ሱረቱ Al-Ankaboot العنكبوت
69 አንቀጾች · መካ · የወረደበት ቅደም ተከተል 85
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ الٓمٓ
Amharic Translation - Africa Academy1. አሊፍ፤ ላም፤ ሚይም፤
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَحَسِبَ ٱلنَّاسُ أَن يُتْرَكُوٓا۟ أَن يَقُولُوٓا۟ ءَامَنَّا وَهُمْ لَا يُفْتَنُونَ
Amharic Translation - Africa Academy2. ሰዎቹ አምነናል በማለታቸው ብቻ (ከአላህ በልዩ ልዩ ነገሮች) ሳይፈተኑ የሚተው መሰላቸውን?
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلَقَدْ فَتَنَّا ٱلَّذِينَ مِن قَبْلِهِمْ فَلَيَعْلَمَنَّ ٱللَّهُ ٱلَّذِينَ صَدَقُوا۟ وَلَيَعْلَمَنَّ ٱلْكَٰذِبِينَ
Amharic Translation - Africa Academy3. እነዚያን ከእነርሱ በፊት የነበሩትንም ህዝቦች በርግጥ ፈትነናል። እነዚያን እውነት የተናገሩትን አላህ በእርግጥ ያውቃል። ውሸታሞችንም ያውቃል።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَمْ حَسِبَ ٱلَّذِينَ يَعْمَلُونَ ٱلسَّيِّـَٔاتِ أَن يَسْبِقُونَا سَآءَ مَا يَحْكُمُونَ
Amharic Translation - Africa Academy4.ይልቁንም እነዚያ መጥፎዎችን ሥራዎች የሚሠሩት ሰዎች የሚያመልጡን መሰላቸውን? ያ የሚፈርዱት ፍርድ ከፋ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
مَن كَانَ يَرْجُوا۟ لِقَآءَ ٱللَّهِ فَإِنَّ أَجَلَ ٱللَّهِ لَـَٔاتٍ وَهُوَ ٱلسَّمِيعُ ٱلْعَلِيمُ
Amharic Translation - Africa Academy5. የአላህን መገናኘት ተስፋ የሚያደርግ ሰው ሁሉ የአላህ ቀጠሮ በእርግጥ መጪ ነው:: እርሱም ሰሚም ሁሉን አዋቂ ነው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَمَن جَٰهَدَ فَإِنَّمَا يُجَٰهِدُ لِنَفْسِهِۦٓ إِنَّ ٱللَّهَ لَغَنِىٌّ عَنِ ٱلْعَٰلَمِينَ
Amharic Translation - Africa Academy6. በአላህ መንገድ ላይ የታገለ ሰው የሚታገለው ለነፍሱ ብቻ ነው:: አላህ ከዓለማት ሁሉ በእርግጥ የተብቃቃ ነውና::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ وَعَمِلُوا۟ ٱلصَّٰلِحَٰتِ لَنُكَفِّرَنَّ عَنْهُمْ سَيِّـَٔاتِهِمْ وَلَنَجْزِيَنَّهُمْ أَحْسَنَ ٱلَّذِى كَانُوا۟ يَعْمَلُونَ
Amharic Translation - Africa Academy7. እነዚያም በአላህና በመልዕክተኛው ያመኑና መልካም ተግባራትንም የሠሩ መጥፎ ሥራዎቻቸውን ከእነርሱ ላይ እናብስላቸዋለን። በዚያም ይሠሩት በነበሩት መልካም ሥራ በእርግጥ እንመነዳቸዋለን።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَوَصَّيْنَا ٱلْإِنسَٰنَ بِوَٰلِدَيْهِ حُسْنًا وَإِن جَٰهَدَاكَ لِتُشْرِكَ بِى مَا لَيْسَ لَكَ بِهِۦ عِلْمٌ فَلَا تُطِعْهُمَآ إِلَىَّ مَرْجِعُكُمْ فَأُنَبِّئُكُم بِمَا كُنتُمْ تَعْمَلُونَ
Amharic Translation - Africa Academy8. የሰውን ልጅ ለወላጆቹ መልካም ተግባርን ሁሉ እንዲፈጽም አዘዝነው:: ወላጆችም ላንተም በእርሱ እውቀት የሌለህን ጣኦት በእኔ እንድታጋራው ቢያስገድዱህ አትታዘዛቸው:: መመለሻችሁ ወደ እኔ ነው:: ከዚያም ትሠሩት የነበራችሁትን ሁሉ እነግራችኋለሁ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ وَعَمِلُوا۟ ٱلصَّٰلِحَٰتِ لَنُدْخِلَنَّهُمْ فِى ٱلصَّٰلِحِينَ
Amharic Translation - Africa Academy9. እነዚያንም በአላህ ያመኑና መልካም ሥራዎችን የሠሩ ሁሉ ከደጋጎቹ ውስጥ በእርግጥ እናስገባቸዋለን::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَمِنَ ٱلنَّاسِ مَن يَقُولُ ءَامَنَّا بِٱللَّهِ فَإِذَآ أُوذِىَ فِى ٱللَّهِ جَعَلَ فِتْنَةَ ٱلنَّاسِ كَعَذَابِ ٱللَّهِ وَلَئِن جَآءَ نَصْرٌ مِّن رَّبِّكَ لَيَقُولُنَّ إِنَّا كُنَّا مَعَكُمْ أَوَلَيْسَ ٱللَّهُ بِأَعْلَمَ بِمَا فِى صُدُورِ ٱلْعَٰلَمِينَ
Amharic Translation - Africa Academy10. ከሰዎች መካከል «በአላህ አመንን።» የሚል ሰው አለ:: ከዚያ በአላህ በማመኑ ምክኒያት በተሰቃየ ጊዜ የሰዎችን ማሰቃየት እንደ አላህ ቅጣት ያደርጋል:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከጌታህም እርዳታ ቢመጣ እኛ በእርግጥ ከናንተ ጋር ነበርን ይላሉ:: አላህ በዓለማት ሕዝብ ልቦች ውስጥ ያለውን ሁሉ አዋቂ አይደለምን?
