caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Ar-Room الروم

60 አንቀጾች · መካ · የወረደበት ቅደም ተከተል 84

بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ الٓمٓ

Amharic Translation - Africa Academy1. አሊፍ፤ ላም፤ ሚይም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

غُلِبَتِ ٱلرُّومُ

Amharic Translation - Africa Academy2. ሩም (በፋርሶች) ተሸነፈች፡፡

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فِىٓ أَدْنَى ٱلْأَرْضِ وَهُم مِّنۢ بَعْدِ غَلَبِهِمْ سَيَغْلِبُونَ

Amharic Translation - Africa Academy3. በጣም (ለዐረቡ ዓለም) ቅርብ በሆነችው ምድር ላይ እነርሱም (ከሶስት አመት ያላነሰ ከዘጠኝ ባልበለጠ በጥቂት አመታት ውስጥ) ከመሸነፋቸው በኋላ ያሸንፋሉ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فِى بِضْعِ سِنِينَ لِلَّهِ ٱلْأَمْرُ مِن قَبْلُ وَمِنۢ بَعْدُ وَيَوْمَئِذٍ يَفْرَحُ ٱلْمُؤْمِنُونَ

Amharic Translation - Africa Academy4. (ከሶስት አመት ያላነሰ ከዘጠኝ ባልበለጠ) በጥቂት አመታት ውስጥ (ያሸንፋሉ)። ጉዳዩ በፊትም ሆነ በኋላ የአላህ ነውና:: በዚያ ቀንም ምዕምናን ይደሰታሉ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

بِنَصْرِ ٱللَّهِ يَنصُرُ مَن يَشَآءُ وَهُوَ ٱلْعَزِيزُ ٱلرَّحِيمُ

Amharic Translation - Africa Academy5. በአላህ እርዳታ (ይደሰታሉ)፡፡ አላህ የሚሻውን ሰው ይረዳል:: እርሱም ሁሉን አሸናፊና አዛኝ ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَعْدَ ٱللَّهِ لَا يُخْلِفُ ٱللَّهُ وَعْدَهُۥ وَلَٰكِنَّ أَكْثَرَ ٱلنَّاسِ لَا يَعْلَمُونَ

Amharic Translation - Africa Academy6. አላህ እርዳታን በቁርጥ ቀጠረ:: አላህ ቀጠሮውን አያፈርስም:: ግን አብዛሀኞቹ ሰዎች አያውቁም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

يَعْلَمُونَ ظَٰهِرًا مِّنَ ٱلْحَيَوٰةِ ٱلدُّنْيَا وَهُمْ عَنِ ٱلْـَٔاخِرَةِ هُمْ غَٰفِلُونَ

Amharic Translation - Africa Academy7. ከቅርቢቱ ህይወት ግልጹን ብቻ ያውቃሉ:: እነርሱም ከኋለኛይቱ ዓለም ፍጹም ዘንጊዎች ናቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَوَلَمْ يَتَفَكَّرُوا۟ فِىٓ أَنفُسِهِم مَّا خَلَقَ ٱللَّهُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضَ وَمَا بَيْنَهُمَآ إِلَّا بِٱلْحَقِّ وَأَجَلٍ مُّسَمًّى وَإِنَّ كَثِيرًا مِّنَ ٱلنَّاسِ بِلِقَآئِ رَبِّهِمْ لَكَٰفِرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy8. በነፍሶቻቸው ሁኔታ አያስተውሉምን ? ሰማያትን፤ ምድርንና በመካከላቸው ያለውን ሁሉ በእውነትና በተወሰነ ጊዜ እንጂ አልፈጠራቸዉም:: ከሰዎች መካከል ብዙዎቹ ከጌታቸው ጋር በመገናኘት ከሓዲያን ናቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَوَلَمْ يَسِيرُوا۟ فِى ٱلْأَرْضِ فَيَنظُرُوا۟ كَيْفَ كَانَ عَٰقِبَةُ ٱلَّذِينَ مِن قَبْلِهِمْ كَانُوٓا۟ أَشَدَّ مِنْهُمْ قُوَّةً وَأَثَارُوا۟ ٱلْأَرْضَ وَعَمَرُوهَآ أَكْثَرَ مِمَّا عَمَرُوهَا وَجَآءَتْهُمْ رُسُلُهُم بِٱلْبَيِّنَٰتِ فَمَا كَانَ ٱللَّهُ لِيَظْلِمَهُمْ وَلَٰكِن كَانُوٓا۟ أَنفُسَهُمْ يَظْلِمُونَ

