caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Al-Ghaafir غافر

85 አንቀጾች · መካ · የወረደበት ቅደም ተከተል 60

بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ حمٓ

Amharic Translation - Africa Academy1. ሓ፤ ሚይም፤

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

تَنزِيلُ ٱلْكِتَٰبِ مِنَ ٱللَّهِ ٱلْعَزِيزِ ٱلْعَلِيمِ

Amharic Translation - Africa Academy2. የመጽሐፉን መውረድ አሸናፊው አዋቂው ከሆነው ከአላህ ብቻ ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

غَافِرِ ٱلذَّنۢبِ وَقَابِلِ ٱلتَّوْبِ شَدِيدِ ٱلْعِقَابِ ذِى ٱلطَّوْلِ لَآ إِلَٰهَ إِلَّا هُوَ إِلَيْهِ ٱلْمَصِيرُ

Amharic Translation - Africa Academy3. ኃጢአት መሀሪና ጸጸትን ተቀባይ፤ ቅጣተ ብርቱ፤ የልግስና ባለቤት ከሆነው አላህ ብቻ የተወረደ ነው:: ከእርሱ በስተቀር (እውነተኛ) አምላክ የለም:: መመለሻዉም ወደ እርሱ ብቻ ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

مَا يُجَٰدِلُ فِىٓ ءَايَٰتِ ٱللَّهِ إِلَّا ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ فَلَا يَغْرُرْكَ تَقَلُّبُهُمْ فِى ٱلْبِلَٰدِ

Amharic Translation - Africa Academy4. በአላህ አንቀጾች እነዚያ የካዱት ቢኾኑ እንጅ ማንም (በመዝለፍ) አይከራከርም፡፡ በያገሮችም ውስጥ መዘዋወራቸው አይሸንግልህ፡፡

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

كَذَّبَتْ قَبْلَهُمْ قَوْمُ نُوحٍ وَٱلْأَحْزَابُ مِنۢ بَعْدِهِمْ وَهَمَّتْ كُلُّ أُمَّةٍۭ بِرَسُولِهِمْ لِيَأْخُذُوهُ وَجَٰدَلُوا۟ بِٱلْبَٰطِلِ لِيُدْحِضُوا۟ بِهِ ٱلْحَقَّ فَأَخَذْتُهُمْ فَكَيْفَ كَانَ عِقَابِ

Amharic Translation - Africa Academy5. ከእነርሱ በፊት የኑህ ህዝቦች ከኋላቸዉም አህዛቦች አስተባበሉ:: ህዝቦችም ሁሉ መልዕክተኛቸውን ሊይዙ አሰቡ፤ በውሸትም በእርሱ እውነትን ሊያጠፉበት ተከራከሩ:: ያዝኳቸዉም። ታዲያ ቅጣቴ እንዴት ነበር?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَكَذَٰلِكَ حَقَّتْ كَلِمَتُ رَبِّكَ عَلَى ٱلَّذِينَ كَفَرُوٓا۟ أَنَّهُمْ أَصْحَٰبُ ٱلنَّارِ

Amharic Translation - Africa Academy6. ልክ እንደዚሁም የጌታህ ቃል በእነዚያ በአላህ በካዱት ላይ እነርሱ የእሳት ጓዶች ናቸው ማለት ተረጋገጠች::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ٱلَّذِينَ يَحْمِلُونَ ٱلْعَرْشَ وَمَنْ حَوْلَهُۥ يُسَبِّحُونَ بِحَمْدِ رَبِّهِمْ وَيُؤْمِنُونَ بِهِۦ وَيَسْتَغْفِرُونَ لِلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ رَبَّنَا وَسِعْتَ كُلَّ شَىْءٍ رَّحْمَةً وَعِلْمًا فَٱغْفِرْ لِلَّذِينَ تَابُوا۟ وَٱتَّبَعُوا۟ سَبِيلَكَ وَقِهِمْ عَذَابَ ٱلْجَحِيمِ

Amharic Translation - Africa Academy7. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚያ ዐርሹን የሚሸከሙት እነዚያም በዙሪያው ያሉት በጌታቸው ምስጋና ያወድሳሉ፤ በእርሱም ያምናሉ። ለነዚያ ላመኑትም (እንዲህ እያሉ) ምህረትን ይለምኑላቸዋል: «ጌታችን ሆይ! ነገሩን ሁሉ በእዝነትና በእውቀት ከበሃል፤ ስለዚህ ለእነዚያ ለተጸጸቱት መንገድህንም ለተከተሉት ምህረት አድርግላቸው፤ የእሳትንም ቅጣት ጠብቃቸው፤

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

رَبَّنَا وَأَدْخِلْهُمْ جَنَّٰتِ عَدْنٍ ٱلَّتِى وَعَدتَّهُمْ وَمَن صَلَحَ مِنْ ءَابَآئِهِمْ وَأَزْوَٰجِهِمْ وَذُرِّيَّٰتِهِمْ إِنَّكَ أَنتَ ٱلْعَزِيزُ ٱلْحَكِيمُ

Amharic Translation - Africa Academy8. «ጌታችን ሆይ! እነርሱም ከአባቶቻቸውና ከሚስቶቻቸዉም ከዝርዮቻቸዉም የበጀውን ሁሉ እነዚያንም ቃል የገባህላቸውን የመኖሪያ ገነቶች አስገባቸው፤ አንተ አሸናፊው ጥበበኛው ነህና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَقِهِمُ ٱلسَّيِّـَٔاتِ وَمَن تَقِ ٱلسَّيِّـَٔاتِ يَوْمَئِذٍ فَقَدْ رَحِمْتَهُۥ وَذَٰلِكَ هُوَ ٱلْفَوْزُ ٱلْعَظِيمُ

Amharic Translation - Africa Academy9. «ከቅጣቶችም ጠብቃቸው፤ በዚያ ቀንም የምትጠብቀውን በእርግጥ አዘንክለት:: ይህም እርሱ ታላቅ ማግኘት ነው::»

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّ ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ يُنَادَوْنَ لَمَقْتُ ٱللَّهِ أَكْبَرُ مِن مَّقْتِكُمْ أَنفُسَكُمْ إِذْ تُدْعَوْنَ إِلَى ٱلْإِيمَٰنِ فَتَكْفُرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy10. እነዚያ በአላህ የካዱት ሰዎች «ወደ እምነት በምትጠሩና በምትክዱ ጊዜ አላህ (እናንተን) መጥላቱ ነፍሶቻችሁን (ዛሬ) ከመጥላታችሁ የበለጠ ነው።» በማለት ይጠራሉ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَالُوا۟ رَبَّنَآ أَمَتَّنَا ٱثْنَتَيْنِ وَأَحْيَيْتَنَا ٱثْنَتَيْنِ فَٱعْتَرَفْنَا بِذُنُوبِنَا فَهَلْ إِلَىٰ خُرُوجٍ مِّن سَبِيلٍ