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلَيَعْلَمَنَّ ٱللَّهُ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ وَلَيَعْلَمَنَّ ٱلْمُنَٰفِقِينَ
Amharic Translation - Africa Academy11. አላህ እነዚያንም በትክክል ያመኑትን በእርግጥ ያውቃል:: መናፍቆቹንም ያውቃል::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَقَالَ ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ لِلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ ٱتَّبِعُوا۟ سَبِيلَنَا وَلْنَحْمِلْ خَطَٰيَٰكُمْ وَمَا هُم بِحَٰمِلِينَ مِنْ خَطَٰيَٰهُم مِّن شَىْءٍ إِنَّهُمْ لَكَٰذِبُونَ
Amharic Translation - Africa Academy12. እነዚያንም የካዱት ሰዎች ለእነዚያ ላመኑት «መንገዳችንን ተከተሉ:: ኃጢአቶቻችሁንም እንሸከማለን» አሉ:: እነርሱም ከኃጢአቶቻቸው ምንንም ተሸካሚዎች አይደሉም:: እነርሱ በእርግጥ ውሸታሞች ናቸው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلَيَحْمِلُنَّ أَثْقَالَهُمْ وَأَثْقَالًا مَّعَ أَثْقَالِهِمْ وَلَيُسْـَٔلُنَّ يَوْمَ ٱلْقِيَٰمَةِ عَمَّا كَانُوا۟ يَفْتَرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy13. ሸክሞቻቸውንና ከሸክሞቻቸው ጋር ሌሎች ሸክሞችንም በእርግጥ ይሸከማሉ:: በትንሳኤም ቀን ይቀጥፉት ከነበሩት ሁሉ በእርግጥ ይጠየቃሉ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلَقَدْ أَرْسَلْنَا نُوحًا إِلَىٰ قَوْمِهِۦ فَلَبِثَ فِيهِمْ أَلْفَ سَنَةٍ إِلَّا خَمْسِينَ عَامًا فَأَخَذَهُمُ ٱلطُّوفَانُ وَهُمْ ظَٰلِمُونَ
Amharic Translation - Africa Academy14. ኑሕንም ወደ ህዝቦቹ በእርግጥ ላክነው:: በውስጣቸዉም ሺህ ዓመትን ሀምሳ ዓመት ሲቀር ተቀመጠ:: እነርሱ በዳዮች ሆነዉም የውሃው ማዕበል አጥለቀለቃቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَأَنجَيْنَٰهُ وَأَصْحَٰبَ ٱلسَّفِينَةِ وَجَعَلْنَٰهَآ ءَايَةً لِّلْعَٰلَمِينَ
Amharic Translation - Africa Academy15. ኑህንና የመርከቢቱን ጓዶች አዳንናቸው:: እርሷንም ለዓለማት ተዓምር አደረግናት::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَإِبْرَٰهِيمَ إِذْ قَالَ لِقَوْمِهِ ٱعْبُدُوا۟ ٱللَّهَ وَٱتَّقُوهُ ذَٰلِكُمْ خَيْرٌ لَّكُمْ إِن كُنتُمْ تَعْلَمُونَ
Amharic Translation - Africa Academy16. መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ! ኢብራሒም ለሕዝቦቹ ባለ ጊዜ የሆነውን (አስታውስ)። «አላህን ተገዙ ፍሩትም ይህን ማድረጋችሁ የምታውቁት ብትሆኑ ለናንተ በላጭ ነው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِنَّمَا تَعْبُدُونَ مِن دُونِ ٱللَّهِ أَوْثَٰنًا وَتَخْلُقُونَ إِفْكًا إِنَّ ٱلَّذِينَ تَعْبُدُونَ مِن دُونِ ٱللَّهِ لَا يَمْلِكُونَ لَكُمْ رِزْقًا فَٱبْتَغُوا۟ عِندَ ٱللَّهِ ٱلرِّزْقَ وَٱعْبُدُوهُ وَٱشْكُرُوا۟ لَهُۥٓ إِلَيْهِ تُرْجَعُونَ
Amharic Translation - Africa Academy17. (ሰዎች ሆይ!) ከአላህ ሌላ የምትገዙት ጣኦታትን ብቻ ነው:: ውሸትንም ትቀጥፋላችሁ:: እነዚያ ከአላህ ሌላ የምትገዟቸው ጣዖታት ለእናንተ ሲሳይን ሊሰጧችሁ አይችሉም:: ስለዚህ ሲሳይን ከአላህ ዘንድ ብቻ ፈልጉ:: ተገዙትም:: ለርሱም አመስግኑ ወደ እርሱም ትመለሳላችሁ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَإِن تُكَذِّبُوا۟ فَقَدْ كَذَّبَ أُمَمٌ مِّن قَبْلِكُمْ وَمَا عَلَى ٱلرَّسُولِ إِلَّا ٱلْبَلَٰغُ ٱلْمُبِينُ
