أَشِحَّةً عَلَيْكُمْ فَإِذَا جَآءَ ٱلْخَوْفُ رَأَيْتَهُمْ يَنظُرُونَ إِلَيْكَ تَدُورُ أَعْيُنُهُمْ كَٱلَّذِى يُغْشَىٰ عَلَيْهِ مِنَ ٱلْمَوْتِ فَإِذَا ذَهَبَ ٱلْخَوْفُ سَلَقُوكُم بِأَلْسِنَةٍ حِدَادٍ أَشِحَّةً عَلَى ٱلْخَيْرِ أُو۟لَٰٓئِكَ لَمْ يُؤْمِنُوا۟ فَأَحْبَطَ ٱللَّهُ أَعْمَٰلَهُمْ وَكَانَ ذَٰلِكَ عَلَى ٱللَّهِ يَسِيرًا
Amharic Translation - Africa Academy19. (አማኞች ሆይ!) በእናንተ ላይ እርዳታን የነፈጉ ሆነው እንጂ የማይመጡትን፤ ሽብሩም በመጣ ጊዜ እንደዚያ ከሞት መከራ በእርሱ ላይ የሚሸፍን አደጋ እንደ ወደቀበት ዓይኖቻቸው ወዲያና ወዲህ የምትንከራተት ሆና ወደ አንተ ሲመለከቱ ታያቸዋለህ:: ሽብሩም በሄደ ጊዜ በገንዘብ ላይ የሚሳሱ ሆነው በተቡ ምላሶች ይነድፏችኋል:: እነዚያ አላመኑም:: ስለዚህ አላህ ስራዎቻቸውን አበላሸ:: ይህም በአላህ ላይ ገር ነው።
Amharic Translation - Muhammad Sadiqበእናንተ ላይ (እርዳታን) የነፈጉ ሆነው እንጅ (የማይመጡትን)፣ ሽብሩም በመጣ ጊዜ እንደዚያ ከሞት (መከራ) በርሱ ላይ የሚሸፍን ዐደጋ እንደወደቀበት ዓይኖቻቸው ወዲያና ወዲህ የምትዞር ኾና ወዳንተ ሲመለከቱ ታያቸዋለህ፡፡ ሽብሩም በኼደ ጊዜ በገንዘብ ላይ የሚሳሱ ኾነው በተቡ ምላሶች ይነድፏችኋል፡፡ እነዚያ አላመኑም፡፡ ስለዚህ አላህ ሥራዎቻቸውን አበላሸ፡፡ ይህም በአላህ ላይ ገርነው፡፡