ሱረቱ Saba سبإ
54 አንቀጾች · መካ · የወረደበት ቅደም ተከተል 58
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ ٱلْحَمْدُ لِلَّهِ ٱلَّذِى لَهُۥ مَا فِى ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَمَا فِى ٱلْأَرْضِ وَلَهُ ٱلْحَمْدُ فِى ٱلْـَٔاخِرَةِ وَهُوَ ٱلْحَكِيمُ ٱلْخَبِيرُ
Amharic Translation - Africa Academy1. ምስጋና ሁሉ ለዚያ በሰማያትም ያለው በምድርም ያለው ሁሉ የእርሱ ለሆነው ለአላህ ብቻ ይገባው:: በመጨረሻይቱም ዓለም ምስጋና ሁሉ ለእርሱ ብቻ ነው:: እርሱም ጥበበኛና ውስጠ አዋቂው ነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
يَعْلَمُ مَا يَلِجُ فِى ٱلْأَرْضِ وَمَا يَخْرُجُ مِنْهَا وَمَا يَنزِلُ مِنَ ٱلسَّمَآءِ وَمَا يَعْرُجُ فِيهَا وَهُوَ ٱلرَّحِيمُ ٱلْغَفُورُ
Amharic Translation - Africa Academy2. አላህ በምድር ውስጥ የሚገባውን ሁሉ ከእርሷ የሚወጣውንም ከሰማይም የሚወርደውን በእርሷ ውስጥ የሚያርገውንም ሁሉ ያውቃል:: እርሱም አዛኝና መሃሪ ነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَقَالَ ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ لَا تَأْتِينَا ٱلسَّاعَةُ قُلْ بَلَىٰ وَرَبِّى لَتَأْتِيَنَّكُمْ عَٰلِمِ ٱلْغَيْبِ لَا يَعْزُبُ عَنْهُ مِثْقَالُ ذَرَّةٍ فِى ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَلَا فِى ٱلْأَرْضِ وَلَآ أَصْغَرُ مِن ذَٰلِكَ وَلَآ أَكْبَرُ إِلَّا فِى كِتَٰبٍ مُّبِينٍ
Amharic Translation - Africa Academy3. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚያ በአላህ የካዱትም ሰዎች «ሰዓቲቱ አትመጣብንም» አሉ፡ «ጉዳዩ እንዳሰባችሁት አይደለም። ሩቁን ሁሉ አዋቂ በሆነው ጌታዬ እምላለሁ:: በእርግጥ ትመጣባችኋለች:: የብናኝ ክብደት ያክል እንኳ በሰማያትና በምድር ውስጥ ከእሱ አይሰወርም አይርቅም:: ከዚህ ያነሰም ሆነ የበለጠ የለም በግልጹ መጽሐፍ ውስጥ የተመዘገበ ቢሆን እንጂ::» በላቸው
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
لِّيَجْزِىَ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ وَعَمِلُوا۟ ٱلصَّٰلِحَٰتِ أُو۟لَٰٓئِكَ لَهُم مَّغْفِرَةٌ وَرِزْقٌ كَرِيمٌ
Amharic Translation - Africa Academy4. እነዚያን ያመኑትንና መልካም የሰሩትን ሊመነዳ ሰዓቲቱ ትመጣባችኋለች:: እነዚያ ለእነርሱ ምህረትና የከበረ ሲሳይ አለላቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَٱلَّذِينَ سَعَوْ فِىٓ ءَايَٰتِنَا مُعَٰجِزِينَ أُو۟لَٰٓئِكَ لَهُمْ عَذَابٌ مِّن رِّجْزٍ أَلِيمٌ
Amharic Translation - Africa Academy5. እነዚያም የሚያመልጡ መስሏቸው አናቅጻችንን ለማፍረስ የጣሩ እነዚያ ለእነርሱ ከመጥፎ ቅጣት የሆነ አሳማሚ ስቃይ አለባቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَيَرَى ٱلَّذِينَ أُوتُوا۟ ٱلْعِلْمَ ٱلَّذِىٓ أُنزِلَ إِلَيْكَ مِن رَّبِّكَ هُوَ ٱلْحَقَّ وَيَهْدِىٓ إِلَىٰ صِرَٰطِ ٱلْعَزِيزِ ٱلْحَمِيدِ
Amharic Translation - Africa Academy6. እነዚያም እውቀትን የተሰጡት ያንን ከጌታህ ወደ አንተ የተወረደውን እውነትና አሸናፊ ምስጉን ወደ ሆነው የአላህ መንገድ የሚመራ መሆኑን ያውቃሉ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَقَالَ ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ هَلْ نَدُلُّكُمْ عَلَىٰ رَجُلٍ يُنَبِّئُكُمْ إِذَا مُزِّقْتُمْ كُلَّ مُمَزَّقٍ إِنَّكُمْ لَفِى خَلْقٍ جَدِيدٍ
Amharic Translation - Africa Academy7. እነዚያም በአላህ የካዱት አሉ: «(ሙታችሁ) ሙሉ መበጣጠስን በተበጣጠሳችሁ ጊዜ በአዲስ መፈጠር ውስጥ ትሆናላችሁ ብሎ የሚነግራችሁን ሰው እናሳያችሁን?