Amharic Translation - Africa Academy18. ብታስተባብሉም ከፊታችሁ የነበሩት ህዝቦች በእርግጥ አስተባብለዋል:: በመልዕክተኛዉም ላይ ግልጽ ማድረስ እንጂ ሌላ የለበትም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَوَلَمْ يَرَوْا۟ كَيْفَ يُبْدِئُ ٱللَّهُ ٱلْخَلْقَ ثُمَّ يُعِيدُهُۥٓ إِنَّ ذَٰلِكَ عَلَى ٱللَّهِ يَسِيرٌ
Amharic Translation - Africa Academy19. አላህ መፍጠርን እንዴት እንደሚጀምርና ከዚያ እንዴት እንደሚመልሰው አይመለከቱምን? ይህ በአላህ ላይ ቀላል ነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قُلْ سِيرُوا۟ فِى ٱلْأَرْضِ فَٱنظُرُوا۟ كَيْفَ بَدَأَ ٱلْخَلْقَ ثُمَّ ٱللَّهُ يُنشِئُ ٱلنَّشْأَةَ ٱلْـَٔاخِرَةَ إِنَّ ٱللَّهَ عَلَىٰ كُلِّ شَىْءٍ قَدِيرٌ
Amharic Translation - Africa Academy20. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «በምድር ላይ ሂዱ:: እናም መፍጠርን እንዴት እንደጀመረ ተመልከቱ:: ከዚያም አላህ የመጨረሻይቱን መነሳት ያስነሳል:: አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነውና።» በላቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
يُعَذِّبُ مَن يَشَآءُ وَيَرْحَمُ مَن يَشَآءُ وَإِلَيْهِ تُقْلَبُونَ
Amharic Translation - Africa Academy21. የሚሻውን ሰው ይቀጣል:: የሚሻውንም ሰው ያዝንለታል ወደ እርሱም ትመለሳላችሁ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَمَآ أَنتُم بِمُعْجِزِينَ فِى ٱلْأَرْضِ وَلَا فِى ٱلسَّمَآءِ وَمَا لَكُم مِّن دُونِ ٱللَّهِ مِن وَلِىٍّ وَلَا نَصِيرٍ
Amharic Translation - Africa Academy22. እናንተ በምድርም ሆነ በሰማይ የምታቅቱ አይደላችሁም። ከአላህም ሌላ ወዳጅም ተከላካይም ምንም የላችሁም።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ بِـَٔايَٰتِ ٱللَّهِ وَلِقَآئِهِۦٓ أُو۟لَٰٓئِكَ يَئِسُوا۟ مِن رَّحْمَتِى وَأُو۟لَٰٓئِكَ لَهُمْ عَذَابٌ أَلِيمٌ
Amharic Translation - Africa Academy23. እነዚያም በአላህ አናቅጽና በመገናኘቱ የካዱ እነዚያ ከእዝነቴ ተስፋን ቆረጡ:: እነዚያም ለእነርሱ አሳማሚ ቅጣት አለባቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَمَا كَانَ جَوَابَ قَوْمِهِۦٓ إِلَّآ أَن قَالُوا۟ ٱقْتُلُوهُ أَوْ حَرِّقُوهُ فَأَنجَىٰهُ ٱللَّهُ مِنَ ٱلنَّارِ إِنَّ فِى ذَٰلِكَ لَـَٔايَٰتٍ لِّقَوْمٍ يُؤْمِنُونَ
Amharic Translation - Africa Academy24. የህዝቦቹም መልስ፡- «ግደሉት ወይም አቃጥሉት።» ማለት እንጂ ሌላ አልነበረም። ከዚያም ከእሳቲቱ አላህ አዳነው። በዚህ ውስጥ ለሚያምኑ ሕዝቦች ብዙ ተዐምራት አሉበት።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَقَالَ إِنَّمَا ٱتَّخَذْتُم مِّن دُونِ ٱللَّهِ أَوْثَٰنًا مَّوَدَّةَ بَيْنِكُمْ فِى ٱلْحَيَوٰةِ ٱلدُّنْيَا ثُمَّ يَوْمَ ٱلْقِيَٰمَةِ يَكْفُرُ بَعْضُكُم بِبَعْضٍ وَيَلْعَنُ بَعْضُكُم بَعْضًا وَمَأْوَىٰكُمُ ٱلنَّارُ وَمَا لَكُم مِّن نَّٰصِرِينَ
Amharic Translation - Africa Academy25. (ኢብራሂም) አለ፡- «ከአላህ ሌላ ጣኦታትን አማልክት የያዛችሁት በቅርቢቱ ህይወት በመካከላችሁ ለመዋደድ ብቻ ነው። ከዚያም በትንሳኤ ቀን ከፊላችሁ በከፊሉ ይክዳል:: ከፊላችሁም ከፊሉን ይረግማል:: መኖሪያችሁም እሳት ናት:: ለእናንተም ከረዳቶች ምንም የላችሁም።»