Amharic Translation - Africa Academy11. «ጌታችን ሆይ! ሁለትን ሞት አሞትከን:: ሁለትንም ሕይወት ህያው አደረግከን:: በኃጢአቶቻችንም መሰከርን። ታዲያ (ከእሳት) ወደ መውጣት መንገድ አለን?» ይላሉ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ذَٰلِكُم بِأَنَّهُۥٓ إِذَا دُعِىَ ٱللَّهُ وَحْدَهُۥ كَفَرْتُمْ وَإِن يُشْرَكْ بِهِۦ تُؤْمِنُوا۟ فَٱلْحُكْمُ لِلَّهِ ٱلْعَلِىِّ ٱلْكَبِيرِ

Amharic Translation - Africa Academy12. (ከሀዲያን ሆይ!) «ይሃችሁ እነሆ አላህ ብቻውን በተጠራ ጊዜ ስለ ካዳችሁ በእርሱም ተጋሪ ቢደረግ የምታምኑ ስለሆናችሁ ነው:: ስለዚህ ፍርዱ ከፍተኛ ታላቅ ለሆነው አላህ ብቻ ነው::» (ይባላሉ)

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

هُوَ ٱلَّذِى يُرِيكُمْ ءَايَٰتِهِۦ وَيُنَزِّلُ لَكُم مِّنَ ٱلسَّمَآءِ رِزْقًا وَمَا يَتَذَكَّرُ إِلَّا مَن يُنِيبُ

Amharic Translation - Africa Academy13. (ሰዎች ሆይ!) እርሱ ያ ለአምላክነቱ ምልክቶችን የሚያሳያችሁ፤ ለእናንተም ከሰማይ ሲሳይን የሚያወርድላችሁ ነው:: ወደርሱም የሚመለስ ሰው ቢሆን እንጂ ሌላው አይገሰጽም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَٱدْعُوا۟ ٱللَّهَ مُخْلِصِينَ لَهُ ٱلدِّينَ وَلَوْ كَرِهَ ٱلْكَٰفِرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy14. አላህንም ከሓዲያን ቢጠሉም (እንኳ) ሃይማኖትን ለእርሱ አጥሪዎች ሆናችሁ ተገዙ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

رَفِيعُ ٱلدَّرَجَٰتِ ذُو ٱلْعَرْشِ يُلْقِى ٱلرُّوحَ مِنْ أَمْرِهِۦ عَلَىٰ مَن يَشَآءُ مِنْ عِبَادِهِۦ لِيُنذِرَ يَوْمَ ٱلتَّلَاقِ

Amharic Translation - Africa Academy15. እርሱ ደረጃዎችን ከፍ አድራጊ የዐርሹ ባለቤት ነው:: የመገናኛውን ቀን ያስፈራራ ዘንድ ከባሮቹ በሚሻው ሰው ላይ ከትዕዛዙ ራዕይን ያወርዳል::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

يَوْمَ هُم بَٰرِزُونَ لَا يَخْفَىٰ عَلَى ٱللَّهِ مِنْهُمْ شَىْءٌ لِّمَنِ ٱلْمُلْكُ ٱلْيَوْمَ لِلَّهِ ٱلْوَٰحِدِ ٱلْقَهَّارِ

Amharic Translation - Africa Academy16. እነርሱ ከመቃብር በሚወጡበት ቀን ከእነርሱ ምንም ነገር በአላህ ላይ አይደበቅም:: «ንግስናው ዛሬ ለማን ነው?» ይባላል:: «ለአሸናፊው ለአንዱ አላህ ብቻ ነው» ይባላል::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ٱلْيَوْمَ تُجْزَىٰ كُلُّ نَفْسٍۭ بِمَا كَسَبَتْ لَا ظُلْمَ ٱلْيَوْمَ إِنَّ ٱللَّهَ سَرِيعُ ٱلْحِسَابِ

Amharic Translation - Africa Academy17. «ዛሬ ነፍስ ሁሉ በሰራችው ስራ ትመነዳለች፤ ዛሬ በደል የለም:: አላህ በእርግጥ ምርመራው ፈጣን ነው።» ይባላል::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَأَنذِرْهُمْ يَوْمَ ٱلْـَٔازِفَةِ إِذِ ٱلْقُلُوبُ لَدَى ٱلْحَنَاجِرِ كَٰظِمِينَ مَا لِلظَّٰلِمِينَ مِنْ حَمِيمٍ وَلَا شَفِيعٍ يُطَاعُ

Amharic Translation - Africa Academy18. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ቅርቢቱንም የትንሳኤ ቀን ልቦች ጭንቀትን የተሞሉ ሆነው ላንቃዎች ዘንድ የሚደርሱበትን ጊዜ አስጠንቅቃቸው:: ለበዳዮች ምንም ወዳጅና ተሰሚ አማላጅ የላቸዉም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

يَعْلَمُ خَآئِنَةَ ٱلْأَعْيُنِ وَمَا تُخْفِى ٱلصُّدُورُ

Amharic Translation - Africa Academy19. አላህ የዓይኖችን ክዳት ልቦችም የሚደብቁትን ሁሉ ያውቃል::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَٱللَّهُ يَقْضِى بِٱلْحَقِّ وَٱلَّذِينَ يَدْعُونَ مِن دُونِهِۦ لَا يَقْضُونَ بِشَىْءٍ إِنَّ ٱللَّهَ هُوَ ٱلسَّمِيعُ ٱلْبَصِيرُ

Amharic Translation - Africa Academy20. አላህም በእውነት ይፈርዳል:: እነዚያም ከእርሱ ሌላ የሚገዟቸው በምንም አይፈርዱም:: አላህ እርሱ ሰሚው ተመልካቹ ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَوَلَمْ يَسِيرُوا۟ فِى ٱلْأَرْضِ فَيَنظُرُوا۟ كَيْفَ كَانَ عَٰقِبَةُ ٱلَّذِينَ كَانُوا۟ مِن قَبْلِهِمْ كَانُوا۟ هُمْ أَشَدَّ مِنْهُمْ قُوَّةً وَءَاثَارًا فِى ٱلْأَرْضِ فَأَخَذَهُمُ ٱللَّهُ بِذُنُوبِهِمْ وَمَا كَانَ لَهُم مِّنَ ٱللَّهِ مِن وَاقٍ

Amharic Translation - Africa Academy21. የእነዚያን ከእነርሱ በፊት የነበሩትን ህዝቦች ፍፃሜ እንዴት እንደነበረ ይመለከቱ ዘንድ በምድር ላይ አይሄዱምን? በሀይልና በምድር ላይ በተዋቸው ምልክቶች ከእነርሱም ይበልጥ የበረቱ ነበሩ:: አላህም በኃጢአቶቻቸው ያዛቸው። ለእነርሱም ከአላህ ቅጣት ምንም ጠባቂ አልነበራቸዉም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ذَٰلِكَ بِأَنَّهُمْ كَانَت تَّأْتِيهِمْ رُسُلُهُم بِٱلْبَيِّنَٰتِ فَكَفَرُوا۟ فَأَخَذَهُمُ ٱللَّهُ إِنَّهُۥ قَوِىٌّ شَدِيدُ ٱلْعِقَابِ