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَفْتَرَىٰ عَلَى ٱللَّهِ كَذِبًا أَم بِهِۦ جِنَّةٌۢ بَلِ ٱلَّذِينَ لَا يُؤْمِنُونَ بِٱلْـَٔاخِرَةِ فِى ٱلْعَذَابِ وَٱلضَّلَٰلِ ٱلْبَعِيدِ
Amharic Translation - Africa Academy8. «በአላህ ላይ ውሸትን ቀጠፈን? ወይስ በእርሱ እብደት አለበት?» አሉ:: እንዳሉት አይደለም። እነዚያ በመጨረሻይቱ ዓለም የማያምኑት በእርሷ በቅጣት ውስጥ የሚሆኑና አሁንም በራቀ ስህተት ውስጥ ናቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَفَلَمْ يَرَوْا۟ إِلَىٰ مَا بَيْنَ أَيْدِيهِمْ وَمَا خَلْفَهُم مِّنَ ٱلسَّمَآءِ وَٱلْأَرْضِ إِن نَّشَأْ نَخْسِفْ بِهِمُ ٱلْأَرْضَ أَوْ نُسْقِطْ عَلَيْهِمْ كِسَفًا مِّنَ ٱلسَّمَآءِ إِنَّ فِى ذَٰلِكَ لَـَٔايَةً لِّكُلِّ عَبْدٍ مُّنِيبٍ
Amharic Translation - Africa Academy9. ከሰማይና ከምድር በፊታቸውና በኋላቸው ወደ አለው ሁሉ አይመለከቱምን? ብንሻ እኮ በእነርሱ ምድርን እንደረምስባቸዋለን :: ወይም በእነርሱ ላይ ከሰማይ ቁራጭን እንጥልባቸዋለን:: በዚህ ውስጥ ወደ ጌታው ተመላሽ ለሆነ ባሪያ ሁሉ ታላቅ ምልክት አለበት፡
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلَقَدْ ءَاتَيْنَا دَاوُۥدَ مِنَّا فَضْلًا يَٰجِبَالُ أَوِّبِى مَعَهُۥ وَٱلطَّيْرَ وَأَلَنَّا لَهُ ٱلْحَدِيدَ
Amharic Translation - Africa Academy10. ለዳውድም ከእኛ የሆነን ችሮታ በእርግጥ ሰጠነው:: (አልንም) ተራራዎች ሆይ! ከእሱ ጋር ውዳሴን መላልሱ:: በራሪዎችንም (ገራንለት)። ብረትንም ለእሱ አለዘብንለት::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَنِ ٱعْمَلْ سَٰبِغَٰتٍ وَقَدِّرْ فِى ٱلسَّرْدِ وَٱعْمَلُوا۟ صَٰلِحًا إِنِّى بِمَا تَعْمَلُونَ بَصِيرٌ
Amharic Translation - Africa Academy11. ሰፋፊዎችን ጥሩሮዎች ስራ:: በአሰራርዋም መጥን:: መልካምንም ስራ ስሩ:: እኔ የምትሰሩትን ነገር ሁሉ ተመልካች ነኝና (አልነው)::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلِسُلَيْمَٰنَ ٱلرِّيحَ غُدُوُّهَا شَهْرٌ وَرَوَاحُهَا شَهْرٌ وَأَسَلْنَا لَهُۥ عَيْنَ ٱلْقِطْرِ وَمِنَ ٱلْجِنِّ مَن يَعْمَلُ بَيْنَ يَدَيْهِ بِإِذْنِ رَبِّهِۦ وَمَن يَزِغْ مِنْهُمْ عَنْ أَمْرِنَا نُذِقْهُ مِنْ عَذَابِ ٱلسَّعِيرِ
Amharic Translation - Africa Academy12. ለሱለይማንም ንፋስን የቀትር በፊት ጉዞዋ የወር መንገድ፤ የቀትር በኋላ ጉዞዋም የወር መንገድ ሲሆን ገራንለት:: የነሀስንም ምንጭ ለእርሱ አፈሰስንለት:: ከአጋንንቶችም በጌታው ፈቃድ በፊቱ የሚሰሩትን (አደረግንለት):: ከእነርሱም ውስጥ ከትእዛዛችን ዝንፍ የሚል ከነዳጅ እሳት ቅጣት እናቀምሰዋለን::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