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَـَٔامَنَ لَهُۥ لُوطٌ وَقَالَ إِنِّى مُهَاجِرٌ إِلَىٰ رَبِّىٓ إِنَّهُۥ هُوَ ٱلْعَزِيزُ ٱلْحَكِيمُ
Amharic Translation - Africa Academy26. ከዚያም ሉጥ ለእርሱ አመነ:: (ኢብራሂምም) «እኔ ወደ ጌታዬ ተሰዳጅ ነኝ:: እነሆ እርሱ አላህ ሁሉን አሸናፊና ጥበበኛ ነውና።» አለ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَوَهَبْنَا لَهُۥٓ إِسْحَٰقَ وَيَعْقُوبَ وَجَعَلْنَا فِى ذُرِّيَّتِهِ ٱلنُّبُوَّةَ وَٱلْكِتَٰبَ وَءَاتَيْنَٰهُ أَجْرَهُۥ فِى ٱلدُّنْيَا وَإِنَّهُۥ فِى ٱلْـَٔاخِرَةِ لَمِنَ ٱلصَّٰلِحِينَ
Amharic Translation - Africa Academy27. ለእርሱም ኢስሐቅንና ያዕቆብን ሰጠነው በዘሩም ውስጥ ነብይነትንና መጽሐፍን አደረግን:: ምንዳውንም በቅርቢቱ ዓለም ሰጠነው:: እርሱም በመጨረሻይቱ ዓለም ከደጋጎቹ ነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلُوطًا إِذْ قَالَ لِقَوْمِهِۦٓ إِنَّكُمْ لَتَأْتُونَ ٱلْفَٰحِشَةَ مَا سَبَقَكُم بِهَا مِنْ أَحَدٍ مِّنَ ٱلْعَٰلَمِينَ
Amharic Translation - Africa Academy28. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ሉጥንም ለሕዝቦቹ ባለ ጊዜ አስታውስ: «እናንተ ጠያፍን ሥራ ትሰራላችሁን? በእርሷ ከዓለማት አንድም ሰው አልቀደማችሁም።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَئِنَّكُمْ لَتَأْتُونَ ٱلرِّجَالَ وَتَقْطَعُونَ ٱلسَّبِيلَ وَتَأْتُونَ فِى نَادِيكُمُ ٱلْمُنكَرَ فَمَا كَانَ جَوَابَ قَوْمِهِۦٓ إِلَّآ أَن قَالُوا۟ ٱئْتِنَا بِعَذَابِ ٱللَّهِ إِن كُنتَ مِنَ ٱلصَّٰدِقِينَ
Amharic Translation - Africa Academy29. «እናንተ በእርግጥ ወንዶችን ትመጣላችሁን? መንገድንም ትቆርጣላችሁን? በሸንጓችሁም የሚነወርን ነገር ትሠራላችሁን?» አላቸው:: የሕዝቦቹም መልስ «ከእውነተኞቹ እንደሆንክ የአላህን ቅጣት አምጣብን።» ማለት እንጂ ሌላ አልነበረም።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالَ رَبِّ ٱنصُرْنِى عَلَى ٱلْقَوْمِ ٱلْمُفْسِدِينَ
Amharic Translation - Africa Academy30. «ጌታዬ ሆይ! በአመጸኞች ሕዝቦች ላይ እርዳኝ።» አለ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلَمَّا جَآءَتْ رُسُلُنَآ إِبْرَٰهِيمَ بِٱلْبُشْرَىٰ قَالُوٓا۟ إِنَّا مُهْلِكُوٓا۟ أَهْلِ هَٰذِهِ ٱلْقَرْيَةِ إِنَّ أَهْلَهَا كَانُوا۟ ظَٰلِمِينَ
Amharic Translation - Africa Academy31. መልዕክተኞቻችንም ወደ ኢብራሂም በብስራት በመጡ ጊዜ «እኛ የዚችን ከተማ ሰዎች አጥፊዎች ነን ሰዎችዋ በዳዮች ነበሩና።» አሉት።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالَ إِنَّ فِيهَا لُوطًا قَالُوا۟ نَحْنُ أَعْلَمُ بِمَن فِيهَا لَنُنَجِّيَنَّهُۥ وَأَهْلَهُۥٓ إِلَّا ٱمْرَأَتَهُۥ كَانَتْ مِنَ ٱلْغَٰبِرِينَ
Amharic Translation - Africa Academy32. «በእርሷ ውስጥ ሉጥ አለ እኮ?» አላቸው:: «እኛ በውስጧ ያለውን ካንተ ይበልጥ አዋቂ ነን:: እርሱንማ በእርግጥ እናድነዋለን:: ቤተሰቦቹንም ጭምር ሚስቱ ብቻ ስትቀር እርሷ በጥፋቱ ውስጥ ከሚቀሩት ናት።» አሉት::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلَمَّآ أَن جَآءَتْ رُسُلُنَا لُوطًا سِىٓءَ بِهِمْ وَضَاقَ بِهِمْ ذَرْعًا وَقَالُوا۟ لَا تَخَفْ وَلَا تَحْزَنْ إِنَّا مُنَجُّوكَ وَأَهْلَكَ إِلَّا ٱمْرَأَتَكَ كَانَتْ مِنَ ٱلْغَٰبِرِينَ