Amharic Translation - Africa Academy9. በምድር ላይ አይሄዱምና የእነዚያን ከበፊታቸው የነበሩትን ሰዎች ፍፃሜ እንዴት እንደነበር አይመለከቱምን? በኃይል ከእነርሱ ይበልጡ ነበሩ:: ምድርንም አረሱ:: እነዚህ ከአለሟትም የበለጠ አለሟት:: መልዕክተኞቻቸዉም በተአምራቶች መጡባቸው:: ግና አስተባበሉና ጠፉ:: አላህም የሚበድላቸው አልነበረም:: ግና ነፍሶቻቸውን በራሳቸው ይበድሉ ነበር::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ثُمَّ كَانَ عَٰقِبَةَ ٱلَّذِينَ أَسَٰٓـُٔوا۟ ٱلسُّوٓأَىٰٓ أَن كَذَّبُوا۟ بِـَٔايَٰتِ ٱللَّهِ وَكَانُوا۟ بِهَا يَسْتَهْزِءُونَ

Amharic Translation - Africa Academy10. ከዚያም የእነዚያ ያጠፉት ሰዎች መጨረሻ በአላህ አናቅጽ ማስተባበላቸውና በእርሷ የሚሳሳቁ የሚያፌዙ መሆናቸው (ምክንያት መጥፎ ቅጣት) ሆነ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ٱللَّهُ يَبْدَؤُا۟ ٱلْخَلْقَ ثُمَّ يُعِيدُهُۥ ثُمَّ إِلَيْهِ تُرْجَعُونَ

Amharic Translation - Africa Academy11. አላህ መፍጠርን ይጀምራል:: ከዚያም ይመልሰዋል:: ከዚያም ወደ እርሱ ትመለሳለችሁ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَيَوْمَ تَقُومُ ٱلسَّاعَةُ يُبْلِسُ ٱلْمُجْرِمُونَ

Amharic Translation - Africa Academy12. ሰዓቲቱም በምትከሰትበት ቀን አመጸኞች ጭጭ ይላሉ (ተስፋ ይቆርጣሉ)።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلَمْ يَكُن لَّهُم مِّن شُرَكَآئِهِمْ شُفَعَٰٓؤُا۟ وَكَانُوا۟ بِشُرَكَآئِهِمْ كَٰفِرِينَ

Amharic Translation - Africa Academy13. ለእነርሱም ከሚያጋሯቸው ጣዖታት መካከል አማላጆች አይኖሩዋቸዉም:: በሚያጋሯቸዉም ጣዖታት ከሓዲያን ይሆናሉ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَيَوْمَ تَقُومُ ٱلسَّاعَةُ يَوْمَئِذٍ يَتَفَرَّقُونَ

Amharic Translation - Africa Academy14. ሰዓቲቱም በምትከሰትበት ቀን በዚያ ቀን ይለያያሉ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَأَمَّا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ وَعَمِلُوا۟ ٱلصَّٰلِحَٰتِ فَهُمْ فِى رَوْضَةٍ يُحْبَرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy15. እነዚያ በአላህ ያመኑትና መልካሞችን ስራዎች የሰሩትማ እነርሱ በገነት ጨፌ ውስጥ ይደሰታሉ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَأَمَّا ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ وَكَذَّبُوا۟ بِـَٔايَٰتِنَا وَلِقَآئِ ٱلْـَٔاخِرَةِ فَأُو۟لَٰٓئِكَ فِى ٱلْعَذَابِ مُحْضَرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy16. እነዚያም በአላህ የካዱትማ በአናቅጻችንና በኋለኛይቱም ዓለም መገናኘት ያስተባበሉት እነዚያ በቅጣት ውስጥ የሚጣዱ ናቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَسُبْحَٰنَ ٱللَّهِ حِينَ تُمْسُونَ وَحِينَ تُصْبِحُونَ

Amharic Translation - Africa Academy17. አላህንም በምታመሹና በምታነጉም ጊዜ አጥሩት::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلَهُ ٱلْحَمْدُ فِى ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِ وَعَشِيًّا وَحِينَ تُظْهِرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy18. ምስጋናም በሰማያትና በምድር ውስጥ ለእርሱ ብቻ የተገባው ነው:: በሰርክም በቀትር ውስጥ በምትገቡም ጊዜ አጥሩት::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

يُخْرِجُ ٱلْحَىَّ مِنَ ٱلْمَيِّتِ وَيُخْرِجُ ٱلْمَيِّتَ مِنَ ٱلْحَىِّ وَيُحْىِ ٱلْأَرْضَ بَعْدَ مَوْتِهَا وَكَذَٰلِكَ تُخْرَجُونَ