Amharic Translation - Africa Academy22. ይህ (መያዝ) እነርሱ መልዕክተኞቻቸው በተዓምራት ይመጡባቸው ስለ ነበሩና ስለካዱ ነው:: አላህም ያዛቸው። እርሱ ኃያል፤ ቅጣተ ብርቱ ነውና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلَقَدْ أَرْسَلْنَا مُوسَىٰ بِـَٔايَٰتِنَا وَسُلْطَٰنٍ مُّبِينٍ

Amharic Translation - Africa Academy23. ሙሳንም በተዓምራቶቻችንና በግልጽ ማስረጃ በእርግጥ ላክነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِلَىٰ فِرْعَوْنَ وَهَٰمَٰنَ وَقَٰرُونَ فَقَالُوا۟ سَٰحِرٌ كَذَّابٌ

Amharic Translation - Africa Academy24. ወደ ፈርዖን ወደ ሃማን እና ወደ ቃሩንም ላክነው:: «ድግምተኛ እና ውሸታም ነው» አሉ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَلَمَّا جَآءَهُم بِٱلْحَقِّ مِنْ عِندِنَا قَالُوا۟ ٱقْتُلُوٓا۟ أَبْنَآءَ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ مَعَهُۥ وَٱسْتَحْيُوا۟ نِسَآءَهُمْ وَمَا كَيْدُ ٱلْكَٰفِرِينَ إِلَّا فِى ضَلَٰلٍ

Amharic Translation - Africa Academy25. ከእኛ ዘንድ እውነትን ይዞ በመጣላቸውም ጊዜ: «የእነዚያን ከእርሱ ጋር ያመኑት ሰዎች ወንድ ልጆች ግደሉ፤ ሴቶቻቸውንም አስቀሩ።» አሉ፤ የከሓዲያንም ተንኮል በጥፋት ውስጥ እንጂ ሌላ አይደለም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَقَالَ فِرْعَوْنُ ذَرُونِىٓ أَقْتُلْ مُوسَىٰ وَلْيَدْعُ رَبَّهُۥٓ إِنِّىٓ أَخَافُ أَن يُبَدِّلَ دِينَكُمْ أَوْ أَن يُظْهِرَ فِى ٱلْأَرْضِ ٱلْفَسَادَ

Amharic Translation - Africa Academy26. ፈርዖንም «ተዉኝ፤ ሙሳን ልግደል:: (ያድነው እንደሆነም) ጌታውን ይጥራ:: እኔ ሃይማኖታችሁን ሊለውጥ ወይም በምድር ውስጥ ጥፋትን ሊያሰራጭ እፈራለሁና።» አለ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَقَالَ مُوسَىٰٓ إِنِّى عُذْتُ بِرَبِّى وَرَبِّكُم مِّن كُلِّ مُتَكَبِّرٍ لَّا يُؤْمِنُ بِيَوْمِ ٱلْحِسَابِ

Amharic Translation - Africa Academy27. ሙሳም «እኔ በምርመራው ቀን ከማያምን ትዕቢተኛ ሁሉ በጌታየና በጌታችሁ ተጠበቅሁ።» አለ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَقَالَ رَجُلٌ مُّؤْمِنٌ مِّنْ ءَالِ فِرْعَوْنَ يَكْتُمُ إِيمَٰنَهُۥٓ أَتَقْتُلُونَ رَجُلًا أَن يَقُولَ رَبِّىَ ٱللَّهُ وَقَدْ جَآءَكُم بِٱلْبَيِّنَٰتِ مِن رَّبِّكُمْ وَإِن يَكُ كَٰذِبًا فَعَلَيْهِ كَذِبُهُۥ وَإِن يَكُ صَادِقًا يُصِبْكُم بَعْضُ ٱلَّذِى يَعِدُكُمْ إِنَّ ٱللَّهَ لَا يَهْدِى مَنْ هُوَ مُسْرِفٌ كَذَّابٌ

Amharic Translation - Africa Academy28. ከፈርዖን ቤተሰቦች አንድ እምነቱን የሚደብቅ ምዕመን ሰውም አለ: «ሰውዬው ከጌታችሁ በታዐምራቶች በእርግጥ የመጣላችሁ ሲሆን 'ጌታየ አላህ ነው' ስለሚል ትገድሉታላችሁን? ውሸታምም ቢሆን ውሸቱ በእርሱ ላይ ነው:: እውነተኛ ቢሆን ግን የእዚያ የሚያስፈራራችሁ ከፊሉ ያገኛችኋል:: አላህ እርሱ ያንን ድንበር አላፊና ውሸታም የሆነውን አይመራምና።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

يَٰقَوْمِ لَكُمُ ٱلْمُلْكُ ٱلْيَوْمَ ظَٰهِرِينَ فِى ٱلْأَرْضِ فَمَن يَنصُرُنَا مِنۢ بَأْسِ ٱللَّهِ إِن جَآءَنَا قَالَ فِرْعَوْنُ مَآ أُرِيكُمْ إِلَّا مَآ أَرَىٰ وَمَآ أَهْدِيكُمْ إِلَّا سَبِيلَ ٱلرَّشَادِ

Amharic Translation - Africa Academy29. «ወገኖቼ ሆይ! በምድር ላይ አሸናፊዎች ስትሆኑ ዛሬ መንግስትነት የእናንተ ነው:: ታዲያ ከአላህ ቅጣት ቢመጣብን የሚያድነን ማን ነው?» አለ:: ፈርዖንም «የማየውን እንጂ አላመላክታችሁም፤ ቅኑን መንገድ እንጂ አልመራችሁም።» አላቸው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَقَالَ ٱلَّذِىٓ ءَامَنَ يَٰقَوْمِ إِنِّىٓ أَخَافُ عَلَيْكُم مِّثْلَ يَوْمِ ٱلْأَحْزَابِ

Amharic Translation - Africa Academy30. ያ ያመነው ሰውም አለ፡- «እኔ በእናንተ ላይ የአህዛብን ቀን ብጤ እፈራላችኋለሁ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

مِثْلَ دَأْبِ قَوْمِ نُوحٍ وَعَادٍ وَثَمُودَ وَٱلَّذِينَ مِنۢ بَعْدِهِمْ وَمَا ٱللَّهُ يُرِيدُ ظُلْمًا لِّلْعِبَادِ

