وَإِذْ قَالَت طَّآئِفَةٌ مِّنْهُمْ يَٰٓأَهْلَ يَثْرِبَ لَا مُقَامَ لَكُمْ فَٱرْجِعُوا۟ وَيَسْتَـْٔذِنُ فَرِيقٌ مِّنْهُمُ ٱلنَّبِىَّ يَقُولُونَ إِنَّ بُيُوتَنَا عَوْرَةٌ وَمَا هِىَ بِعَوْرَةٍ إِن يُرِيدُونَ إِلَّا فِرَارًا
Amharic Translation - Africa Academy13. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከእነርሱም የሆነ ቡድን «የየስሪብ ሰዎች ሆይ! ለእናንተ ስፍራ የላችሁምና ተመለሱ።» ባሉ ጊዜ (የሆነውን አስታውሱ):: ከእነርሱም መካከል ከፊሎቹ ነውረኛ ሳይሆኑ «ቤቶቻችን ነውረኛ ናቸው።» በማለት ነብዩን ከጦሩ ለመመለስ ፈቃድን ይጠይቃሉ:: መሸሽን እንጂ ሌላን አይፈልጉም::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqከእነርሱም የሆኑ ጭፍሮች «የየስሪብ ሰዎች ሆይ! ለእናንተ ስፍራ የላችሁምና ተመለሱ» ባሉ ጊዜ (አስታውሱ)፡፡ ከእነርሱም «ከፊሎቹ እርሷ ነውረኛ ሳትሆን ቤቶቻችን ነውረኛ ናቸው» የሚሉ ሆነው ነቢዩን (ከጦሩ ለመመለስ) ፈቃድን ይጠይቃሉ፡፡ መሸሽን እንጂ ሌላ አይፈልጉም፡፡