْوَٰبُهَا وَقَالَ لَهُمْ خَزَنَتُهَآ أَلَمْ يَأْتِكُمْ رُسُلٌ مِّنكُمْ يَتْلُونَ عَلَيْكُمْ ءَايَٰتِ رَبِّكُمْ وَيُنذِرُونَكُمْ لِقَآءَ يَوْمِكُمْ هَٰذَا قَالُوا۟ بَلَىٰ وَلَٰكِنْ حَقَّتْ كَلِمَةُ ٱلْعَذَابِ عَلَى ٱلْكَٰفِرِينَ

Amharic Translation - Africa Academy71. እነዚያ በአላህ የካዱትም የተከፋፈሉ ቡድኖች ሆነው ወደ ገሀነም ይነዳሉ፤ በመጧትም ጊዜ በሮቿ ይከፈታሉ:: ወደሷ በመጡም ጊዜ ዘበኞቿ «ከእናንተ የሆኑ የጌታችሁን አናቅጽ በእናንተ ላይ የሚያነቡላችሁ የዚህንም ቀን መገናኘት የሚያስጠነቅቋችሁ መልዕክተኞች አልመጧችሁምን ነበርን?» ይሏቸዋል፤ «የለም መጥተውልናል። ግን የቅጣቲቱ ቃል በከሓዲያን ላይ ተረጋገጠች።» (ይላሉ።)
Amharic Translation - Muhammad Sadiqእነዚያ የካዱትም የተከፋፈሉ ጭፍሮች ኾነው ወደ ገሀነም ይንነዳሉ፡፡ በመጧትም ጊዜ ደጃፎችዋ ይከፈታሉ፡፡ ዘበኞችዋም «ከእናንተ የኾኑ መልክተኞች የጌታችሁን አንቀጾች በናንተ ላይ የሚያነቡላችሁ የዚህንም ቀን መገናኘት የምያስጠነቅቋችሁ መል እክተኞች አልመጣችሁምን ነበርን?" ይሏቸዋል። "የለም መጥተውልናል። ግን የቅጣትቱ ቃል በከሃዲያን ላይ ተረጋገጠች" ይላሉ።
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70