Amharic Translation - Africa Academy31. «የ(ነብዩ) ኑህን ህዝቦች የዓድንና የሰሙድም የእነዚያን ከኋላቸው የነበሩትንም ህዝቦች ልማድ ብጤ እፈራላችኋለሁ:: አላህም ለባሮቹ መበደል የሚሻ ጌታ (ሆኖ) አይደለም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَيَٰقَوْمِ إِنِّىٓ أَخَافُ عَلَيْكُمْ يَوْمَ ٱلتَّنَادِ

Amharic Translation - Africa Academy32. «ወገኖቼ ሆይ! እኔ በእናንተ ላይ የመጠራሪያን ቀን እፈራለሁ::»

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

يَوْمَ تُوَلُّونَ مُدْبِرِينَ مَا لَكُم مِّنَ ٱللَّهِ مِنْ عَاصِمٍ وَمَن يُضْلِلِ ٱللَّهُ فَمَا لَهُۥ مِنْ هَادٍ

Amharic Translation - Africa Academy33. ወደ ኋላ ዞራችሁ በምትሸሹበት ቀን፤ ለእናንተ ከአላህ ቅጣት ምንም ጠባቂ የላችሁም፤ አላህም የሚያጠመው ሰው ለእርሱ ምንም አቅኚ የለዉም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلَقَدْ جَآءَكُمْ يُوسُفُ مِن قَبْلُ بِٱلْبَيِّنَٰتِ فَمَا زِلْتُمْ فِى شَكٍّ مِّمَّا جَآءَكُم بِهِۦ حَتَّىٰٓ إِذَا هَلَكَ قُلْتُمْ لَن يَبْعَثَ ٱللَّهُ مِنۢ بَعْدِهِۦ رَسُولًا كَذَٰلِكَ يُضِلُّ ٱللَّهُ مَنْ هُوَ مُسْرِفٌ مُّرْتَابٌ

Amharic Translation - Africa Academy34. ዩሱፍም ከዚህ በፊት ግልጽ ማስረጃዎችን በእርግጥ አመጣላችሁ:: ከዚያ እርሱ ካመጣላችሁ ነገር ከመጠራጠር አልተወገዳችሁም:: በጠፋም ጊዜ «አላህ ከእርሱ በኋላ መልዕክተኛን በጭራሽ አይልክም» አላችሁ፤ አላህ እንደዚሁ ድንበር አላፊ ተጠራጣሪ የሆነን ሰው ያሳስታል።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ٱلَّذِينَ يُجَٰدِلُونَ فِىٓ ءَايَٰتِ ٱللَّهِ بِغَيْرِ سُلْطَٰنٍ أَتَىٰهُمْ كَبُرَ مَقْتًا عِندَ ٱللَّهِ وَعِندَ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ كَذَٰلِكَ يَطْبَعُ ٱللَّهُ عَلَىٰ كُلِّ قَلْبِ مُتَكَبِّرٍ جَبَّارٍ

Amharic Translation - Africa Academy35. እነዚያ የመጣላቸው አስረጅ ሳይኖር በአላህ ታዓምራቶች የሚከራከሩ (ክርክራቸው) አላህ ዘንድና እነዚያም ያመኑት ዘንድ መጠላቱ በጣም ተለቀ:: እንደዚሁ አላህ በኩሩ ጨካኝ ልብ ሁሉ ላይ ያትማል::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَقَالَ فِرْعَوْنُ يَٰهَٰمَٰنُ ٱبْنِ لِى صَرْحًا لَّعَلِّىٓ أَبْلُغُ ٱلْأَسْبَٰبَ

Amharic Translation - Africa Academy36. ፈርዖንም አለ፡- «ሃማን ሆይ! መንገዶችን እደርስ ዘንድ ረዥም ህንፃን ካብልኝ። የሰማያትን መንገዶች እደርስ ዘንድ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَسْبَٰبَ ٱلسَّمَٰوَٰتِ فَأَطَّلِعَ إِلَىٰٓ إِلَٰهِ مُوسَىٰ وَإِنِّى لَأَظُنُّهُۥ كَٰذِبًا وَكَذَٰلِكَ زُيِّنَ لِفِرْعَوْنَ سُوٓءُ عَمَلِهِۦ وَصُدَّ عَنِ ٱلسَّبِيلِ وَمَا كَيْدُ فِرْعَوْنَ إِلَّا فِى تَبَابٍ

Amharic Translation - Africa Academy37. «የሰማያትን መንገዶች እደርስ ዘንድ። ከዚያ ወደ ሙሳ አምላክ እመለከት ዘንድ። እኔም ውሸታም ነው ብዬ እጠረጥረዋለሁ።» አለ:: ልክ እንደዚሁ ለፈርዖን መጥፎ ስራው ተሸለመለት:: ከቅኑ መንገድም ታገደ:: የፈርዖንም ተንኮል በከሳራ ውስጥ እንጂ አይደለም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَقَالَ ٱلَّذِىٓ ءَامَنَ يَٰقَوْمِ ٱتَّبِعُونِ أَهْدِكُمْ سَبِيلَ ٱلرَّشَادِ

Amharic Translation - Africa Academy38. ያ ያመነውም አለ፡- «ወገኖቼ ሆይ! ተከተሉኝ ቀጥታውን መንገድ እመራችኋለሁና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

يَٰقَوْمِ إِنَّمَا هَٰذِهِ ٱلْحَيَوٰةُ ٱلدُّنْيَا مَتَٰعٌ وَإِنَّ ٱلْـَٔاخِرَةَ هِىَ دَارُ ٱلْقَرَارِ

Amharic Translation - Africa Academy39. «ወገኖቼ ሆይ! ይህች ቅርቢቱ ሕይወት የጥቂት ቀናት መጣቀሚያ ብቻ ናት፤ መጨረሻይቱ ዓለም ግን እርሷ ትክክለኛ መርጊያ አገር ናት::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

مَنْ عَمِلَ سَيِّئَةً فَلَا يُجْزَىٰٓ إِلَّا مِثْلَهَا وَمَنْ عَمِلَ صَٰلِحًا مِّن ذَكَرٍ أَوْ أُنثَىٰ وَهُوَ مُؤْمِنٌ فَأُو۟لَٰٓئِكَ يَدْخُلُونَ ٱلْجَنَّةَ يُرْزَقُونَ فِيهَا بِغَيْرِ حِسَابٍ

Amharic Translation - Africa Academy40. «መጥፎን የሰራ ሰው ብጤዋን እንጅ አይመነዳም:: እርሱ ምዕመን ሆኖ ከወንድ ወይም ከሴት በጎ የሰራም እነዚያ ገነትን ይገባሉ:: በእርሷ ውስጥም ያለ ቁጥር ይለገሳሉ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَيَٰقَوْمِ مَا لِىٓ أَدْعُوكُمْ إِلَى ٱلنَّجَوٰةِ وَتَدْعُونَنِىٓ إِلَى ٱلنَّارِ

Amharic Translation - Africa Academy41. «ወገኖቼ ሆይ! ወደ መዳን የምጠራችሁ ስሆን ወደ እሳትም የምትጠሩኝ ስትሆኑ ለእኔ ምን አለኝ!