Amharic Translation - Africa Academy33. መልዕክተኞቻችንም ወደ ሉጥ በመጡት ጊዜ በነሱ ምክንያት አዘነ:: በእነርሱም ልቡ ተጨነቀ። አሉትም: «አትፍራ። አትዘንም። እኛ አዳኞችህ ነን:: ቤተሰቦችህንም ሚስትህ ብቻ ስትቀር:: እርሷ ግን በጥፋቱ ውስጥ ከቀሪዎቹ ናት።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِنَّا مُنزِلُونَ عَلَىٰٓ أَهْلِ هَٰذِهِ ٱلْقَرْيَةِ رِجْزًا مِّنَ ٱلسَّمَآءِ بِمَا كَانُوا۟ يَفْسُقُونَ
Amharic Translation - Africa Academy34. «እኛ በዚህ ከተማ ሰዎች ላይ ያምጹ በነበሩበት ምክንያት ከሰማይ ቅጣትን አውራጆች ነን።» (አሉት)
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلَقَد تَّرَكْنَا مِنْهَآ ءَايَةًۢ بَيِّنَةً لِّقَوْمٍ يَعْقِلُونَ
Amharic Translation - Africa Academy35. በእርግጥም ለሚያስቡ ሰዎች ሁሉ ከእርሷ ግልጽ ምልክትን ተውን (አስቀረን)::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَإِلَىٰ مَدْيَنَ أَخَاهُمْ شُعَيْبًا فَقَالَ يَٰقَوْمِ ٱعْبُدُوا۟ ٱللَّهَ وَٱرْجُوا۟ ٱلْيَوْمَ ٱلْـَٔاخِرَ وَلَا تَعْثَوْا۟ فِى ٱلْأَرْضِ مُفْسِدِينَ
Amharic Translation - Africa Academy36. ወደ መድየንም ወንድማቸውን ሹዐይብን ላክን። «ህዝቦቼ ሆይ! አላህን ተገዙ:: የመጨረሻውንም ቀን ፍሩ:: በምድርም ውስጥ የምታጠፉ ሆናችሁ አታበላሹ።» አላቸው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَكَذَّبُوهُ فَأَخَذَتْهُمُ ٱلرَّجْفَةُ فَأَصْبَحُوا۟ فِى دَارِهِمْ جَٰثِمِينَ
Amharic Translation - Africa Academy37. እናም አስተባበሉትና የምድር መንቀጥቀጥ ያዘቻቸው፡፡ ባገራቸዉም ውስጥ ተንከፍረው አደሩ (አነጉ)።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَعَادًا وَثَمُودَا۟ وَقَد تَّبَيَّنَ لَكُم مِّن مَّسَٰكِنِهِمْ وَزَيَّنَ لَهُمُ ٱلشَّيْطَٰنُ أَعْمَٰلَهُمْ فَصَدَّهُمْ عَنِ ٱلسَّبِيلِ وَكَانُوا۟ مُسْتَبْصِرِينَ
Amharic Translation - Africa Academy38. ዓድንና ሠሙድንም አጠፋን:: የመኖሪያዎቻቸውን ፍርስራሾች በማየት መጥፋታቸው ለእናንተ በእውነት ተገለጠላችሁ:: ሰይጣንም ሥራዎቻቸውን ለእነርሱ ሸለመላቸው:: ከመንገድም አገዳቸው:: የማስተዋልም ባለቤቶች ነበሩ:: ግን አላስተዋሉም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَقَٰرُونَ وَفِرْعَوْنَ وَهَٰمَٰنَ وَلَقَدْ جَآءَهُم مُّوسَىٰ بِٱلْبَيِّنَٰتِ فَٱسْتَكْبَرُوا۟ فِى ٱلْأَرْضِ وَمَا كَانُوا۟ سَٰبِقِينَ
Amharic Translation - Africa Academy39. ቃሩንንም ፈርዖንንም ሃማንንም አጠፋን:: ሙሳም በተዐምራት በእርግጥ መጣባቸው:: በምድርም ላይ ኮሩ:: አምላጮችም አልነበሩም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَكُلًّا أَخَذْنَا بِذَنۢبِهِۦ فَمِنْهُم مَّنْ أَرْسَلْنَا عَلَيْهِ حَاصِبًا وَمِنْهُم مَّنْ أَخَذَتْهُ ٱلصَّيْحَةُ وَمِنْهُم مَّنْ خَسَفْنَا بِهِ ٱلْأَرْضَ وَمِنْهُم مَّنْ أَغْرَقْنَا وَمَا كَانَ ٱللَّهُ لِيَظْلِمَهُمْ وَلَٰكِن كَانُوٓا۟ أَنفُسَهُمْ يَظْلِمُونَ
Amharic Translation - Africa Academy40. ሁሉንም በኃጢአቱ ያዝነው:: ከእነርሱም ውስጥ ጠጠርን ያዘለ ነፍስን የላክንበት አለ:: ከእነርሱም ውስጥ ጩኸት የያዘችው አለ:: ከእነርሱም ውስጥ በእርሱ ምድርን የደረባንበት አለ:: ከእነርሱም ውስጥ ያሰመጥነው አለ:: አላህ የሚበድላቸው አልነበረም:: ግን ነፍሶቻቸውን የሚበድሉ ነበሩ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