يَعْمَلُونَ لَهُۥ مَا يَشَآءُ مِن مَّحَٰرِيبَ وَتَمَٰثِيلَ وَجِفَانٍ كَٱلْجَوَابِ وَقُدُورٍ رَّاسِيَٰتٍ ٱعْمَلُوٓا۟ ءَالَ دَاوُۥدَ شُكْرًا وَقَلِيلٌ مِّنْ عِبَادِىَ ٱلشَّكُورُ
Amharic Translation - Africa Academy13. ከምኩራቦች፤ ከምስሎችም እንደ ገንዳ ከሆነ ገበታዎችም፤ ከተደላደለ ታላላቅ ድስቶችም የሚሻውን ሁሉ ይሰሩለታል፣ (አልናቸዉም:) «የዳውድ ቤተሰቦች ሆይ! በጣም አመስጋኞች ሆናችሁ ለጌታችሁ ስሩ::» ከባሮቼ ውስጥ አመስጋኞቹ ጥቂቶች ናቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَلَمَّا قَضَيْنَا عَلَيْهِ ٱلْمَوْتَ مَا دَلَّهُمْ عَلَىٰ مَوْتِهِۦٓ إِلَّا دَآبَّةُ ٱلْأَرْضِ تَأْكُلُ مِنسَأَتَهُۥ فَلَمَّا خَرَّ تَبَيَّنَتِ ٱلْجِنُّ أَن لَّوْ كَانُوا۟ يَعْلَمُونَ ٱلْغَيْبَ مَا لَبِثُوا۟ فِى ٱلْعَذَابِ ٱلْمُهِينِ
Amharic Translation - Africa Academy14. በእርሱም ላይ ሞትን በፈጸምንበት ጊዜ መሞቱን ብትሩን የምትበላ ተንቀሳቃሽ ምስጥ እንጂ ሌላ አላመለከታቸዉም:: በወደቀ ጊዜም አጋንንቶች ሩቅን ሚስጥር የሚያውቁ በሆነ ኖሮ በአዋራጅ ስቃይ ውስጥ የማይቆዩ እንደነበሩ ተረዱ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
لَقَدْ كَانَ لِسَبَإٍ فِى مَسْكَنِهِمْ ءَايَةٌ جَنَّتَانِ عَن يَمِينٍ وَشِمَالٍ كُلُوا۟ مِن رِّزْقِ رَبِّكُمْ وَٱشْكُرُوا۟ لَهُۥ بَلْدَةٌ طَيِّبَةٌ وَرَبٌّ غَفُورٌ
Amharic Translation - Africa Academy15. ለሰበእ ነገዶች በመኖሪያቸው በእውነት አስደናቂ ምልክት ነበራቸው:: ከግራና ከቀኝ ሁለት አትክልቶች ነበሯቸው:: «ከጌታችሁ ሲሳይ ብሉ ለእሱም አመስግኑ:: አገራችሁ ውብ አገር ናት:: ጌታችሁም መሃሪ ጌታ ነው» ተባሉ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَأَعْرَضُوا۟ فَأَرْسَلْنَا عَلَيْهِمْ سَيْلَ ٱلْعَرِمِ وَبَدَّلْنَٰهُم بِجَنَّتَيْهِمْ جَنَّتَيْنِ ذَوَاتَىْ أُكُلٍ خَمْطٍ وَأَثْلٍ وَشَىْءٍ مِّن سِدْرٍ قَلِيلٍ
Amharic Translation - Africa Academy16. አላህን ከማመስገን ዞሩም:: በእነርሱም ላይ የግድቡን ጎርፍ ለቀቅንባቸው:: በሁለቱ አትክልቶቻቸዉም ሌሎች ሁለትን አትክልቶች ባለ መርጋጋ ፍሬዎችን ባለ ጠደቻና ከቁርቁራም ባለ ጥቂት ዛፎችን ለወጥናቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ذَٰلِكَ جَزَيْنَٰهُم بِمَا كَفَرُوا۟ وَهَلْ نُجَٰزِىٓ إِلَّا ٱلْكَفُورَ
Amharic Translation - Africa Academy17. በመካዳቸው ምክንያት ይህንን መነዳናቸው:: (እንደዚህ ያለውን ቅጣት) በጣም ከሓዲ ለሆነ ሰው ብቻ እንጂ ለሌላው እንሰጣለን?