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

تَدْعُونَنِى لِأَكْفُرَ بِٱللَّهِ وَأُشْرِكَ بِهِۦ مَا لَيْسَ لِى بِهِۦ عِلْمٌ وَأَنَا۠ أَدْعُوكُمْ إِلَى ٱلْعَزِيزِ ٱلْغَفَّٰرِ

Amharic Translation - Africa Academy42. « (እናንተ) በአላህ ልክድና በእርሱም ለእኔ እውቀቱ የሌለኝ ነገር በእርሱ እንዳጋራ ትጠሩኛላችሁ! እኔ አሸናፊና መሀሪ ወደ ሆነው አላህ እጠራችኋለሁ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

لَا جَرَمَ أَنَّمَا تَدْعُونَنِىٓ إِلَيْهِ لَيْسَ لَهُۥ دَعْوَةٌ فِى ٱلدُّنْيَا وَلَا فِى ٱلْـَٔاخِرَةِ وَأَنَّ مَرَدَّنَآ إِلَى ٱللَّهِ وَأَنَّ ٱلْمُسْرِفِينَ هُمْ أَصْحَٰبُ ٱلنَّارِ

Amharic Translation - Africa Academy43. «በእርግጥ ወደ እርሱ የምትጠሩኝ ጣዖት ለእርሱ በቅርቢቱም ሆነ በመጨረሻይቱ ዓለም ተሰሚ ጥሪ የለዉም። መመለሻችንም እርግጥ ወደ አላህ ብቻ ነው:: ወሰን አላፊዎችም እነርሱ የእሳት ጓዶች ናቸው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَسَتَذْكُرُونَ مَآ أَقُولُ لَكُمْ وَأُفَوِّضُ أَمْرِىٓ إِلَى ٱللَّهِ إِنَّ ٱللَّهَ بَصِيرٌۢ بِٱلْعِبَادِ

Amharic Translation - Africa Academy44. «ወደ ፊትም ለእናንተ የምላችሁን ምክር (ቅጣትን በምታዩ ጊዜ) ታስታውሱታላችሁ:: ነገሬንም ሁሉ ወደ አላህ አስጠጋለሁ:: አላህ ባሮቹን ተመልካች ነውና።»

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَوَقَىٰهُ ٱللَّهُ سَيِّـَٔاتِ مَا مَكَرُوا۟ وَحَاقَ بِـَٔالِ فِرْعَوْنَ سُوٓءُ ٱلْعَذَابِ

Amharic Translation - Africa Academy45. ካሴሯቸዉም መጥፎዎች አላህ ጠበቀው፡፡ በፈርዖን ቤተሰቦችም ላይ ክፉ ቅጣት ሰፈረባቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ٱلنَّارُ يُعْرَضُونَ عَلَيْهَا غُدُوًّا وَعَشِيًّا وَيَوْمَ تَقُومُ ٱلسَّاعَةُ أَدْخِلُوٓا۟ ءَالَ فِرْعَوْنَ أَشَدَّ ٱلْعَذَابِ

Amharic Translation - Africa Academy46. እሳት በጧትና በማታ በእርሷ ላይ ይቀርባሉ፡፡ ሰዓቲቱም በምትሆንበት ቀን «የፈርዖንን ቤተሰቦች ብርቱን ቅጣት ገሀነምን አስገቧቸው» ይባላል።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَإِذْ يَتَحَآجُّونَ فِى ٱلنَّارِ فَيَقُولُ ٱلضُّعَفَٰٓؤُا۟ لِلَّذِينَ ٱسْتَكْبَرُوٓا۟ إِنَّا كُنَّا لَكُمْ تَبَعًا فَهَلْ أَنتُم مُّغْنُونَ عَنَّا نَصِيبًا مِّنَ ٱلنَّارِ

Amharic Translation - Africa Academy47. በእሳት ውስጥ የሚከራከሩበትን ጊዜ አስታውስ: ደካማዎቹም ለነዚያ ለኮሩት «እኛ ለእናንተ ተከታዮች ነበርንና እናንተ አሁን ከእሳት ከፊሉን ከእኛ ላይ ገፍታሪዎች ናችሁን?» ይላሉ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَالَ ٱلَّذِينَ ٱسْتَكْبَرُوٓا۟ إِنَّا كُلٌّ فِيهَآ إِنَّ ٱللَّهَ قَدْ حَكَمَ بَيْنَ ٱلْعِبَادِ

Amharic Translation - Africa Academy48. እነዚያም የኮሩት «እኛ ሁላችንም በውስጧ ነን አላህ በባሮቹ መካከል በእርግጥ ፈርዷል» ይላሉ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَقَالَ ٱلَّذِينَ فِى ٱلنَّارِ لِخَزَنَةِ جَهَنَّمَ ٱدْعُوا۟ رَبَّكُمْ يُخَفِّفْ عَنَّا يَوْمًا مِّنَ ٱلْعَذَابِ

Amharic Translation - Africa Academy49. እነዚያም በእሳት ውስጥ ያሉት ለገሀነም ዘበኞች «ጌታችሁን ለምኑልን፤ ከእኛ ላይ ከቅጣቱ ለአንድም ቀን ያቃልልን።» ይላሉ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَالُوٓا۟ أَوَلَمْ تَكُ تَأْتِيكُمْ رُسُلُكُم بِٱلْبَيِّنَٰتِ قَالُوا۟ بَلَىٰ قَالُوا۟ فَٱدْعُوا۟ وَمَا دُعَٰٓؤُا۟ ٱلْكَٰفِرِينَ إِلَّا فِى ضَلَٰلٍ

Amharic Translation - Africa Academy50. ዘበኞቹም «መልዕክተኞቻችሁ በታዐምራቶች ይመጡላችሁ አልነበሩምን?» ይላሉ ከሓዲያንም «እንዴታ መጥተውልናል እንጅ፤ ግን አሰተባበልናቸው።» ይላሉ። «እንግዲያውስ ጸልዩ የከሓዲያንም ጸሎት በከንቱ እንጂ አይደለም።» ይሏቸዋል፡:

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّا لَنَنصُرُ رُسُلَنَا وَٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ فِى ٱلْحَيَوٰةِ ٱلدُّنْيَا وَيَوْمَ يَقُومُ ٱلْأَشْهَٰدُ

Amharic Translation - Africa Academy51. እኛ መልክተኞቻችንን እነዚያንም ያመኑትን በቅርቢቱ ሕይወትም ምስክሮች በሚቆሙበት ቀንም በእርግጥ እንረዳለን።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

يَوْمَ لَا يَنفَعُ ٱلظَّٰلِمِينَ مَعْذِرَتُهُمْ وَلَهُمُ ٱللَّعْنَةُ وَلَهُمْ سُوٓءُ ٱلدَّارِ