مَثَلُ ٱلَّذِينَ ٱتَّخَذُوا۟ مِن دُونِ ٱللَّهِ أَوْلِيَآءَ كَمَثَلِ ٱلْعَنكَبُوتِ ٱتَّخَذَتْ بَيْتًا وَإِنَّ أَوْهَنَ ٱلْبُيُوتِ لَبَيْتُ ٱلْعَنكَبُوتِ لَوْ كَانُوا۟ يَعْلَمُونَ
Amharic Translation - Africa Academy41. የእነዚያ ከአላህ ሌላ ረዳቶችን (ጣኦታትን) የያዙ ሰዎች ምሳሌ ቤትን እንደሠራች ሸረሪት ብጤ ነው:: ከቤቶችም ሁሉ በጣም ደካማው የሸረሪት ቤት ነው:: ቢያውቁ ኖሮ አማልክት አድርገው አይገዟቸዉም ነበር::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِنَّ ٱللَّهَ يَعْلَمُ مَا يَدْعُونَ مِن دُونِهِۦ مِن شَىْءٍ وَهُوَ ٱلْعَزِيزُ ٱلْحَكِيمُ
Amharic Translation - Africa Academy42. አላህ ያንን ከእርሱ ሌላ የሚገዙትን ማንኛውንም ያውቃል:: እርሱም ሁሉን አሸናፊዉና ጥበበኛው ነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَتِلْكَ ٱلْأَمْثَٰلُ نَضْرِبُهَا لِلنَّاسِ وَمَا يَعْقِلُهَآ إِلَّا ٱلْعَٰلِمُونَ
Amharic Translation - Africa Academy43. እነዚህንም ምሳሌዎች ለሰዎች እንገልጻቸዋለን:: ከሊቃውንቶቹም በስተቀር ሌሎችአያውቋትም፡፡
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
خَلَقَ ٱللَّهُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضَ بِٱلْحَقِّ إِنَّ فِى ذَٰلِكَ لَـَٔايَةً لِّلْمُؤْمِنِينَ
Amharic Translation - Africa Academy44. አላህም ሰማያትንና ምድርን እውነተኛ ሆኖ ፈጠረ፤ በዚህ ውስጥ ለአማኞች ተዐምር አለበት።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ٱتْلُ مَآ أُوحِىَ إِلَيْكَ مِنَ ٱلْكِتَٰبِ وَأَقِمِ ٱلصَّلَوٰةَ إِنَّ ٱلصَّلَوٰةَ تَنْهَىٰ عَنِ ٱلْفَحْشَآءِ وَٱلْمُنكَرِ وَلَذِكْرُ ٱللَّهِ أَكْبَرُ وَٱللَّهُ يَعْلَمُ مَا تَصْنَعُونَ
Amharic Translation - Africa Academy45. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከመጽሐፉ ወደ አንተ የተወረደውን አንብብ:: ሶላትንም ደንቡን ጠብቀህ ስገድ:: ሶላት ከመጥፎና ከሚጠላ ነገር ሁሉ ትከለክላለችና:: አላህን ማውሳት ከመልካም ነገር ሁሉ በላጭ ነው:: አላህም የምትሠሩትን ስራ ሁሉ ያውቃል::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلَا تُجَٰدِلُوٓا۟ أَهْلَ ٱلْكِتَٰبِ إِلَّا بِٱلَّتِى هِىَ أَحْسَنُ إِلَّا ٱلَّذِينَ ظَلَمُوا۟ مِنْهُمْ وَقُولُوٓا۟ ءَامَنَّا بِٱلَّذِىٓ أُنزِلَ إِلَيْنَا وَأُنزِلَ إِلَيْكُمْ وَإِلَٰهُنَا وَإِلَٰهُكُمْ وَٰحِدٌ وَنَحْنُ لَهُۥ مُسْلِمُونَ
Amharic Translation - Africa Academy46. (እናንተ ያመናችሁ ሆይ!) ከእነርሱ እነዚያን የበደሉትን ሲቀር የመጽሐፉ ባለቤቶችን በዚያች እርሷ መልካም በሆነችው ክርክር እንጂ አትከራከሩ:። በሉም፡- «በዚያ ወደ እኛ በተወረደው ወደ እናንተም በተወረደው አመንን:: አምላካችንም አምላካችሁም አንድ ነው:: እኛም ለእርሱ ታዛዦች ነን።»
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَكَذَٰلِكَ أَنزَلْنَآ إِلَيْكَ ٱلْكِتَٰبَ فَٱلَّذِينَ ءَاتَيْنَٰهُمُ ٱلْكِتَٰبَ يُؤْمِنُونَ بِهِۦ وَمِنْ هَٰٓؤُلَآءِ مَن يُؤْمِنُ بِهِۦ وَمَا يَجْحَدُ بِـَٔايَٰتِنَآ إِلَّا ٱلْكَٰفِرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy47. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እንደዚሁም ወደ አንተ መጽሐፍን አወረድን:: እነዚያም መጽሐፍን የሰጠናቸው በእርሱ ያምናሉ:: ከእነዚህም (ከመካ) ሰዎች በእርሱ የሚያምኑ አሉ:: በተዓምራታችንም ከሓዲያን እንጂ ማንም አይክድም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَمَا كُنتَ تَتْلُوا۟ مِن قَبْلِهِۦ مِن كِتَٰبٍ وَلَا تَخُطُّهُۥ بِيَمِينِكَ إِذًا لَّٱرْتَابَ ٱلْمُبْطِلُونَ
