وَإِذْ تَقُولُ لِلَّذِىٓ أَنْعَمَ ٱللَّهُ عَلَيْهِ وَأَنْعَمْتَ عَلَيْهِ أَمْسِكْ عَلَيْكَ زَوْجَكَ وَٱتَّقِ ٱللَّهَ وَتُخْفِى فِى نَفْسِكَ مَا ٱللَّهُ مُبْدِيهِ وَتَخْشَى ٱلنَّاسَ وَٱللَّهُ أَحَقُّ أَن تَخْشَىٰهُ فَلَمَّا قَضَىٰ زَيْدٌ مِّنْهَا وَطَرًا زَوَّجْنَٰكَهَا لِكَىْ لَا يَكُونَ عَلَى ٱلْمُؤْمِنِينَ حَرَجٌ فِىٓ أَزْوَٰجِ أَدْعِيَآئِهِمْ إِذَا قَضَوْا۟ مِنْهُنَّ وَطَرًا وَكَانَ أَمْرُ ٱللَّهِ مَفْعُولًا
Amharic Translation - Africa Academy37. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ለዚያም አላህ በእርሱ ላይ ለለገሰለትና አንተም (ነጻ በማውጣት) በእርሱ ላይ ለለገስክለት ሰው አላህ ገላጩ የሆነን ነገር በነፍስህ ውስጥ የምትደብቅና አላህን ልትፈራው ይልቅ የተገባው ሲሆን ሰዎችን የምትፈራ ሆነህ «ሚስትህን ያዝ:: አላህንም ፍራ» በምትል ጊዜ (የሆነዉን አስታውስ):: ዘይድም ከእርሷ ጉዳዩን በፈጸመ ጊዜ በምዕመኖች ላይ ልጅ አድርገው ባስጠጓቸው ሰዎች ሚስቶች ከእነርሱ ጉዳይን በፈጸሙ ጊዜ በማግባት ችግር እንዳይደርስባቸው እርሷን አጋባንህ (ዳርንህ):: የአላህም ትእዛዝ ተፈጻሚ ነው::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqለእዚያም አላህ በእርሱ ላይ ለለገሰለትና (አንተም ነጻ በማውጣት) በእርሱ ላይ ለለገስክለት ሰው (ለዘይድ) አላህ ገላጩ የሆነን ነገር በነፍስህ ውስጥ የምትደብቅና አላህ ልትፈራው ይልቅ የተገባው ሲሆን ሰዎችን የምትፈራ ሆነህ «ሚስትህን ባንተ ዘንድ ያዝ፤ (ከመፍታት) አላህንም ፍራ» በምትል ጊዜ (አስታውስ)፡፡ ዘይድም ከእርሷ ጉዳይን በፈጸመ ጊዜ በምእምናኖች ላይ ልጅ አድርገው ባስጠጉዋቸው (ሰዎች) ሚስቶች ከእነርሱ ጉዳይን በፈጸሙ ጊዜ (በማግባት) ችግር እንዳይኖርባቸው እርሷን አጋባንህ፡፡ የአላህም ትእዛዝ ተፈጻሚ ነው፡፡