Amharic Translation - Africa Academy52. በደለኞችን ምክንያታቸው በማይጠቅማቸው ቀን እንረዳለን። ለነርሱም ርግማን አላቸው:: ለነርሱም መጥፎ አገር አላቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلَقَدْ ءَاتَيْنَا مُوسَى ٱلْهُدَىٰ وَأَوْرَثْنَا بَنِىٓ إِسْرَٰٓءِيلَ ٱلْكِتَٰبَ

Amharic Translation - Africa Academy53. ሙሳንም መምሪያ በእርግጥ ሰጠነው:: የኢስራኢልንም ልጆች መጽሐፍን አወረስናቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

هُدًى وَذِكْرَىٰ لِأُو۟لِى ٱلْأَلْبَٰبِ

Amharic Translation - Africa Academy54. ለባለ አእምሮዎች መሪና ገሳጭ ሲሆን፤

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَٱصْبِرْ إِنَّ وَعْدَ ٱللَّهِ حَقٌّ وَٱسْتَغْفِرْ لِذَنۢبِكَ وَسَبِّحْ بِحَمْدِ رَبِّكَ بِٱلْعَشِىِّ وَٱلْإِبْكَٰرِ

Amharic Translation - Africa Academy55. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ታገስም የአላህ ተስፋ እውነት ነውና፤ ለስህተትህም ምህረትን ለምን፤ ከቀትር በኋላም በማለዳም ጌታህን ከማመስገን ጋር አጥራው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّ ٱلَّذِينَ يُجَٰدِلُونَ فِىٓ ءَايَٰتِ ٱللَّهِ بِغَيْرِ سُلْطَٰنٍ أَتَىٰهُمْ إِن فِى صُدُورِهِمْ إِلَّا كِبْرٌ مَّا هُم بِبَٰلِغِيهِ فَٱسْتَعِذْ بِٱللَّهِ إِنَّهُۥ هُوَ ٱلسَّمِيعُ ٱلْبَصِيرُ

Amharic Translation - Africa Academy56. እነዚያ የመጣላቸው አስረጅ ሳይኖር በአላህ አናቅጽ የሚከራከሩ በልቦቻቸው ውስጥ እነርሱ ደራሾች ያልሆኑት ኩራት ብቻ እንጂ ምንም የለም:: በአላህም ብቻ ተጠበቅ፤ እነሆ እርሱ ሁሉን ሰሚና ሁሉን ተመልካች ነውና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

لَخَلْقُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِ أَكْبَرُ مِنْ خَلْقِ ٱلنَّاسِ وَلَٰكِنَّ أَكْثَرَ ٱلنَّاسِ لَا يَعْلَمُونَ

Amharic Translation - Africa Academy57. ሰማያትንና ምድርን መፍጠር ሰዎችን ከመፍጠር ይልቅ ታላቅ ነው:: ግን አብዛሀኞቹ ሰዎች አያውቁም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَمَا يَسْتَوِى ٱلْأَعْمَىٰ وَٱلْبَصِيرُ وَٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ وَعَمِلُوا۟ ٱلصَّٰلِحَٰتِ وَلَا ٱلْمُسِىٓءُ قَلِيلًا مَّا تَتَذَكَّرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy58. ዐይነ ስዉርና የሚያይ እነዚያም አምነው መልካሞችን የሰሩትና መጥፎ ሰሪው አይስተካከሉም። በጣም ጥቂትን ብቻ ትገስፃላችሁ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّ ٱلسَّاعَةَ لَـَٔاتِيَةٌ لَّا رَيْبَ فِيهَا وَلَٰكِنَّ أَكْثَرَ ٱلنَّاسِ لَا يُؤْمِنُونَ

Amharic Translation - Africa Academy59. ሰዓቲቱ በእርግጥ መጪ ናት:: በእርሷ ጥርጥር የለም:: ግን አብዛሀኞቹ ሰዎች አያምኑም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَقَالَ رَبُّكُمُ ٱدْعُونِىٓ أَسْتَجِبْ لَكُمْ إِنَّ ٱلَّذِينَ يَسْتَكْبِرُونَ عَنْ عِبَادَتِى سَيَدْخُلُونَ جَهَنَّمَ دَاخِرِينَ

Amharic Translation - Africa Academy60. (ባሮቼ ሆይ!) ጌታችሁም አለ: «ለምኑኝ እቀበላችኋለሁና። እነዚያ እኔን ከመገዛት የሚኮሩት ተዋራጆች ሆነው ገሀነም በእርግጥ ይገባሉ።»

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ٱللَّهُ ٱلَّذِى جَعَلَ لَكُمُ ٱلَّيْلَ لِتَسْكُنُوا۟ فِيهِ وَٱلنَّهَارَ مُبْصِرًا إِنَّ ٱللَّهَ لَذُو فَضْلٍ عَلَى ٱلنَّاسِ وَلَٰكِنَّ أَكْثَرَ ٱلنَّاسِ لَا يَشْكُرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy61. አላህ ያ ለእናንተ ሌሊትን በውስጡ ልታርፉበት ጨለማ፤ ቀንኑ ደግሞ ልትሰሩበት የሚያሳይ ብርሃን ያደረገላችሁ ነው:: አላህ በሰዎች ላይ በእርግጥ የታላቅ ችሮታ ባለቤት ነውና:: ግን አብዛሀኞቹ ሰዎች አያመሰግኑም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ذَٰلِكُمُ ٱللَّهُ رَبُّكُمْ خَٰلِقُ كُلِّ شَىْءٍ لَّآ إِلَٰهَ إِلَّا هُوَ فَأَنَّىٰ تُؤْفَكُونَ

Amharic Translation - Africa Academy62. ይሃችሁ ጌታችሁ አላህ ነው:: የነገሩ ሁሉ ፈጣሪ ነው:: ከእርሱ ሌላ አምላክ የለም:: ታዲያ ከእምነት ወዴት ትመለሳላችሁ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

كَذَٰلِكَ يُؤْفَكُ ٱلَّذِينَ كَانُوا۟ بِـَٔايَٰتِ ٱللَّهِ يَجْحَدُونَ

Amharic Translation - Africa Academy63. ልክ እንደዚሁ እነዚያ በአላህ አናቅጽ ይክዱ የነበሩት ከእምነት ይመለሳሉ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ٱللَّهُ ٱلَّذِى جَعَلَ لَكُمُ ٱلْأَرْضَ قَرَارًا وَٱلسَّمَآءَ بِنَآءً وَصَوَّرَكُمْ فَأَحْسَنَ صُوَرَكُمْ وَرَزَقَكُم مِّنَ ٱلطَّيِّبَٰتِ ذَٰلِكُمُ ٱللَّهُ رَبُّكُمْ فَتَبَارَكَ ٱللَّهُ رَبُّ ٱلْعَٰلَمِينَ