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَجَعَلْنَا بَيْنَهُمْ وَبَيْنَ ٱلْقُرَى ٱلَّتِى بَٰرَكْنَا فِيهَا قُرًى ظَٰهِرَةً وَقَدَّرْنَا فِيهَا ٱلسَّيْرَ سِيرُوا۟ فِيهَا لَيَالِىَ وَأَيَّامًا ءَامِنِينَ
Amharic Translation - Africa Academy18. በእነርሱና በዚያች በውስጧ በረከትን ባደረግንባት አገር (በሻም) መካከልም ተከታታይ መንደሮችን (ቅጥልጥል ከተሞች) አደረግን:: በእርሷም ጉዞን ወሰንን። «በሌሊቶችም ሆነ በቀኖች ዉስጥ ጸጥተኞች ሆናችሁ ተጓዙ» (አልን)::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَقَالُوا۟ رَبَّنَا بَٰعِدْ بَيْنَ أَسْفَارِنَا وَظَلَمُوٓا۟ أَنفُسَهُمْ فَجَعَلْنَٰهُمْ أَحَادِيثَ وَمَزَّقْنَٰهُمْ كُلَّ مُمَزَّقٍ إِنَّ فِى ذَٰلِكَ لَـَٔايَٰتٍ لِّكُلِّ صَبَّارٍ شَكُورٍ
Amharic Translation - Africa Academy19. «ጌታችን ሆይ! በጉዞዎቻችን መካከል አራርቅልን» አሉም:: ነፍሶቻቸውንም በደሉ:: መገረሚያ ወሬዎችም አደረግናቸው:: መበታተንንም ሁሉ በታተንናቸው:: በዚህ ውስጥ በጣም ታጋሽና አመስጋኝ ለሆነ ሁሉ ብዙ መገለጫዎች አሉበት::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلَقَدْ صَدَّقَ عَلَيْهِمْ إِبْلِيسُ ظَنَّهُۥ فَٱتَّبَعُوهُ إِلَّا فَرِيقًا مِّنَ ٱلْمُؤْمِنِينَ
Amharic Translation - Africa Academy20. ዲያብሎስም በእነርሱ ላይ ምኞቱን በእርግጥ ፈጸመ:: እናም ከአመኑት የሆኑት ቡድኖች በስተቀር ተከተሉት::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَمَا كَانَ لَهُۥ عَلَيْهِم مِّن سُلْطَٰنٍ إِلَّا لِنَعْلَمَ مَن يُؤْمِنُ بِٱلْـَٔاخِرَةِ مِمَّنْ هُوَ مِنْهَا فِى شَكٍّ وَرَبُّكَ عَلَىٰ كُلِّ شَىْءٍ حَفِيظٌ
Amharic Translation - Africa Academy21. በመጨረሻይቱም ዓለም የሚያምነውን ከዚያ እርሱ ከእርሷ በመጠራጠር ውስጥ ከሆነው ሰው ለይተን እንድናውቅ እንጂ በእነርሱ ላይ ለእርሱ ምንም ስልጣን አልነበረዉም:: ጌታህም በነገሩ ሁሉ ላይ ተጠባባቂ ነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قُلِ ٱدْعُوا۟ ٱلَّذِينَ زَعَمْتُم مِّن دُونِ ٱللَّهِ لَا يَمْلِكُونَ مِثْقَالَ ذَرَّةٍ فِى ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَلَا فِى ٱلْأَرْضِ وَمَا لَهُمْ فِيهِمَا مِن شِرْكٍ وَمَا لَهُۥ مِنْهُم مِّن ظَهِيرٍ
Amharic Translation - Africa Academy22. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «እነዚያን ከአላህ ሌላ አማልክት ብላችሁ የምታስቧቸውን ጥሩ:: በሰማያትም ሆነ በምድር ውስጥ የብናኝ ክብደት ያህል እንኳ ምንም አይችሉም:: ለእነርሱም በሁለቱም ውስጥ ምንም ሽርክና የላቸዉም:: ከእነርሱም ለእርሱ ምንም አጋዥ የለዉም።» በላቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلَا تَنفَعُ ٱلشَّفَٰعَةُ عِندَهُۥٓ إِلَّا لِمَنْ أَذِنَ لَهُۥ حَتَّىٰٓ إِذَا فُزِّعَ عَن قُلُوبِهِمْ قَالُوا۟ مَاذَا قَالَ رَبُّكُمْ قَالُوا۟ ٱلْحَقَّ وَهُوَ ٱلْعَلِىُّ ٱلْكَبِيرُ
Amharic Translation - Africa Academy23. ምልጃም እርሱ ለፈቀደለት ሰው ብቻ ቢሆን እንጂ እሱ ዘንድ ምንም አትጠቅምም:: ከልቦቻቸው ላይ ድንጋጤው በተገለጠ ጊዜ ተማላጆቹ «ጌታችሁ ምን አለ?» ይላሉ:: አማላጆቹም: «እውነትን አለ። እርሱም ከፍተኛውና ታላቁ ጌታ ነው።» ይላሉ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قُلْ مَن يَرْزُقُكُم مِّنَ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِ قُلِ ٱللَّهُ وَإِنَّآ أَوْ إِيَّاكُمْ لَعَلَىٰ هُدًى أَوْ فِى ضَلَٰلٍ مُّبِينٍ
Amharic Translation - Africa Academy24. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ)፤ «ከሰማያትና ከምድር ሲሳይን የሚሰጣችሁ ማነው?» በላቸው። «አላህ ነው እኛ ወይም እናንተ በትክክለኛው መንገድ ላይ ወይም በግልጽ መሳሳት ውስጥ ነን።» በላቸው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قُل لَّا تُسْـَٔلُونَ عَمَّآ أَجْرَمْنَا وَلَا نُسْـَٔلُ عَمَّا تَعْمَلُونَ
