وَتَرَى ٱلْمَلَٰٓئِكَةَ حَآفِّينَ مِنْ حَوْلِ ٱلْعَرْشِ يُسَبِّحُونَ بِحَمْدِ رَبِّهِمْ وَقُضِىَ بَيْنَهُم بِٱلْحَقِّ وَقِيلَ ٱلْحَمْدُ لِلَّهِ رَبِّ ٱلْعَٰلَمِينَ
Amharic Translation - Africa Academy75. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) መላዕክትንም በጌታቸው ምስጋና ቀላቅለው የሚያጠሩ ሲሆኑ በአርሹ ዙሪያ ከባቢዎች ሆነው ታያለህ፡፡ በመካከላቸውም እውነት ይፈረዳል። ይባላልም፤ «ምስጋና ሁሉ ለዓለማት ጌታ ለሆነው ለአላህ ብቻ ይገባው።»
Amharic Translation - Muhammad Sadiqመላእክትንም በጌታቸው ምስጋና ቀላቅለው የሚያጠሩ ሲኾኑ በዐርሹ ዙሪያ ከባቢዎች ኾነው ታያለህ፡፡ በመካከላቸው በእውነት ይፈረዳል፡፡ ይባላልም፤ «ምስጋና ለአላህ ለዓለማት ጌታ ይገባው፡፡»