Amharic Translation - Africa Academy64. (ሰዎች ሆይ)! አላህ ያ ምድርን መርጊያ ሰማይንም ጣሪያ ያደረገላችሁ ነው፡፡ የቀረፃችሁም ቅርፃችሁንም ያሳመረ፤ ከጣፋጭ ሲሳዮችም የሰጣችሁ ነው:: ይሃችሁ ጌታችሁ አላህ ነው። የዓለማትም ጌታ አላህ ላቀ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

هُوَ ٱلْحَىُّ لَآ إِلَٰهَ إِلَّا هُوَ فَٱدْعُوهُ مُخْلِصِينَ لَهُ ٱلدِّينَ ٱلْحَمْدُ لِلَّهِ رَبِّ ٱلْعَٰلَمِينَ

Amharic Translation - Africa Academy65. እርሱ ብቻ ሁል ጊዜ ህያው ነው:: ከእርሱ ሌላ አምላክ የለም:: ሃይማኖትንም ለርሱ ያጠራችሁ ስትሆኑ «ምስጋና ሁሉ ለዓለማት ጌታ ለሆነው ለአላህ ብቻ ይገባው›› የምትሉ ሆናችሁ ተገዙት::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قُلْ إِنِّى نُهِيتُ أَنْ أَعْبُدَ ٱلَّذِينَ تَدْعُونَ مِن دُونِ ٱللَّهِ لَمَّا جَآءَنِىَ ٱلْبَيِّنَٰتُ مِن رَّبِّى وَأُمِرْتُ أَنْ أُسْلِمَ لِرَبِّ ٱلْعَٰلَمِينَ

Amharic Translation - Africa Academy66. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «እኔ ከጌታዬ አስረጂዎች በመጡልኝ ጊዜ እነዚያን ከአላህ ሌላ የምትገዙዋቸውን እንዳልገዛ ተከልክያለሁ፤ ለዓለማትም ጌታ ብቻም እንድገዛ ታዝዣለሁ።» በላቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

هُوَ ٱلَّذِى خَلَقَكُم مِّن تُرَابٍ ثُمَّ مِن نُّطْفَةٍ ثُمَّ مِنْ عَلَقَةٍ ثُمَّ يُخْرِجُكُمْ طِفْلًا ثُمَّ لِتَبْلُغُوٓا۟ أَشُدَّكُمْ ثُمَّ لِتَكُونُوا۟ شُيُوخًا وَمِنكُم مَّن يُتَوَفَّىٰ مِن قَبْلُ وَلِتَبْلُغُوٓا۟ أَجَلًا مُّسَمًّى وَلَعَلَّكُمْ تَعْقِلُونَ

Amharic Translation - Africa Academy67. (ሰዎች ሆይ!) እርሱ (አላህ) ያ ከዐፈር ከዚያም ከፍትወት ጠብታ ከዚያም ከረጋ ደም የፈጠራችሁ ነው:: ከዚያም ህፃን አድርጎ ያወጣችኋል:: ከዚያም ጥንካሬያችሁን ትደርሱ ዘንድ፤ ከዚያም ሽማግሌዎች ትሆኑ ዘንድ ያቆያችኋል:: ከናንተም ውስጥ ከዚህ በፊት የሚሞት አለ:: ይህንንም ያደረገው ኑራችሁ የተወሰነ ጊዜም ልትደርሱ ታውቁም ዘንድ ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

هُوَ ٱلَّذِى يُحْىِۦ وَيُمِيتُ فَإِذَا قَضَىٰٓ أَمْرًا فَإِنَّمَا يَقُولُ لَهُۥ كُن فَيَكُونُ

Amharic Translation - Africa Academy68. እርሱ (አላህ) ያ ህያው የሚያደርግና የሚያሞትም ነው:: አንዳችን ነገር በሻም ጊዜ ለእርሱ የሚለው ሁን ነው ወዲያዉም ይሆናል::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَلَمْ تَرَ إِلَى ٱلَّذِينَ يُجَٰدِلُونَ فِىٓ ءَايَٰتِ ٱللَّهِ أَنَّىٰ يُصْرَفُونَ

Amharic Translation - Africa Academy69.(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ወደ እነዚያ በአላህ አናቅጽ ወደሚከራከሩት ከእምነት እንዴት እንደሚመለሱ አታይምን?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ٱلَّذِينَ كَذَّبُوا۟ بِٱلْكِتَٰبِ وَبِمَآ أَرْسَلْنَا بِهِۦ رُسُلَنَا فَسَوْفَ يَعْلَمُونَ

Amharic Translation - Africa Academy70. ወደ እነዚያ በመጽሐፉ በዚያም መልዕክተኞቻችንን በእርሱ በላክንበት ወዳስተባበሉበት አታይምን? ወደፊትም ያውቃሉ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِذِ ٱلْأَغْلَٰلُ فِىٓ أَعْنَٰقِهِمْ وَٱلسَّلَٰسِلُ يُسْحَبُونَ

Amharic Translation - Africa Academy71. እንዘዝላዎቹና ሰንሰለቶቹ በአንገቶቻቸው ላይ በተደረጉ ጊዜ (በእርሷ) ይጎተታሉ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فِى ٱلْحَمِيمِ ثُمَّ فِى ٱلنَّارِ يُسْجَرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy72. በገሀነም ውስጥ ይጎተታሉ፤ ከዚያም በእሳት ውስጥ ይማገዳሉ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ثُمَّ قِيلَ لَهُمْ أَيْنَ مَا كُنتُمْ تُشْرِكُونَ

Amharic Translation - Africa Academy73. ከዚያም ለእነርሱ ይባላሉ፡- «(በአላህ) ታጋሯቸው የነበራችሁት የታሉ?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

مِن دُونِ ٱللَّهِ قَالُوا۟ ضَلُّوا۟ عَنَّا بَل لَّمْ نَكُن نَّدْعُوا۟ مِن قَبْلُ شَيْـًٔا كَذَٰلِكَ يُضِلُّ ٱللَّهُ ٱلْكَٰفِرِينَ

Amharic Translation - Africa Academy74. ከአላህ ሌላ የምታጋሩዋቸው (የት አሉ)?» «ከእኛ ተሰወሩብን፤ ከቶ ከዚህ በፊት ምንም የምንገዛ አልነበርንም» ይላሉ:: ልክ እንደዚሁ አላህ ካሐዲያንን ያሳስታል::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ذَٰلِكُم بِمَا كُنتُمْ تَفْرَحُونَ فِى ٱلْأَرْضِ بِغَيْرِ ٱلْحَقِّ وَبِمَا كُنتُمْ تَمْرَحُونَ

Amharic Translation - Africa Academy75. «ይህ (ቅጣታችሁ) ያላአግባብ በምድር ውስጥ ትደሰቱ በነበራችሁትና ትንበጣረሩ በነበራችሁት ነው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ٱدْخُلُوٓا۟ أَبْوَٰبَ جَهَنَّمَ خَٰلِدِينَ فِيهَا فَبِئْسَ مَثْوَى ٱلْمُتَكَبِّرِينَ

Amharic Translation - Africa Academy76. የገሀነምን በሮች ውስጧ ዘወታሪዎች ስትሆኑ ግቡ።» (ይባላሉ)። የትዕቢተኞችም መኖሪያ (ገሀነም) ምን ትከፋ!

