caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Al-Ahzaab፣ አንቀጽ 51

መዲና · የወረደበት ቅደም ተከተል 90 · 33:51

تُرْجِى مَن تَشَآءُ مِنْهُنَّ وَتُـْٔوِىٓ إِلَيْكَ مَن تَشَآءُ وَمَنِ ٱبْتَغَيْتَ مِمَّنْ عَزَلْتَ فَلَا جُنَاحَ عَلَيْكَ ذَٰلِكَ أَدْنَىٰٓ أَن تَقَرَّ أَعْيُنُهُنَّ وَلَا يَحْزَنَّ وَيَرْضَيْنَ بِمَآ ءَاتَيْتَهُنَّ كُلُّهُنَّ وَٱللَّهُ يَعْلَمُ مَا فِى قُلُوبِكُمْ وَكَانَ ٱللَّهُ عَلِيمًا حَلِيمًا

Amharic Translation - Africa Academy51. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከእነርሱ መካከል የምትፈልጋትን ታቆያለህ :: የምትፈልጋትንም ወደ አንተ ታስጠጋለህ:: በመፍታት ከአራቅሃትም የፈለግሃትን በመመለስ ብታስጠጋ ባንተ ላይ ኃጢአት የለብህም:: ይህ ዓይኖቻቸው ወደ መርጋት ወደ አለማዘናቸዉም ለሁሉም በሰጠሃቸው ነገር ወደ መውደዳቸዉም በጣም የቀረበ ነው:: አላህም በልቦቻችሁ ውስጥ ያለውን ሁሉ ያውቃል:: አላህ ሁሉን አዋቂና ታጋሽ ነው::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqከእነርሱ የምትሻትን ታቆያለህ፡፡ የምትሻውንም ወደ አንተ ታስጠጋለህ፡፡ (በመፍታት) ከአራቅሃትም የፈለግሃትን (በመመለስ ብታስጠጋ) በአንተ ላይ ኀጢአት የለብህም፡፡ ይህ ዓይኖቻቸው ወደ መርጋት፣ ወደ አለማዘናቸውም፣ ለሁሉም በሰጠሃቸው ነገር ወደ መውደዳቸውም በጣም የቀረበ ነው፡፡ አላህም በልቦቻችሁ ውስጥ ያለውን ሁሉ ያውቃል፡፡ አላህም ዐዋቂ ታጋሽ ነው፡፡
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70