ٱلنَّبِىُّ أَوْلَىٰ بِٱلْمُؤْمِنِينَ مِنْ أَنفُسِهِمْ وَأَزْوَٰجُهُۥٓ أُمَّهَٰتُهُمْ وَأُو۟لُوا۟ ٱلْأَرْحَامِ بَعْضُهُمْ أَوْلَىٰ بِبَعْضٍ فِى كِتَٰبِ ٱللَّهِ مِنَ ٱلْمُؤْمِنِينَ وَٱلْمُهَٰجِرِينَ إِلَّآ أَن تَفْعَلُوٓا۟ إِلَىٰٓ أَوْلِيَآئِكُم مَّعْرُوفًا كَانَ ذَٰلِكَ فِى ٱلْكِتَٰبِ مَسْطُورًا
Amharic Translation - Africa Academy6. ነብዩ (ሙሐመድ) ለአማኞች ከነፍሶቻቸው ይበልጥ ቀራቢ ነው:: ሚስቶቹም እናቶቻቸው ናቸው:: የዝምድና ባለቤቶችም ከፊላቸው በከፊሉ ላይ (ለውርስ) በአላህ መጽሐፍ ውስጥ ከአማኞችና ከስደተኞች ይልቅ የተገባቸው ናቸው:: ለወዳጆቻችሁ በኑዛዜ መልካም ስራን ብትሰሩ ግን ይፈቀዳል:: ይህ በአላህ መጽሐፉ ውስጥ ቀድሞውኑ የተመዘገበ ነው::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqነቢዩ በምእምናን ከነፍሶቻቸው ይበልጥ ተገቢ ነው፡፡ ሚስቶቹም እናቶቻቸው ናቸው፡፡ የዝምድና ባለቤቶችም ከፊላቸው በከፊሉ (ውርስ) በአላህ መጽሐፍ ውስጥ ከምእምናንና ከስደተኞቹ ይልቅ የተገባቸው ናቸው፡፡ግን ወደ ወዳጆቻችሁ (በኑዛዜ) መልካምን ብትሰሩ (ይፈቀዳል)፡፡ ይህ በመጽሐፉ ውሰጥ የተመዘገበ ነው፡፡