Amharic Translation - Africa Academy19. ህያውን ከሙት ያወጣል:: ሙትንም ከህያው ያወጣል:: ምድርንም ከሞተች በኋላ ህያው ያደርጋታል:: ልክ እንደዚሁም (ከመቃብር) ትወጣላችሁ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَمِنْ ءَايَٰتِهِۦٓ أَنْ خَلَقَكُم مِّن تُرَابٍ ثُمَّ إِذَآ أَنتُم بَشَرٌ تَنتَشِرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy20. እናንተንም ከአፈር መፍጠሩ ከዚያም እናንተ ወዲያውኑ የምትበታተኑ ሰዎች መሆናችሁ ከአስደናቂ ምልክቶቹ ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَمِنْ ءَايَٰتِهِۦٓ أَنْ خَلَقَ لَكُم مِّنْ أَنفُسِكُمْ أَزْوَٰجًا لِّتَسْكُنُوٓا۟ إِلَيْهَا وَجَعَلَ بَيْنَكُم مَّوَدَّةً وَرَحْمَةً إِنَّ فِى ذَٰلِكَ لَـَٔايَٰتٍ لِّقَوْمٍ يَتَفَكَّرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy21. ለእናንተም ከነፍሶቻችሁ ሚስቶችን ወደ እነርሱ ትረኩ ዘንድ መፍጠሩ በመካከላችሁም ፍቅርንና እዝነትን ማድረጉ ከአስደናቂ ምልክቶቹ ነው:: በዚህ ውስጥ ለሚያስተውሉ ህዝቦች ሁሉ አያሌ ተዐምራት አሉበት::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَمِنْ ءَايَٰتِهِۦ خَلْقُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِ وَٱخْتِلَٰفُ أَلْسِنَتِكُمْ وَأَلْوَٰنِكُمْ إِنَّ فِى ذَٰلِكَ لَـَٔايَٰتٍ لِّلْعَٰلِمِينَ

Amharic Translation - Africa Academy22. ሰማያትንና ምድርን መፍጠሩ የቋንቋዎቻችሁና የመልኮቻችሁም መለያየት ከአስደናቂ ምልክቶቹ ነው:: በዚህ ውስጥ ለአዋቂዎች አያሌ ታዐምራት አሉበት::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَمِنْ ءَايَٰتِهِۦ مَنَامُكُم بِٱلَّيْلِ وَٱلنَّهَارِ وَٱبْتِغَآؤُكُم مِّن فَضْلِهِۦٓ إِنَّ فِى ذَٰلِكَ لَـَٔايَٰتٍ لِّقَوْمٍ يَسْمَعُونَ

Amharic Translation - Africa Academy23. በሌሊትም ሆነ በቀን መተኛታችሁ ከችሮታዉም መፈለጋችሁም ከምልክቶቹ ነው:: በዚህ ውስጥ ለሚሰሙ ህዝቦች ሁሉ ብዙ ታዐምራት አሉበት::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَمِنْ ءَايَٰتِهِۦ يُرِيكُمُ ٱلْبَرْقَ خَوْفًا وَطَمَعًا وَيُنَزِّلُ مِنَ ٱلسَّمَآءِ مَآءً فَيُحْىِۦ بِهِ ٱلْأَرْضَ بَعْدَ مَوْتِهَآ إِنَّ فِى ذَٰلِكَ لَـَٔايَٰتٍ لِّقَوْمٍ يَعْقِلُونَ

Amharic Translation - Africa Academy24. ብልጭታንም ፈሪዎችና ከጃዮች ስትሆኑ ለእናንተ ማሳየቱ ከሰማይም ውሃን ማውረዱ በእርሱም ምድርን ከሞተች በኋላ ህያው ማድረጉ ከአስደናቂ ምልክቶቹ ነው:: በዚህ ውስጥ ለሚያስቡ ህዝቦች ሁሉ አያሌ ታዐምራት አሉበት::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَمِنْ ءَايَٰتِهِۦٓ أَن تَقُومَ ٱلسَّمَآءُ وَٱلْأَرْضُ بِأَمْرِهِۦ ثُمَّ إِذَا دَعَاكُمْ دَعْوَةً مِّنَ ٱلْأَرْضِ إِذَآ أَنتُمْ تَخْرُجُونَ

Amharic Translation - Africa Academy25. ሰማይና ምድርም ያለ ምሰሶ በትእዛዙ መቆማቸው ከዚያም መልአክ ለትንሳኤ ከምድር ጥሪን በጠራችሁ ጊዜ እናንተ ወዲያውኑ የምትወጡ መሆናችሁ ከአስደናቂ ምልክቶቹ ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلَهُۥ مَن فِى ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِ كُلٌّ لَّهُۥ قَٰنِتُونَ

