خَلَقَكُم مِّن نَّفْسٍ وَٰحِدَةٍ ثُمَّ جَعَلَ مِنْهَا زَوْجَهَا وَأَنزَلَ لَكُم مِّنَ ٱلْأَنْعَٰمِ ثَمَٰنِيَةَ أَزْوَٰجٍ يَخْلُقُكُمْ فِى بُطُونِ أُمَّهَٰتِكُمْ خَلْقًا مِّنۢ بَعْدِ خَلْقٍ فِى ظُلُمَٰتٍ ثَلَٰثٍ ذَٰلِكُمُ ٱللَّهُ رَبُّكُمْ لَهُ ٱلْمُلْكُ لَآ إِلَٰهَ إِلَّا هُوَ فَأَنَّىٰ تُصْرَفُونَ
Amharic Translation - Africa Academy6. (ሰዎች ሆይ!) ከአንዲት ነፍስ ፈጠራችሁ:: ከዚያም ከእርሷ መቀናጆዋን ፈጠረ:: ለእናንተም ከግመልና ከዳልጋ ከብት፤ ከፍየልና ከበግ ስምንት አይነቶችን (ጥንዶችን) አወረደ:: በእናቶቻችሁ ሆዶች ውስጥ በሶስት ጨለማዎች ውስጥ ከመፍጠር በኋላ ሙሉ መፍጠርን ይፈጥራችኋል፤ ይህን ያደረገው ጌታችሁ አላህ ነው:: ስልጣኑም የእርሱ ብቻ ነው:: ከእርሱ ሌላ ትክክለኛ አምላክ የለም:: ታዲያ ወዴት ትዞራላችሁ::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqከአንዲት ነፍስ ፈጠራችሁ፡፡ ከዚያም ከእርሷ መቀናጆዋን አደረገ፡፡ ለእናንተም ከግመልና ከከብት፣ ከፍየል፣ ከበግ ስምንት ዓይነቶችን (ወንድና ሴት) አወረደ፡፡ በእናቶቻችሁ ሆዶች ውስጥ በሦስት ጨለማዎች ውስጥ ከመፍጠር በኋላ (ሙሉ) መፍጠርን ይፈጠራችኋል፡፡ ይህ ጌታችሁ አላህ ነው፡፡ ስልጣኑ የርሱ ብቻ ነው፡፡ ከእርሱ ሌላ አምላክ የለም፡፡ ታዲያ ወዴት ትዞራላችሁ፡፡