أَوَلَمْ يَسِيرُوا۟ فِى ٱلْأَرْضِ فَيَنظُرُوا۟ كَيْفَ كَانَ عَٰقِبَةُ ٱلَّذِينَ مِن قَبْلِهِمْ كَانُوٓا۟ أَشَدَّ مِنْهُمْ قُوَّةً وَأَثَارُوا۟ ٱلْأَرْضَ وَعَمَرُوهَآ أَكْثَرَ مِمَّا عَمَرُوهَا وَجَآءَتْهُمْ رُسُلُهُم بِٱلْبَيِّنَٰتِ فَمَا كَانَ ٱللَّهُ لِيَظْلِمَهُمْ وَلَٰكِن كَانُوٓا۟ أَنفُسَهُمْ يَظْلِمُونَ
Amharic Translation - Africa Academy9. በምድር ላይ አይሄዱምና የእነዚያን ከበፊታቸው የነበሩትን ሰዎች ፍፃሜ እንዴት እንደነበር አይመለከቱምን? በኃይል ከእነርሱ ይበልጡ ነበሩ:: ምድርንም አረሱ:: እነዚህ ከአለሟትም የበለጠ አለሟት:: መልዕክተኞቻቸዉም በተአምራቶች መጡባቸው:: ግና አስተባበሉና ጠፉ:: አላህም የሚበድላቸው አልነበረም:: ግና ነፍሶቻቸውን በራሳቸው ይበድሉ ነበር::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqበምድር ላይ አይኼዱምና የእነዚያን ከበፊታቸው የነበሩትን ሰዎች ፍጻሜ እንዴት እንደነበረ አይመለከቱምን? በኀይል ከእነርሱም ይበልጥ የጠነከሩ ነበሩ፡፡ ምድርንም አረሱ፡፡ (እነዚህ) ከአለሟትም የበዛ አለሟት፡፡ መልዕክተኞቻቸውም በተዓምራቶች መጡባቸው፤ (አስተባበሉምና ጠፉ)፡፡ አላህም የሚበድላቸው አልነበረም፤ ግን ነፍሶቻቸውን ይበድሉ ነበሩ፡፡