caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Al-Ahzaab፣ አንቀጽ 4

መዲና · የወረደበት ቅደም ተከተል 90 · 33:4

مَّا جَعَلَ ٱللَّهُ لِرَجُلٍ مِّن قَلْبَيْنِ فِى جَوْفِهِۦ وَمَا جَعَلَ أَزْوَٰجَكُمُ ٱلَّٰٓـِٔى تُظَٰهِرُونَ مِنْهُنَّ أُمَّهَٰتِكُمْ وَمَا جَعَلَ أَدْعِيَآءَكُمْ أَبْنَآءَكُمْ ذَٰلِكُمْ قَوْلُكُم بِأَفْوَٰهِكُمْ وَٱللَّهُ يَقُولُ ٱلْحَقَّ وَهُوَ يَهْدِى ٱلسَّبِيلَ

Amharic Translation - Africa Academy4. (ሙስሊሞች ሆይ!) አላህ ለአንድ ሰው በሆዱ ውስጥ ሁለትን ልቦች አላደረገም:: እነዚያን «እንደናቶቻችን ጀርባዎች ይሁኑብን» የምትሏቸውን ሚስቶቻችሁንም እናቶቻችሁ አላደረገም:: ልጅ በማድረግ የምታስጠጓቸውንም ልጆቻችሁ አላደረገም:: ይህ በአፎቻችሁ የምትሉት ቃላችሁ ብቻ ነው:: አላህ እውነትን ይናገራል:: ትክክለኛውን መንገድም ይመራል::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqአላህ ለአንድ ሰው በሆዱ ውስጥ ሁለትን ልቦች አላደረገም፡፡ ሚስቶቻችሁንም እነዚያን ከእነርሱ እንደናቶቻችሁ ጀርባዎች ይሁኑብን የምትሏቸውን እናቶቻችሁ አላደረገም፡፡ ልጅ በማድረግ የምታስጠጓቸውንም ልጆቻችሁ አላደረገም፡፡ ይህ በአፎቻችሁ የምትሉት ነው፡፡ አላህም እውነቱን ይናገራል፡፡ እርሱም ትክክለኛውን መንገድ ይመራል፡፡
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70