Amharic Translation - Africa Academy25. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ !)«ካጠፋነው ጥፋት አትጠየቁም:: ከምትሰሩትም ስራ አንጠየቅም።» በላቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قُلْ يَجْمَعُ بَيْنَنَا رَبُّنَا ثُمَّ يَفْتَحُ بَيْنَنَا بِٱلْحَقِّ وَهُوَ ٱلْفَتَّاحُ ٱلْعَلِيمُ
Amharic Translation - Africa Academy26.(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ጌታችን በመካከላችን ይሰበስባል። ከዚያም በመካከላችን በእውነት ይፈርዳል:: እርሱም በትክክል ፈራጁና አዋቂው ነው።» በላቸው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قُلْ أَرُونِىَ ٱلَّذِينَ أَلْحَقْتُم بِهِۦ شُرَكَآءَ كَلَّا بَلْ هُوَ ٱللَّهُ ٱلْعَزِيزُ ٱلْحَكِيمُ
Amharic Translation - Africa Academy27.(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «እነዚያን ተጋሪዎች አድርጋችሁ በእሱ ያስጠጋችኋቸውን ጣዖታት እስቲ አሳዩኝ:: ተው አታጋሩ:: በእውነት እርሱ አሸናፊዉና ጥበበኛው አላህ ነው።» በላቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَمَآ أَرْسَلْنَٰكَ إِلَّا كَآفَّةً لِّلنَّاسِ بَشِيرًا وَنَذِيرًا وَلَٰكِنَّ أَكْثَرَ ٱلنَّاسِ لَا يَعْلَمُونَ
Amharic Translation - Africa Academy28. አንተንም ለሰዎች ሁሉ በመላ አብሳሪና አስፈራሪ አድርገን ቢሆን እንጂ አልላክንህም:: ግን አብዛኞቹ ሰዎች አያውቁም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَيَقُولُونَ مَتَىٰ هَٰذَا ٱلْوَعْدُ إِن كُنتُمْ صَٰدِقِينَ
Amharic Translation - Africa Academy29. «እውነተኞችም እንደ ሆናችሁ ይህ ቀጠሮ መቼ ነው?» ይላሉ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قُل لَّكُم مِّيعَادُ يَوْمٍ لَّا تَسْتَـْٔخِرُونَ عَنْهُ سَاعَةً وَلَا تَسْتَقْدِمُونَ
Amharic Translation - Africa Academy30. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ለእናንተ ከእርሱ አንዳችንም ሰዓት የማትዘገዩበት የማትቀድሙበትም የቀጠሮ ቀን አላችሁ።» በላቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَقَالَ ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ لَن نُّؤْمِنَ بِهَٰذَا ٱلْقُرْءَانِ وَلَا بِٱلَّذِى بَيْنَ يَدَيْهِ وَلَوْ تَرَىٰٓ إِذِ ٱلظَّٰلِمُونَ مَوْقُوفُونَ عِندَ رَبِّهِمْ يَرْجِعُ بَعْضُهُمْ إِلَىٰ بَعْضٍ ٱلْقَوْلَ يَقُولُ ٱلَّذِينَ ٱسْتُضْعِفُوا۟ لِلَّذِينَ ٱسْتَكْبَرُوا۟ لَوْلَآ أَنتُمْ لَكُنَّا مُؤْمِنِينَ
Amharic Translation - Africa Academy31. እነዚያም የካዱት «በዚህ ቁርኣንና በዚያ ከበፊቱ ባለዉም መጽሐፍ በጭራሽ አናምንም።» አሉ:: በዳዮችም ከፊላቸው ወደ ከፊሉ ንግግርን የሚመላላሱ ሆነው በጌታቸው ዘንድ በሚቆሙ ጊዜ ብታይ ኖሮ አስደናቂን ነገር ታይ ነበር:: እነዚያ የተዋረዱት ለእነዚያ ለኮሩት «እናንተ ባልነበራችሁ ኖሮ ትክክለኛ አማኞች በሆንን ነበር።» ይላሉ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالَ ٱلَّذِينَ ٱسْتَكْبَرُوا۟ لِلَّذِينَ ٱسْتُضْعِفُوٓا۟ أَنَحْنُ صَدَدْنَٰكُمْ عَنِ ٱلْهُدَىٰ بَعْدَ إِذْ جَآءَكُم بَلْ كُنتُم مُّجْرِمِينَ
Amharic Translation - Africa Academy32. እነዚያ የኮሩት ለእነዚያ ለተዋረዱት «ትክክለኛው እምነት ከመጣላችሁ በኋላ እኛ ከለከልናችሁን? አይደለም:: እናንተው ከሓዲያን ነበራችሁ።» ይሏቸዋል።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَقَالَ ٱلَّذِينَ ٱسْتُضْعِفُوا۟ لِلَّذِينَ ٱسْتَكْبَرُوا۟ بَلْ مَكْرُ ٱلَّيْلِ وَٱلنَّهَارِ إِذْ تَأْمُرُونَنَآ أَن نَّكْفُرَ بِٱللَّهِ وَنَجْعَلَ لَهُۥٓ أَندَادًا وَأَسَرُّوا۟ ٱلنَّدَامَةَ لَمَّا رَأَوُا۟ ٱلْعَذَابَ وَجَعَلْنَا ٱلْأَغْلَٰلَ فِىٓ أَعْنَاقِ ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ هَلْ يُجْزَوْنَ إِلَّا مَا كَانُوا۟ يَعْمَلُونَ
Amharic Translation - Africa Academy33. እነዚያም የተዋረዱት ለእነዚያ ለኮሩት «አይደለም። በአላህ እንድንክድና ለእርሱ ባላንጣዎችን እንድናደርግ ስታዙን (የከለከለን) የሌሊትና የቀን ዱለታችሁ ነው።» ይላሉ:: ቅጣትንም ባዩ ጊዜ ጸጸትን ይደብቃሉ:: በእነዚያም በካዱት አንገቶች ላይ እንዛዝሎችን እናደርጋለን:: ይሰሩት የነበሩትን እንጂ ሌላን ይመነዳሉን?