Amharic Translation - Africa Academy26. በሰማያትና በምድር ውስጥ ያለው ሁሉ የእርሱ ብቻ ነው:: ሁሉም ለእርሱ ታዛዦች ናቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَهُوَ ٱلَّذِى يَبْدَؤُا۟ ٱلْخَلْقَ ثُمَّ يُعِيدُهُۥ وَهُوَ أَهْوَنُ عَلَيْهِ وَلَهُ ٱلْمَثَلُ ٱلْأَعْلَىٰ فِى ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِ وَهُوَ ٱلْعَزِيزُ ٱلْحَكِيمُ

Amharic Translation - Africa Academy27. እርሱ ያ ፍጡራንን ከምንም የሚጀምር (የሚያስገኝ) ከዚያም የሚመልሳቸው ብቸኛ አምላክ ነው:: መመለሱም በእርሱ ላይ በጣም ቀላል ነው:: ለእርሱም በሰማያትና በምድር ከፍተኛው ምሳሌ (ባህሪ) አለው:: እርሱም ሁሉን አሸናፊና ጥበበኛ ነው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ضَرَبَ لَكُم مَّثَلًا مِّنْ أَنفُسِكُمْ هَل لَّكُم مِّن مَّا مَلَكَتْ أَيْمَٰنُكُم مِّن شُرَكَآءَ فِى مَا رَزَقْنَٰكُمْ فَأَنتُمْ فِيهِ سَوَآءٌ تَخَافُونَهُمْ كَخِيفَتِكُمْ أَنفُسَكُمْ كَذَٰلِكَ نُفَصِّلُ ٱلْـَٔايَٰتِ لِقَوْمٍ يَعْقِلُونَ

Amharic Translation - Africa Academy28. (ጣዖት አምላኪዎች ሆይ!) ለእናንተ ከነፍሶቻችሁ የሆነን ምሳሌ አደረገላችሁ:: እርሱም እጆቻችሁ ከያዟቸው ባሮች ውስጥ በሰጠናችሁ ጸጋ ለእናንተ ተጋሪዎች አሏችሁን? ታዲያ እናንተና እነርሱ በእርሱ እኩል ለኩል (ትክክል) ናችሁን? ነፍሶቻችሁን (ብጤዎቻችሁን) እንደምትፈሩ ትፈሯቸዋላችሁን ? ልክ እንደዚሁ ለሚያስተውሉ ህዝቦች ሁሉ አናቅጽን እንገልጻለን::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

بَلِ ٱتَّبَعَ ٱلَّذِينَ ظَلَمُوٓا۟ أَهْوَآءَهُم بِغَيْرِ عِلْمٍ فَمَن يَهْدِى مَنْ أَضَلَّ ٱللَّهُ وَمَا لَهُم مِّن نَّٰصِرِينَ

Amharic Translation - Africa Academy29. ይልቁንም እነዚህ የበደሉ ሰዎች ያለ ዕውቀት ዝንባሌዎቻቸውን ተከተሉ:: አላህም ያጠመመውን ሰው የሚያቀናው ማነው? ለእነርሱም ከረዳቶች ምንም የላቸዉም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَأَقِمْ وَجْهَكَ لِلدِّينِ حَنِيفًا فِطْرَتَ ٱللَّهِ ٱلَّتِى فَطَرَ ٱلنَّاسَ عَلَيْهَا لَا تَبْدِيلَ لِخَلْقِ ٱللَّهِ ذَٰلِكَ ٱلدِّينُ ٱلْقَيِّمُ وَلَٰكِنَّ أَكْثَرَ ٱلنَّاسِ لَا يَعْلَمُونَ

Amharic Translation - Africa Academy30. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ወደ እውነት ተዘንባይ ሆነህም ፊትህን ለሃይማኖት ቀጥ አድርግ:: የአላህን ፍጥረት ያችን አላህ ሰዎችን በርሷ ላይ የፈጠረባትን ሃይማኖት (ያዟት):: የአላህን ፍጥረት መለወጥ የለም:: ይህ ቀጥተኛው ሃይማኖት ነው:: ግን አብዛኞቹ ሰዎች አያውቁም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

مُنِيبِينَ إِلَيْهِ وَٱتَّقُوهُ وَأَقِيمُوا۟ ٱلصَّلَوٰةَ وَلَا تَكُونُوا۟ مِنَ ٱلْمُشْرِكِينَ

Amharic Translation - Africa Academy31. ወደ እርሱ ተመላሾች ሆናችሁ የአላህን ሃይማኖት ያዙ:: ፍሩትም:: ሶላትንም አስተካክላችሁ ስገዱ:: ከአጋሪዎችም አትሁኑ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

مِنَ ٱلَّذِينَ فَرَّقُوا۟ دِينَهُمْ وَكَانُوا۟ شِيَعًا كُلُّ حِزْبٍۭ بِمَا لَدَيْهِمْ فَرِحُونَ

