ضَرَبَ ٱللَّهُ مَثَلًا رَّجُلًا فِيهِ شُرَكَآءُ مُتَشَٰكِسُونَ وَرَجُلًا سَلَمًا لِّرَجُلٍ هَلْ يَسْتَوِيَانِ مَثَلًا ٱلْحَمْدُ لِلَّهِ بَلْ أَكْثَرُهُمْ لَا يَعْلَمُونَ
Amharic Translation - Africa Academy29. አላህ በእርሱ ተጨቃጫቂዎች የሆኑ ተጋሪዎች ያሉትን ባሪያና ለአንድ ሰው ብቻ ንጹህ የሆነን ባሪያ ለሚያጋራና በአንድነት ለሚያምን ሰው ምሳሌ አደረገ። በምሳሌ ይስተካካላሉን? ምስጋና ሁሉ ለአላህ ይገባው:: በእውነቱ አብዛኞቻቸው አያውቁም::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqአላህ በእርሱ ተጨቃጫቂዎች የኾኑ ተጋሪዎች ያሉትን ባሪያና ለአንድ ሰው ብቻ ንጹሕ የኾነን ባሪያ (ለሚያጋራና ባንድነቱ ለሚያምን ሰው) ምሳሌ አደረገ፡፡ በምሳሌ ይስተካከላሉን? ምስጋና ለአላህ ይገባው፡፡ በእውነቱ አብዛኞቻቸው አያውቁም፡፡