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَمَآ أَرْسَلْنَا فِى قَرْيَةٍ مِّن نَّذِيرٍ إِلَّا قَالَ مُتْرَفُوهَآ إِنَّا بِمَآ أُرْسِلْتُم بِهِۦ كَٰفِرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy34. በየትኛዋም ከተማ አስፈራሪን አላክንም ነዋሪዎችዋ «እኛ በተላካችሁት ከሓዲያን ነን።» ያሉ ቢሆኑ እንጂ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَقَالُوا۟ نَحْنُ أَكْثَرُ أَمْوَٰلًا وَأَوْلَٰدًا وَمَا نَحْنُ بِمُعَذَّبِينَ
Amharic Translation - Africa Academy35. «እኛም በገንዘቦችና በልጆች ይበልጥ የበዛን ነን:: እኛም የምንቀጣ አይደለንም» አሉ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قُلْ إِنَّ رَبِّى يَبْسُطُ ٱلرِّزْقَ لِمَن يَشَآءُ وَيَقْدِرُ وَلَٰكِنَّ أَكْثَرَ ٱلنَّاسِ لَا يَعْلَمُونَ
Amharic Translation - Africa Academy36. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ጌታዬ ሲሳይን ለሚሻው ሰው ሁሉ ያሰፋል:: ለሚሻው ሰዉም ሁሉ ያጠባል:: ግን አብዛኛዎቹ ሰዎች ይህን አያውቁም።» በላቸው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَمَآ أَمْوَٰلُكُمْ وَلَآ أَوْلَٰدُكُم بِٱلَّتِى تُقَرِّبُكُمْ عِندَنَا زُلْفَىٰٓ إِلَّا مَنْ ءَامَنَ وَعَمِلَ صَٰلِحًا فَأُو۟لَٰٓئِكَ لَهُمْ جَزَآءُ ٱلضِّعْفِ بِمَا عَمِلُوا۟ وَهُمْ فِى ٱلْغُرُفَٰتِ ءَامِنُونَ
Amharic Translation - Africa Academy37. ገንዘቦቻችሁና ልጆቻችሁም ያች እኛ ዘንድ መቅረብን የምታቀርባችሁ አይደለችም:: ያ በትክክል ያመነና መልካምን የሰራ ብቻ ሲቀር:: እነዚያ ለእነርሱ በሰሩት መልካም ስራ እጥፍ ምንዳ አለላቸው:: እነርሱም በገነት ሰገነቶች ውስጥ ጸጥተኞች ናቸው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَٱلَّذِينَ يَسْعَوْنَ فِىٓ ءَايَٰتِنَا مُعَٰجِزِينَ أُو۟لَٰٓئِكَ فِى ٱلْعَذَابِ مُحْضَرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy38. እነዚያም የሚያቅቱ መስሏቸው አናቅጻችንን ለማበላሸት የሚጥሩ ሁሉ እነዚያ በቅጣት ውስጥ የሚጣዱ ናቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قُلْ إِنَّ رَبِّى يَبْسُطُ ٱلرِّزْقَ لِمَن يَشَآءُ مِنْ عِبَادِهِۦ وَيَقْدِرُ لَهُۥ وَمَآ أَنفَقْتُم مِّن شَىْءٍ فَهُوَ يُخْلِفُهُۥ وَهُوَ خَيْرُ ٱلرَّٰزِقِينَ
Amharic Translation - Africa Academy39. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ጌታዬ ሲሳይን ከባሮቹ ለሚሻው ሰው ያሰፋል:: ለእርሱም ያጠባል:: ከማንኛዉም ነገር የምትለግሱትን እርሱ ይተካዋል:: እርሱም ከሲሳይ ሰጪዎች ሁሉ በላጭ ነው።» በላቸው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَيَوْمَ يَحْشُرُهُمْ جَمِيعًا ثُمَّ يَقُولُ لِلْمَلَٰٓئِكَةِ أَهَٰٓؤُلَآءِ إِيَّاكُمْ كَانُوا۟ يَعْبُدُونَ
Amharic Translation - Africa Academy40. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ሁሉንም በሚሰበስባቸውና ከዚያም ለመላእክቶቹ «እነዚህ እናንተን ይገዙ ነበሩን?» በሚላቸው ቀን የሚሆነውን አስታውስ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالُوا۟ سُبْحَٰنَكَ أَنتَ وَلِيُّنَا مِن دُونِهِم بَلْ كَانُوا۟ يَعْبُدُونَ ٱلْجِنَّ أَكْثَرُهُم بِهِم مُّؤْمِنُونَ