Amharic Translation - Africa Academy48. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከእርሱ በፊትም መጽሐፍን የምታነብ በቀኝህም የምትጽፈው አልነበርክም:: ያን ጊዜ አጥፊዎቹ በእርግጥ በተጠራጠሩ ነበር::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
بَلْ هُوَ ءَايَٰتٌۢ بَيِّنَٰتٌ فِى صُدُورِ ٱلَّذِينَ أُوتُوا۟ ٱلْعِلْمَ وَمَا يَجْحَدُ بِـَٔايَٰتِنَآ إِلَّا ٱلظَّٰلِمُونَ
Amharic Translation - Africa Academy49. አይደለም:: እርሱ (ቁርኣን) በእነዚያ እውቀትን በተሰጡት ሰዎች ልቦች ውስጥ የጠለቀ ግልፆች አናቅጽ ነው:: በአናቅጻችንም በዳዮቹ እንጂ ሌላው አይክድም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَقَالُوا۟ لَوْلَآ أُنزِلَ عَلَيْهِ ءَايَٰتٌ مِّن رَّبِّهِۦ قُلْ إِنَّمَا ٱلْـَٔايَٰتُ عِندَ ٱللَّهِ وَإِنَّمَآ أَنَا۠ نَذِيرٌ مُّبِينٌ
Amharic Translation - Africa Academy50. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከሓዲያን «በእርሱ ላይ ከጌታው ዘንድ ተዐምራት ለምን አልተወረዱም?» አሉ:: »ተዐምራት ከአላህ ዘንድ ብቻ ናቸው:: እኔም ግልጽ አስፈራሪ ብቻ ነኝ።» በላቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَوَلَمْ يَكْفِهِمْ أَنَّآ أَنزَلْنَا عَلَيْكَ ٱلْكِتَٰبَ يُتْلَىٰ عَلَيْهِمْ إِنَّ فِى ذَٰلِكَ لَرَحْمَةً وَذِكْرَىٰ لِقَوْمٍ يُؤْمِنُونَ
Amharic Translation - Africa Academy51. እኛ መጽሐፉን በእነርሱ ላይ የሚነበብ ሆኖ ባንተ ላይ ማውረዳችን አይበቃቸዉምን? በዚህ ውስጥ ለሚያምኑ ሕዝቦች ሁሉ ችሮታና ግሳጼ አለበት::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قُلْ كَفَىٰ بِٱللَّهِ بَيْنِى وَبَيْنَكُمْ شَهِيدًا يَعْلَمُ مَا فِى ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِ وَٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ بِٱلْبَٰطِلِ وَكَفَرُوا۟ بِٱللَّهِ أُو۟لَٰٓئِكَ هُمُ ٱلْخَٰسِرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy52. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «በእኔና በእናንተ መካከል መስካሪ በአላህ በቃ:: በሰማያትና በምድር ያለውን ሁሉ ያውቃል።» በላቸው:: እነዚያም በብላሽ ነገር ያመኑና በአላህ የካዱ እነዚያ እነርሱ ከሳሪዎቹ ናቸው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَيَسْتَعْجِلُونَكَ بِٱلْعَذَابِ وَلَوْلَآ أَجَلٌ مُّسَمًّى لَّجَآءَهُمُ ٱلْعَذَابُ وَلَيَأْتِيَنَّهُم بَغْتَةً وَهُمْ لَا يَشْعُرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy53. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በቅጣትም ያስቸኩሉሃል! የተወሰነም ጊዜ ባልነበረ ኖሮ ቅጣቱ በመጣባቸው ነበር:: እነርሱ የማያውቁ ሲሆኑም በድንገት በእርግጥ ይመጣባቸዋል::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
يَسْتَعْجِلُونَكَ بِٱلْعَذَابِ وَإِنَّ جَهَنَّمَ لَمُحِيطَةٌۢ بِٱلْكَٰفِرِينَ
Amharic Translation - Africa Academy54. በቅጣት ያስቸኩሉሃል! ገሀነምም ከሓዲያንን በእርግጥ ከባቢ ናት::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
