أَلَمْ تَرَ أَنَّ ٱللَّهَ أَنزَلَ مِنَ ٱلسَّمَآءِ مَآءً فَسَلَكَهُۥ يَنَٰبِيعَ فِى ٱلْأَرْضِ ثُمَّ يُخْرِجُ بِهِۦ زَرْعًا مُّخْتَلِفًا أَلْوَٰنُهُۥ ثُمَّ يَهِيجُ فَتَرَىٰهُ مُصْفَرًّا ثُمَّ يَجْعَلُهُۥ حُطَٰمًا إِنَّ فِى ذَٰلِكَ لَذِكْرَىٰ لِأُو۟لِى ٱلْأَلْبَٰبِ
Amharic Translation - Africa Academy21. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አላህ ከሰማይ ውሃን እንዳወረደና በምድር ውስጥ ምንጮች አድርጎ እንዳስገባው አላየህምን? ከዚያም በእርሱ ብዙ አይነቶች የሆኑ የተለያዩ አዝመራዎችን ያወጣበታል:: ከዚያም ይደርቃል:: ገርጥቶም ታየዋለህ:: ከዚያ ስብርብር ያደርገዋል፤ በዚህ ውስጥ ለባለ አእምሮዎች ግሳፄ አለበት::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqአላህ ከሰማይ ውሃን እንዳወረደና በምድርም ውስጥ ምንጮች አድርጎ እንዳስገባው አላየህምን? ከዚያም በእርሱ ዓይነቶቹ የተለያዩን አዝመራ ያወጣል፡፡ ከዚያም ይደርቃል፡፡ ገርጥቶም ታየዋለህ፡፡ ከዚያም ስብርብር ያደርገዋል፡፡ በዚህ ውስጥ ለባለ አእምሮዎች ግሣጼ አለበት፡፡