Amharic Translation - Africa Academy41. መላእክቶቹም «ጥራት ይገባህ ረዳታችን ከእነርሱ ሌላ የሆንከው አንተው ብቻ ነህ:: እንደሚሉት አይደለም:: ይልቁንም አጋንንትን ይገዙ ነበሩ:: አብዛኞቻቸው በእነርሱ አማኞች ናቸው።» ይላሉ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَٱلْيَوْمَ لَا يَمْلِكُ بَعْضُكُمْ لِبَعْضٍ نَّفْعًا وَلَا ضَرًّا وَنَقُولُ لِلَّذِينَ ظَلَمُوا۟ ذُوقُوا۟ عَذَابَ ٱلنَّارِ ٱلَّتِى كُنتُم بِهَا تُكَذِّبُونَ
Amharic Translation - Africa Academy42. ዛሬም ከፊላችሁ ለከፊሉ መጥቀምንም ሆነ መጉዳትን አይችሉም:: ለእነዚያም ለበደሉት ሰዎች «ያችን በእርሷ ታስተባብሉባት የነበራችሁትን የእሳት ቅጣት ቅመሱ» እንላቸዋለን::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَإِذَا تُتْلَىٰ عَلَيْهِمْ ءَايَٰتُنَا بَيِّنَٰتٍ قَالُوا۟ مَا هَٰذَآ إِلَّا رَجُلٌ يُرِيدُ أَن يَصُدَّكُمْ عَمَّا كَانَ يَعْبُدُ ءَابَآؤُكُمْ وَقَالُوا۟ مَا هَٰذَآ إِلَّآ إِفْكٌ مُّفْتَرًى وَقَالَ ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ لِلْحَقِّ لَمَّا جَآءَهُمْ إِنْ هَٰذَآ إِلَّا سِحْرٌ مُّبِينٌ
Amharic Translation - Africa Academy43. በእነርሱም ላይ አናቅጻችን ግልጽ ሆነው በተነበቡላቸው ጊዜ «ይህ አባቶቻችሁ ይገዙት ከነበሩት ነገር ሊከለክላችሁ የሚፈልግ ሰው እንጂ ሌላ አይደለም።» አሉ:: «ይህም ቁርዓን የተቀጣጠፈ ውሸት ነው እንጂ ሌላ አይደለም።» አሉም። እነዚያም በአላህ የካዱት እውነትን በመጣላቸው ጊዜ «ግልጥ ድግምት ነው እንጂ ሌላ አይደለም።» አሉ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَمَآ ءَاتَيْنَٰهُم مِّن كُتُبٍ يَدْرُسُونَهَا وَمَآ أَرْسَلْنَآ إِلَيْهِمْ قَبْلَكَ مِن نَّذِيرٍ
Amharic Translation - Africa Academy44. የሚያጠኗቸው የሆኑ መጽሐፎችንም ምንም አልሰጠናቸዉም:: ካንተ በፊትም አስፈራሪ ነብይን ወደ እነርሱ አልላክንም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَكَذَّبَ ٱلَّذِينَ مِن قَبْلِهِمْ وَمَا بَلَغُوا۟ مِعْشَارَ مَآ ءَاتَيْنَٰهُمْ فَكَذَّبُوا۟ رُسُلِى فَكَيْفَ كَانَ نَكِيرِ
Amharic Translation - Africa Academy45. እነዚያም ከእነርሱ በፊት የነበሩት አስተባብለዋል:: የሰጠናቸውንም ከአስር አንዱን እንኳን እነዚህ አልደረሱም:: እናም መልዕክተኞቼን አስተባበሉ:: ነቀፍኳቸዉም:: መንቀፌም እንዴት ነበር::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قُلْ إِنَّمَآ أَعِظُكُم بِوَٰحِدَةٍ أَن تَقُومُوا۟ لِلَّهِ مَثْنَىٰ وَفُرَٰدَىٰ ثُمَّ تَتَفَكَّرُوا۟ مَا بِصَاحِبِكُم مِّن جِنَّةٍ إِنْ هُوَ إِلَّا نَذِيرٌ لَّكُم بَيْنَ يَدَىْ عَذَابٍ شَدِيدٍ
Amharic Translation - Africa Academy46. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «የምገስጻችሁ በአንዲት ነገር ብቻ ነው:: እርሷም ሁለት ሁለት፤ አንድ አንድም ሆናችሁ ለአላህ እንድትነሱና ከዚያም በጓደኛችሁ (በሙሐመድ) ምንም እብደት የሌለበት መሆኑን መርምራችሁ እንድትረዱ ነው:: እርሱ ለእናንተ ከብርቱ ቅጣት በስተፊት አስጠንቃቂ ነው እንጂ ሌላ አይደለም።» በላቸው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قُلْ مَا سَأَلْتُكُم مِّنْ أَجْرٍ فَهُوَ لَكُمْ إِنْ أَجْرِىَ إِلَّا عَلَى ٱللَّهِ وَهُوَ عَلَىٰ كُلِّ شَىْءٍ شَهِيدٌ