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَٱصْبِرْ إِنَّ وَعْدَ ٱللَّهِ حَقٌّ فَإِمَّا نُرِيَنَّكَ بَعْضَ ٱلَّذِى نَعِدُهُمْ أَوْ نَتَوَفَّيَنَّكَ فَإِلَيْنَا يُرْجَعُونَ

Amharic Translation - Africa Academy77. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ታገስም:: የአላህ ቀጠሮ እውነት ነውና፤ የዚያንም የምናስፈራራቸውን ከፊሉን በህይወትህ ብናሳይህ መልካም ነው:: ወይም ሳናሳይህ ብንገድልህ ወደ እኛ ይመለሳሉ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلَقَدْ أَرْسَلْنَا رُسُلًا مِّن قَبْلِكَ مِنْهُم مَّن قَصَصْنَا عَلَيْكَ وَمِنْهُم مَّن لَّمْ نَقْصُصْ عَلَيْكَ وَمَا كَانَ لِرَسُولٍ أَن يَأْتِىَ بِـَٔايَةٍ إِلَّا بِإِذْنِ ٱللَّهِ فَإِذَا جَآءَ أَمْرُ ٱللَّهِ قُضِىَ بِٱلْحَقِّ وَخَسِرَ هُنَالِكَ ٱلْمُبْطِلُونَ

Amharic Translation - Africa Academy78. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ካንተ በፊትም መልዕክተኞችን በእርግጥ ልከናል። ከእነርሱ ባንተ ላይ የተረክንልህ አለ:: ከእነርሱም ባንተ ላይ ያልተረክነውም አለ:: ለማንኛዉም መልዕክተኛ በአላህ ፈቃድ ካልሆነ በስተቀር ተዓምርን ሊያመጣ አይገባዉም:: የአላህም ትዕዛዝ በመጣ ጊዜ በእውነት ይፈረዳል:: እዚያ ዘንድም አጥፊዎች ይከስራሉ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ٱللَّهُ ٱلَّذِى جَعَلَ لَكُمُ ٱلْأَنْعَٰمَ لِتَرْكَبُوا۟ مِنْهَا وَمِنْهَا تَأْكُلُونَ

Amharic Translation - Africa Academy79. አላህ ያ ለእናንተ ግመልን ከብትንና ፍየልን ከእርሷ ከፊሏን ልትጋልቡ የፈጠረላችሁ ነውና:: ከእርሷም ትበላላችሁ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلَكُمْ فِيهَا مَنَٰفِعُ وَلِتَبْلُغُوا۟ عَلَيْهَا حَاجَةً فِى صُدُورِكُمْ وَعَلَيْهَا وَعَلَى ٱلْفُلْكِ تُحْمَلُونَ

Amharic Translation - Africa Academy80. ለእናተም በርሷ ውስጥ ጥቅሞች አሏችሁ:: በእርሷም ላይ ዕቃን በመጫን በልቦቻችሁ ያሰባችሁትን ጉዳይ ትደርሱ ዘንድ ፈጠረላችሁ። በእርሷም ላይ በመርከቦችም ላይ ትሳፈራላችሁ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَيُرِيكُمْ ءَايَٰتِهِۦ فَأَىَّ ءَايَٰتِ ٱللَّهِ تُنكِرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy81. ተዓምራትንም ያሳያችኋል:: ታዲያ ከአላህ ተዓምራት መካከል የትኛውን ትክዳላችሁ?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَفَلَمْ يَسِيرُوا۟ فِى ٱلْأَرْضِ فَيَنظُرُوا۟ كَيْفَ كَانَ عَٰقِبَةُ ٱلَّذِينَ مِن قَبْلِهِمْ كَانُوٓا۟ أَكْثَرَ مِنْهُمْ وَأَشَدَّ قُوَّةً وَءَاثَارًا فِى ٱلْأَرْضِ فَمَآ أَغْنَىٰ عَنْهُم مَّا كَانُوا۟ يَكْسِبُونَ

Amharic Translation - Africa Academy82. የእነዚያም ከእነርሱ በፊት የነበሩትን ህዝቦች ፍፃሜ እንዴት እንደነበር ይመለከቱ ዘንድ በምድር ላይ አይሄዱምን ? ከእነርሱ ይበልጥ ብዙዎች በኃይልና በምድር ላይ በተዋቸው ምልክቶችም በጣም ብርቱዎች ነበሩ:: ያም ይሰሩት የነበሩት ለእነርሱ ምንም አልጠቀማቸዉም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَلَمَّا جَآءَتْهُمْ رُسُلُهُم بِٱلْبَيِّنَٰتِ فَرِحُوا۟ بِمَا عِندَهُم مِّنَ ٱلْعِلْمِ وَحَاقَ بِهِم مَّا كَانُوا۟ بِهِۦ يَسْتَهْزِءُونَ

Amharic Translation - Africa Academy83. መልዕክተኞቻቸዉም ተዓምራትን ባመጡላችሁ ጊዜ እነርሱ ዘንድ ባለው ዕውቀት ተደሰቱ:: በእርሱ ይሳለቁበት የነበሩት ቅጣትም በእነርሱ ላይ ሰፈረባቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَلَمَّا رَأَوْا۟ بَأْسَنَا قَالُوٓا۟ ءَامَنَّا بِٱللَّهِ وَحْدَهُۥ وَكَفَرْنَا بِمَا كُنَّا بِهِۦ مُشْرِكِينَ

Amharic Translation - Africa Academy84. ብርቱ ቅጣታችንንም ባዩ ጊዜ «በአላህ አንድነት አምነናል በእርሱም እናጋራ በነበርነው ጣዖታት ክደናል» አሉ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَلَمْ يَكُ يَنفَعُهُمْ إِيمَٰنُهُمْ لَمَّا رَأَوْا۟ بَأْسَنَا سُنَّتَ ٱللَّهِ ٱلَّتِى قَدْ خَلَتْ فِى عِبَادِهِۦ وَخَسِرَ هُنَالِكَ ٱلْكَٰفِرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy85. ብርቱ ቅጣታችንን ባዩ ጊዜ ማመናቸዉም የሚጠቅማቸው አልነበረም:: የአላህን ደንብ ያችን በባሮቹ ውስጥ ያለፈችውን ተጠንቀቁ:: በዚያ ጊዜም ከሓዲያን ከሰሩ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70