caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Az-Zumar፣ አንቀጽ 7

መካ · የወረደበት ቅደም ተከተል 59 · 39:7

إِن تَكْفُرُوا۟ فَإِنَّ ٱللَّهَ غَنِىٌّ عَنكُمْ وَلَا يَرْضَىٰ لِعِبَادِهِ ٱلْكُفْرَ وَإِن تَشْكُرُوا۟ يَرْضَهُ لَكُمْ وَلَا تَزِرُ وَازِرَةٌ وِزْرَ أُخْرَىٰ ثُمَّ إِلَىٰ رَبِّكُم مَّرْجِعُكُمْ فَيُنَبِّئُكُم بِمَا كُنتُمْ تَعْمَلُونَ إِنَّهُۥ عَلِيمٌۢ بِذَاتِ ٱلصُّدُورِ

Amharic Translation - Africa Academy7. በአላህ ብትክዱ አላህ ከናንተ የተብቃቃ ነው:: ለባሪያዎቹም ክህደትን አይወድም፤ ብታመሰግኑም እርሱን ይወድላችኋል:: ማንኛይቱም ኃጢአትን ተሸካሚ ነፍስ የሌላይቱን ኃጢአት አትሸከምም:: ከዚያም የሁላችሁም መመለሻችሁ ወደ ጌታችሁ ብቻ ነው:: ትሰሩት የነበራችሁትንም ሁሉ ይነግራችኋል:: እርሱ በልቦች ውስጥ ያሉትን ሁሉ አዋቂ ነውና::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqብትክዱ አላህ ከእናንተ የተብቃቃ ነው፡፡ ለባሪያዎቹም ከህደትን አይወድም፡፡ ብታመሰግኑም፤ እርሱን ይወድላችኋል፡፡ ማንኛይቱም ኃጢኣትን ተሸካሚ ነፍስ የሌላይቱን ኃጢኣት አትሸከምም፡፡ ከዚያም መመለሻችሁ ወደ ጌታችሁ ነው፡፡ ትሠሩት የነበራችሁትንም ይነግራችኋል፡፡ እርሱ በልቦች ውስጥ ያሉትን ዐዋቂ ነውና፡፡
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70