Amharic Translation - Africa Academy32. ከእነዚያ ሃይማኖታቸውን ከለያዩትና ክፍልፍልም ከሆኑት አትሁኑ:: ህዝብ ሁሉ እነርሱ ዘንድ ባለው ነገር ብቻ ተደሳቾች ናቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَإِذَا مَسَّ ٱلنَّاسَ ضُرٌّ دَعَوْا۟ رَبَّهُم مُّنِيبِينَ إِلَيْهِ ثُمَّ إِذَآ أَذَاقَهُم مِّنْهُ رَحْمَةً إِذَا فَرِيقٌ مِّنْهُم بِرَبِّهِمْ يُشْرِكُونَ

Amharic Translation - Africa Academy33. ሰዎችንም ችግር ባገኛቸው ጊዜ ጌታቸውን ወደ እርሱ ተመላሾች ሆነው ይጠሩታል:: ከዚያም ከእርሱ ችሮታንም ባቀመሳቸው ጊዜ ከእነርሱ ከፊሎቹ ወዲያውኑ በጌታቸው ጣዖትን ያጋራሉ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

لِيَكْفُرُوا۟ بِمَآ ءَاتَيْنَٰهُمْ فَتَمَتَّعُوا۟ فَسَوْفَ تَعْلَمُونَ

Amharic Translation - Africa Academy34. በሰጠናቸው ጸጋ ሊክዱ (ያጋራሉ):: ተጣቀሙም:: በእርግጥም መጨረሻችሁን ወደፊት ታውቃላችሁ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَمْ أَنزَلْنَا عَلَيْهِمْ سُلْطَٰنًا فَهُوَ يَتَكَلَّمُ بِمَا كَانُوا۟ بِهِۦ يُشْرِكُونَ

Amharic Translation - Africa Academy35. በእነርሱ ላይ አላህ አስረጅን አወረደን? ታድያ እርሱ በነዚያ በእርሱ ያጋሩ በነበሩት ነገር ይናገራልን? የለም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَإِذَآ أَذَقْنَا ٱلنَّاسَ رَحْمَةً فَرِحُوا۟ بِهَا وَإِن تُصِبْهُمْ سَيِّئَةٌۢ بِمَا قَدَّمَتْ أَيْدِيهِمْ إِذَا هُمْ يَقْنَطُونَ

Amharic Translation - Africa Academy36. ሰዎችንም ችሮታን ባቀመስናቸው ጊዜ በእርሷ ይደሰታሉ:: እጆቻቸዉም ባሳለፉት ምክንያት መከራ ብታገኛቸው ወዲያውኑ እነርሱ ተስፋ ይቆርጣሉ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَوَلَمْ يَرَوْا۟ أَنَّ ٱللَّهَ يَبْسُطُ ٱلرِّزْقَ لِمَن يَشَآءُ وَيَقْدِرُ إِنَّ فِى ذَٰلِكَ لَـَٔايَٰتٍ لِّقَوْمٍ يُؤْمِنُونَ

Amharic Translation - Africa Academy37. አላህ ለሚሻው ሰው ሲሳይን የሚያሰፋ የሚያጠብም መሆኑን አያዩምን? በዚህ ውስጥ ለሚያምኑ ህዝቦች አስደናቂ ምልክቶች አሉበት::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَـَٔاتِ ذَا ٱلْقُرْبَىٰ حَقَّهُۥ وَٱلْمِسْكِينَ وَٱبْنَ ٱلسَّبِيلِ ذَٰلِكَ خَيْرٌ لِّلَّذِينَ يُرِيدُونَ وَجْهَ ٱللَّهِ وَأُو۟لَٰٓئِكَ هُمُ ٱلْمُفْلِحُونَ

Amharic Translation - Africa Academy38.ስለዚህ (አማኝ ሆይ!) የዝምድናን ባለቤት ተገቢውን ስጠው:: ለድሃም ለመንገደኛም እርዳ:: ይህ ለእነዚያ የአላህን ፊት ለሚሹ ሁሉ መልካም ነው:: እነዚያ እነርሱም በሁለተኛው ዓለም የፈለጉትን የሚያገኙ ምርጥ ክፍሎች ናቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَمَآ ءَاتَيْتُم مِّن رِّبًا لِّيَرْبُوَا۟ فِىٓ أَمْوَٰلِ ٱلنَّاسِ فَلَا يَرْبُوا۟ عِندَ ٱللَّهِ وَمَآ ءَاتَيْتُم مِّن زَكَوٰةٍ تُرِيدُونَ وَجْهَ ٱللَّهِ فَأُو۟لَٰٓئِكَ هُمُ ٱلْمُضْعِفُونَ