Amharic Translation - Africa Academy47. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ከዋጋ ማንኛውንም የጠየቅኋችሁ ቢኖር እርሱ ለእናንተው ነው:: ዋጋዬ በአላህ ላይ እንጂ በሌላ ላይ አይደለም:: እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ አዋቂ ነው።» በላቸው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قُلْ إِنَّ رَبِّى يَقْذِفُ بِٱلْحَقِّ عَلَّٰمُ ٱلْغُيُوبِ
Amharic Translation - Africa Academy48. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ጌታዬ እውነትን ብቻ ያወርዳል:: ሩቅ የሆኑትን ምስጢሮች ሁሉ አዋቂ ነው።» በላቸው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قُلْ جَآءَ ٱلْحَقُّ وَمَا يُبْدِئُ ٱلْبَٰطِلُ وَمَا يُعِيدُ
Amharic Translation - Africa Academy49. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «እውነቱ መጣ ውሸት መነሻም መድረሻም የለዉምና ተወገደ።» በላቸው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قُلْ إِن ضَلَلْتُ فَإِنَّمَآ أَضِلُّ عَلَىٰ نَفْسِى وَإِنِ ٱهْتَدَيْتُ فَبِمَا يُوحِىٓ إِلَىَّ رَبِّىٓ إِنَّهُۥ سَمِيعٌ قَرِيبٌ
Amharic Translation - Africa Academy50. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ብሳሳትም የምሳሳተው በራሴ ላይ ብቻ ነው:: ብመራም ጌታዬ ወደ እኔ በሚያወርደው መመሪያ መሰረት ነው:: እርሱ ሁሉ ሰሚና ለሁሉም ቅርብ ነውና።» በላቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلَوْ تَرَىٰٓ إِذْ فَزِعُوا۟ فَلَا فَوْتَ وَأُخِذُوا۟ مِن مَّكَانٍ قَرِيبٍ
Amharic Translation - Africa Academy51. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በደነገጡና ማምለጫ በሌላቸው ጊዜ ከቅርብ ስፍራም በተያዙ ጊዜ ሁኔታቸውን ብታይ ኖሮ (አስደናቂን ነገር ባየህ ነበር)::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَقَالُوٓا۟ ءَامَنَّا بِهِۦ وَأَنَّىٰ لَهُمُ ٱلتَّنَاوُشُ مِن مَّكَانٍۭ بَعِيدٍ
Amharic Translation - Africa Academy52. «በእርሱም አሁን አመንን።» ይላሉ:: ለእነርሱም ከሩቅ ስፍራ እምነትን በቀላሉ ማግኘት ከየታቸው ይታደሉና?
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَقَدْ كَفَرُوا۟ بِهِۦ مِن قَبْلُ وَيَقْذِفُونَ بِٱلْغَيْبِ مِن مَّكَانٍۭ بَعِيدٍ
Amharic Translation - Africa Academy53. በፊትም በእርሱ በእርግጥ ክደዋል:: ከሩቅ ስፍራም በግምት ንግግርን ይጥላሉ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَحِيلَ بَيْنَهُمْ وَبَيْنَ مَا يَشْتَهُونَ كَمَا فُعِلَ بِأَشْيَاعِهِم مِّن قَبْلُ إِنَّهُمْ كَانُوا۟ فِى شَكٍّ مُّرِيبٍۭ
Amharic Translation - Africa Academy54. ከዚህ ቀደም በመሰሎቻቸው እንደተሰራዉም ብጤ በእነርሱና በሚፈልጉት መካከል ተጋረደ:: እነርሱ በእርግጥ በአወላዋይ ጥርጣሬ ውስጥ ነበሩና::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
→