caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Al-Ahzaab፣ አንቀጽ 50

መዲና · የወረደበት ቅደም ተከተል 90 · 33:50

يَٰٓأَيُّهَا ٱلنَّبِىُّ إِنَّآ أَحْلَلْنَا لَكَ أَزْوَٰجَكَ ٱلَّٰتِىٓ ءَاتَيْتَ أُجُورَهُنَّ وَمَا مَلَكَتْ يَمِينُكَ مِمَّآ أَفَآءَ ٱللَّهُ عَلَيْكَ وَبَنَاتِ عَمِّكَ وَبَنَاتِ عَمَّٰتِكَ وَبَنَاتِ خَالِكَ وَبَنَاتِ خَٰلَٰتِكَ ٱلَّٰتِى هَاجَرْنَ مَعَكَ وَٱمْرَأَةً مُّؤْمِنَةً إِن وَهَبَتْ نَفْسَهَا لِلنَّبِىِّ إِنْ أَرَادَ ٱلنَّبِىُّ أَن يَسْتَنكِحَهَا خَالِصَةً لَّكَ مِن دُونِ ٱلْمُؤْمِنِينَ قَدْ عَلِمْنَا مَا فَرَضْنَا عَلَيْهِمْ فِىٓ أَزْوَٰجِهِمْ وَمَا مَلَكَتْ أَيْمَٰنُهُمْ لِكَيْلَا يَكُونَ عَلَيْكَ حَرَجٌ وَكَانَ ٱللَّهُ غَفُورًا رَّحِيمًا

Amharic Translation - Africa Academy50. አንተ ነብይ ሆይ! እነዚያን መህሮቻቸውን የሰጠሃቸውን ሚስቶችህን፤ አላህ ባንተ ላይ ከመለሰልህም ሴቶች መካከል እነዚያን እጅህ የጨበጠቻቸውን ምርኮኞች ሴቶች፤ እነዚያን ካንተ ጋር የተሰደዱትን የአጎቶችህንና፤ የአክስቶችህን ሴት ልጆች (እንደዚሁም) የእናትህ ወንድም ሴት ልጆችና የእናትህ እህት ሴት ልጆች ማግባትን ላንተ ፈቅደንልሃል:: ማንኛዋም በአላህ ያመነች ሴት ራሷን ለነብዩ ብትሰጥ ነብዩ ሊያገባት የፈለገ እንደ ሆነ ከአማኞች ሌላ ላንተ ብቻ የተሰጠ መብት ሲሆን ፈቀድንልህ:: በአማኞች ላይ በሚስቶቻቸውና እጆቻቸው በጨበጧቸው ባሮች ነገር ግዴታ ያደረግንባቸውን በእርግጥ አውቀናል:: ባንተ ላይ ችግር እንዳይኖር ያለፉትን ፈቀድንልህ:: አላህ መሃሪና አዛኝ ነውና::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqአንተ ነቢዩ ሆይ! እኛ እነዚያን መህሮቻቸውን የሰጠሃቸውን ሚስቶችህን፣ አላህ ባንተ ላይ ከመለሰልህም እነዚያን እጅህ የጨበጠቻቸውን ምርኮኞች፣ እነዚያንም ከአንተ ጋር የተሰደዱትን የአጎትህን ሴቶች ልጆች፣ የአክስቶችህንም ሴቶች ልጆች፣ የየሹማህንም ሴቶች ልጆች፣ የየሹሜዎችህንም ሴቶች ልጆች (ማግባትን) ለአንተ ፈቅደንልሃል፡፡ የአመነችንም ሴት ነፍሷን (ራሷን) ለነቢዩ ብትሰጥ ነቢዩ ሊያገባት የፈለገ እንደ ኾነ ከምእምናን ሌላ ላንተ ብቻ የጠራች ስትኾን (ፈቀድንልህ)፡፡ በእነርሱ (በምእምናን) ላይ በሚስቶቻቸውና እጆቻቸው በጨበጧቸው (ባሮች ነገር) ግዴታ ያደረግንባቸውን በእርግጥ ዐውቀናል፡፡ ባንተ ላይ ችግር እንዳይኖር (ያለፉትን ፈቀድንልህ)፡፡ አላህም መሓሪ አዛኝ ነው፡፡
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70