Amharic Translation - Africa Academy39. (ሰዎች ሆይ!) በሰዎች ውስጥም ይጨመር ዘንድ በማቀድ የምትሰጡት ገንዘብ በአላህ ዘንድ ቅንጣት አይጨምርም:: የአላህን ፊት ብቻ የምትሹ ሆናችሁ የምትሰጡት ምጽዋት ግን እነዚያ እውነተኛ ሰጪዎች (አበርካቾች) እነርሱ ናቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ٱللَّهُ ٱلَّذِى خَلَقَكُمْ ثُمَّ رَزَقَكُمْ ثُمَّ يُمِيتُكُمْ ثُمَّ يُحْيِيكُمْ هَلْ مِن شُرَكَآئِكُم مَّن يَفْعَلُ مِن ذَٰلِكُم مِّن شَىْءٍ سُبْحَٰنَهُۥ وَتَعَٰلَىٰ عَمَّا يُشْرِكُونَ

Amharic Translation - Africa Academy40. አላህ ያ የፈጠራችሁ ከዚያም ሲሳይን የሰጣችሁ ከዚያም የሚገድላችሁ ከዚያም ህያው የሚያደርጋችሁ ነው:: ከምታጋሯቸው ጣዖታት ውስጥ ከዚሃችሁ አንዳችን የሚሰራ አለን? ለአላህ ጥራት ይገባው በእርሱ ከሚያጋሩትም ሁሉ ላቀ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ظَهَرَ ٱلْفَسَادُ فِى ٱلْبَرِّ وَٱلْبَحْرِ بِمَا كَسَبَتْ أَيْدِى ٱلنَّاسِ لِيُذِيقَهُم بَعْضَ ٱلَّذِى عَمِلُوا۟ لَعَلَّهُمْ يَرْجِعُونَ

Amharic Translation - Africa Academy41. የሰዎች እጆች በሰሩት ኃጢአት ምክንያት የዚያን የሰሩትን ከፊሉን ያቀምሳቸው ዘንድ መከራው በየብስና በባህር ተገለጠ (ተሰራጨ)። እነርሱ ሊመለሱ ይከጀላልና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قُلْ سِيرُوا۟ فِى ٱلْأَرْضِ فَٱنظُرُوا۟ كَيْفَ كَانَ عَٰقِبَةُ ٱلَّذِينَ مِن قَبْلُ كَانَ أَكْثَرُهُم مُّشْرِكِينَ

Amharic Translation - Africa Academy42. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «በምድር ላይ ሂዱ የእነዚያንም በፊት የነበሩት ሰዎች መጨረሻ እንዴት እንደነበረ ተመልከቱ።» በላቸው:: አብዛኞቻቸው አጋሪዎች ነበሩ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَأَقِمْ وَجْهَكَ لِلدِّينِ ٱلْقَيِّمِ مِن قَبْلِ أَن يَأْتِىَ يَوْمٌ لَّا مَرَدَّ لَهُۥ مِنَ ٱللَّهِ يَوْمَئِذٍ يَصَّدَّعُونَ

Amharic Translation - Africa Academy43. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ለእርሱ መመለስ የሌለው ቀን የትንሳኤ ቀን ከአላህ ሳይመጣ በፊት ፊትህን ወደ ቀጥተኛው ሃይማኖት ቀጥ አድርግ :: በዚያ ቀን ወደ ገነትና ወደ እሳት ይለያያሉ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

مَن كَفَرَ فَعَلَيْهِ كُفْرُهُۥ وَمَنْ عَمِلَ صَٰلِحًا فَلِأَنفُسِهِمْ يَمْهَدُونَ

Amharic Translation - Africa Academy44. በአላህ የካደ ሰው የክህደቱ ጠንቁ በእርሱው ላይ ብቻ ነው:: መልካምም የሰሩ ሁሉ ለነፍሶቻቸው ማረፊያዎችን ያዘጋጃሉ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

لِيَجْزِىَ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ وَعَمِلُوا۟ ٱلصَّٰلِحَٰتِ مِن فَضْلِهِۦٓ إِنَّهُۥ لَا يُحِبُّ ٱلْكَٰفِرِينَ

