وَلَئِن سَأَلْتَهُم مَّنْ خَلَقَ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضَ لَيَقُولُنَّ ٱللَّهُ قُلْ أَفَرَءَيْتُم مَّا تَدْعُونَ مِن دُونِ ٱللَّهِ إِنْ أَرَادَنِىَ ٱللَّهُ بِضُرٍّ هَلْ هُنَّ كَٰشِفَٰتُ ضُرِّهِۦٓ أَوْ أَرَادَنِى بِرَحْمَةٍ هَلْ هُنَّ مُمْسِكَٰتُ رَحْمَتِهِۦ قُلْ حَسْبِىَ ٱللَّهُ عَلَيْهِ يَتَوَكَّلُ ٱلْمُتَوَكِّلُونَ
Amharic Translation - Africa Academy38. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ሰማያትንና ምድርን የፈጠረ ማን እንደሆነ ብትጠይቃቸው «አላህ ነው» ይሉሃል:: «ከአላህ ሌላ የምትገዟቸውን ጣዖታት አያችሁን? እስቲ ንገሩኝ:: አላህ በጉዳት ቢፈልገኝ እነርሱ ጉዳቱን ገላጮች ናቸውን? ወይስ በችሮታው ቢፈልገኝ እነርሱም ችሮታውን አጋጆች ናቸውን?» በላቸው:: «አላህ በቂዬ ነው:: በእርሱ ላይ ተመኪዎች ይመካሉ» በል::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqሰማያትንና ምድርን የፈጠረ ማን እንደ ኾነ ብትጠይቃቸው «አላህ ነው» ይሉሃል፡፡ «ከአላህ ሌላ የምትግገዟቸውን (ጣዖታት) አያችሁን? (ንገሩኝ) አላህ በጉዳት ቢፈልገኝ እነርሱ ጉዳቱን ገላጮች ናቸውን? ወይስ በችሮታው ቢፈቅደኝ እነርሱ ችሮታውን አጋጆች ናቸውን?» በላቸው፡፡ «አላህ በቂዬ ነው፡፡ በእርሱ ላይ ተመኪዎች ይመካሉ» በል፡፡