Amharic Translation - Africa Academy45. እነዚያን ያመኑትንና መልካሞችንም የሰሩትን ከችሮታው ይመነዳ ዘንድ (ይለያያሉ):: እርሱ ከሓዲያንን አይወድምና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَمِنْ ءَايَٰتِهِۦٓ أَن يُرْسِلَ ٱلرِّيَاحَ مُبَشِّرَٰتٍ وَلِيُذِيقَكُم مِّن رَّحْمَتِهِۦ وَلِتَجْرِىَ ٱلْفُلْكُ بِأَمْرِهِۦ وَلِتَبْتَغُوا۟ مِن فَضْلِهِۦ وَلَعَلَّكُمْ تَشْكُرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy46. (ሰዎች ሆይ!) ንፋሶችንም (በዝናብ) ልታበስራችሁ ከችሮታዉም (በእርሷ) ሊያቀምሳችሁ መርከቦችም በትእዛዙ እንዲንሻለሉ ከችሮታዉም እንድትፈልጉ ታመሰግኑትም ዘንድ መላኩ ከአስደናቂ ምልክቶቹ ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلَقَدْ أَرْسَلْنَا مِن قَبْلِكَ رُسُلًا إِلَىٰ قَوْمِهِمْ فَجَآءُوهُم بِٱلْبَيِّنَٰتِ فَٱنتَقَمْنَا مِنَ ٱلَّذِينَ أَجْرَمُوا۟ وَكَانَ حَقًّا عَلَيْنَا نَصْرُ ٱلْمُؤْمِنِينَ

Amharic Translation - Africa Academy47. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ካንተ በፊትም መልዕክተኞችን ወደ የህዝቦቻቸው በእርግጥ ላክን:: በግልጽ ማስረጃዎችም መጡባቸው:: ከእነዚያ ካመጹትም ተበቀልን:: ምዕመናኖችንም መርዳት በእኛ ላይ ተገቢ ሆነ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ٱللَّهُ ٱلَّذِى يُرْسِلُ ٱلرِّيَٰحَ فَتُثِيرُ سَحَابًا فَيَبْسُطُهُۥ فِى ٱلسَّمَآءِ كَيْفَ يَشَآءُ وَيَجْعَلُهُۥ كِسَفًا فَتَرَى ٱلْوَدْقَ يَخْرُجُ مِنْ خِلَٰلِهِۦ فَإِذَآ أَصَابَ بِهِۦ مَن يَشَآءُ مِنْ عِبَادِهِۦٓ إِذَا هُمْ يَسْتَبْشِرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy48. አላህ ያ ! ንፋሶችን የሚልክ ነው:: ደመናንም ይቀሰቅሳል:: በሰማይ ላይም እንደሚሻ ይዘረጋዋል :: ቁርጥራጮችም ያደርገዋል:: ዝናቡንም ከደመናው መካከል ሲወጣ ታያለህ:: በእርሱም ከባሮቹ የሚሻውን በለየ ጊዜ ወዲያውኑ እነርሱ ይደሰታሉ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَإِن كَانُوا۟ مِن قَبْلِ أَن يُنَزَّلَ عَلَيْهِم مِّن قَبْلِهِۦ لَمُبْلِسِينَ

Amharic Translation - Africa Academy49. በእነርሱም ላይ ከመውረዱ በፊት ከእርሱ በፊት በእርግጥ ተስፋ ቆራጮች ነበሩ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَٱنظُرْ إِلَىٰٓ ءَاثَٰرِ رَحْمَتِ ٱللَّهِ كَيْفَ يُحْىِ ٱلْأَرْضَ بَعْدَ مَوْتِهَآ إِنَّ ذَٰلِكَ لَمُحْىِ ٱلْمَوْتَىٰ وَهُوَ عَلَىٰ كُلِّ شَىْءٍ قَدِيرٌ

Amharic Translation - Africa Academy50. ምድርንም ከሞተች በኋላ እንዴት ህያው እንደሚያደርጋት ወደ አላህ ችሮታ ፈለጎች ተመልከት:: ይህን አድራጊ ጌታ ሙታንንም በእርግጥ ህያው አድራጊ ነው :: እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነውና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلَئِنْ أَرْسَلْنَا رِيحًا فَرَأَوْهُ مُصْفَرًّا لَّظَلُّوا۟ مِنۢ بَعْدِهِۦ يَكْفُرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy51. ንፋስንም በአዝመራዎች ላይ ብንልክና ገርጥቶ ቢያዩት ከእርሱ በኋላ በእርግጥ ችሮታውን የሚክዱ ይሆናሉ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَإِنَّكَ لَا تُسْمِعُ ٱلْمَوْتَىٰ وَلَا تُسْمِعُ ٱلصُّمَّ ٱلدُّعَآءَ إِذَا وَلَّوْا۟ مُدْبِرِينَ

Amharic Translation - Africa Academy52. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አንተም ሙታንን አታሰማም:: ደንቆሮዎችንም ዟሪዎች ሆነው በሸሹ ጊዜ ጥሪን አታሰማም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَمَآ أَنتَ بِهَٰدِ ٱلْعُمْىِ عَن ضَلَٰلَتِهِمْ إِن تُسْمِعُ إِلَّا مَن يُؤْمِنُ بِـَٔايَٰتِنَا فَهُم مُّسْلِمُونَ

Amharic Translation - Africa Academy53. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አንተ እውሮችንም ከጥመታቸው የምታቀና አይደለህም:: በአናቅጻችን የሚያምኑትን ሰዎች እንጂ ሌላን አታሰማም:: እነርሱም ታዛዦች ናቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ٱللَّهُ ٱلَّذِى خَلَقَكُم مِّن ضَعْفٍ ثُمَّ جَعَلَ مِنۢ بَعْدِ ضَعْفٍ قُوَّةً ثُمَّ جَعَلَ مِنۢ بَعْدِ قُوَّةٍ ضَعْفًا وَشَيْبَةً يَخْلُقُ مَا يَشَآءُ وَهُوَ ٱلْعَلِيمُ ٱلْقَدِيرُ

Amharic Translation - Africa Academy54. (ሰዎች ሆይ!) አላህ ያ ከደካማ ፍትወት ጠብታ የፈጠራችሁ ነው:: ከዚያ ከደካማነት በኋላም ኃይልን አደረገ:: ከዚያም ከብርቱነት በኋላ ደካማነትና ሽበትንም አደረገ:: የሚሻውን ይፈጥራል:: እርሱም ሁሉን አዋቂውና ቻዩ ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَيَوْمَ تَقُومُ ٱلسَّاعَةُ يُقْسِمُ ٱلْمُجْرِمُونَ مَا لَبِثُوا۟ غَيْرَ سَاعَةٍ كَذَٰلِكَ كَانُوا۟ يُؤْفَكُونَ

Amharic Translation - Africa Academy55. ሰዓቲቱ በምትከሰትበት ቀን ከሓዲያን «ከአንዲት ሰዓት በስተቀር በመቃብር (በዱንያ) አልቆየንም።» ብለው ይምላሉ:: ልክ እንደዚሁ በዚህኛው ዐለምም እያሉ ከእውነት ይመለሱ ነበር::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَقَالَ ٱلَّذِينَ أُوتُوا۟ ٱلْعِلْمَ وَٱلْإِيمَٰنَ لَقَدْ لَبِثْتُمْ فِى كِتَٰبِ ٱللَّهِ إِلَىٰ يَوْمِ ٱلْبَعْثِ فَهَٰذَا يَوْمُ ٱلْبَعْثِ وَلَٰكِنَّكُمْ كُنتُمْ لَا تَعْلَمُونَ

Amharic Translation - Africa Academy56. እነዚያም እውቀትንና እምነትን የተሰጡት «በአላህ መጽሐፍ ፍርድ እስከ ትንሳኤ ቀን በእርግጥ ቆያችሁ ይህም የካዳችሁት የትንሳኤ ቀን ነው:: ግን እናንተ የማታውቁ ነበራችሁ።» ይሏቸዋል::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَيَوْمَئِذٍ لَّا يَنفَعُ ٱلَّذِينَ ظَلَمُوا۟ مَعْذِرَتُهُمْ وَلَا هُمْ يُسْتَعْتَبُونَ

Amharic Translation - Africa Academy57. በዚያም ቀን እነዚያን የበደሉትን ማመካኘታቸው አይጠቅማቸዉም:: እነርሱም በወቀሳ አይታለፉም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلَقَدْ ضَرَبْنَا لِلنَّاسِ فِى هَٰذَا ٱلْقُرْءَانِ مِن كُلِّ مَثَلٍ وَلَئِن جِئْتَهُم بِـَٔايَةٍ لَّيَقُولَنَّ ٱلَّذِينَ كَفَرُوٓا۟ إِنْ أَنتُمْ إِلَّا مُبْطِلُونَ

Amharic Translation - Africa Academy58. በዚህም ቁርኣን ውስጥ ለሰዎች የምሳሌ አይነቶችን ሁሉ በእርግጥ ገለጽን:: በተዓምርን ብታመጣላቸው እንኳን እነዚያ በአላህ የካዱት ሰዎች «እናንተ አበላሺዎች የጥፋት ተጣሪ ዎች እንጂ ሌላ አይደላችሁም።» ይላሉ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

كَذَٰلِكَ يَطْبَعُ ٱللَّهُ عَلَىٰ قُلُوبِ ٱلَّذِينَ لَا يَعْلَمُونَ

Amharic Translation - Africa Academy59 ልክ እንደዚሁ አላህ በነዚያ በማያውቁት ሰዎች ልቦች ላይ ያትማል::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَٱصْبِرْ إِنَّ وَعْدَ ٱللَّهِ حَقٌّ وَلَا يَسْتَخِفَّنَّكَ ٱلَّذِينَ لَا يُوقِنُونَ

Amharic Translation - Africa Academy60. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ስለዚህ ታገሥ:: የአላህ ቀጠሮ እውነት ነውና:: እነዚያም በትንሳኤ የማያረጋግጡት ሰዎች አያቅልሉህ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70