يَوْمَ يَغْشَىٰهُمُ ٱلْعَذَابُ مِن فَوْقِهِمْ وَمِن تَحْتِ أَرْجُلِهِمْ وَيَقُولُ ذُوقُوا۟ مَا كُنتُمْ تَعْمَلُونَ
Amharic Translation - Africa Academy55. ቅጣቱ ከበላያቸው ከእግሮቻቸዉም ሥር በሚሸፍናቸው ቀን «ትሰሩት የነበራችሁትን ቅመሱ።» በሚላቸዉም ቀን ትከባቸዋለች።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
يَٰعِبَادِىَ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓا۟ إِنَّ أَرْضِى وَٰسِعَةٌ فَإِيَّٰىَ فَٱعْبُدُونِ
Amharic Translation - Africa Academy56. እናንተ ያመናችሁ ባሮቼ ሆይ! ምድሬ በእርግጥ ሰፊ ናት:: ብትቸገሩ ተሰደዱ እኔንም ብቻ ተገዙኝ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
كُلُّ نَفْسٍ ذَآئِقَةُ ٱلْمَوْتِ ثُمَّ إِلَيْنَا تُرْجَعُونَ
Amharic Translation - Africa Academy57. ነፍስ ሁሉ ሞትን ቀማሽ ናት:: ከዚያም ወደ እኛ ትመለሳላችሁ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ وَعَمِلُوا۟ ٱلصَّٰلِحَٰتِ لَنُبَوِّئَنَّهُم مِّنَ ٱلْجَنَّةِ غُرَفًا تَجْرِى مِن تَحْتِهَا ٱلْأَنْهَٰرُ خَٰلِدِينَ فِيهَا نِعْمَ أَجْرُ ٱلْعَٰمِلِينَ
Amharic Translation - Africa Academy58. እነዚያም በአላህ ያመኑና መልካም ስራዎችን የሠሩ ከገነት በስሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸው ሰገነቶች በውስጣቸው ዘውታሪዎች ሲሆኑ በእርግጥ እናሰፍራቸዋለን:: የሠራተኞችም ምንዳ ምንኛ አማረ!
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ٱلَّذِينَ صَبَرُوا۟ وَعَلَىٰ رَبِّهِمْ يَتَوَكَّلُونَ
Amharic Translation - Africa Academy59. እነርሱ እነዚያ የታገሱ በጌታቸዉም ላይ የሚመኩ ናቸው፡
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَكَأَيِّن مِّن دَآبَّةٍ لَّا تَحْمِلُ رِزْقَهَا ٱللَّهُ يَرْزُقُهَا وَإِيَّاكُمْ وَهُوَ ٱلسَّمِيعُ ٱلْعَلِيمُ
Amharic Translation - Africa Academy60. ከተንቀሳቃሽ ፍጡራን ምግባቸውን የማይሸከሙ ብዙ ናቸው:: አላህ ይመግባቸዋል:: እናንተንም ይመግባል:: እርሱ ሰሚና አዋቂ ነውና::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلَئِن سَأَلْتَهُم مَّنْ خَلَقَ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضَ وَسَخَّرَ ٱلشَّمْسَ وَٱلْقَمَرَ لَيَقُولُنَّ ٱللَّهُ فَأَنَّىٰ يُؤْفَكُونَ
Amharic Translation - Africa Academy61. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ሰማያትንና ምድርን የፈጠረ ጸሐይንና ጨረቃንም የገራ ማን እንደሆነ ብትጠይቃቸው በእርግጥ ”አላህ ነው“ ይሉሃል:: ታዲያ እንዴት ይመለሳሉ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ٱللَّهُ يَبْسُطُ ٱلرِّزْقَ لِمَن يَشَآءُ مِنْ عِبَادِهِۦ وَيَقْدِرُ لَهُۥٓ إِنَّ ٱللَّهَ بِكُلِّ شَىْءٍ عَلِيمٌ
Amharic Translation - Africa Academy62. አላህ ከባሮቹ ለሚሻው ሲሳይን ያሰፋል:: ለእርሱም ያጠባል:: አላህ በነገሩ ሁሉ አዋቂ ነውና::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلَئِن سَأَلْتَهُم مَّن نَّزَّلَ مِنَ ٱلسَّمَآءِ مَآءً فَأَحْيَا بِهِ ٱلْأَرْضَ مِنۢ بَعْدِ مَوْتِهَا لَيَقُولُنَّ ٱللَّهُ قُلِ ٱلْحَمْدُ لِلَّهِ بَلْ أَكْثَرُهُمْ لَا يَعْقِلُونَ
Amharic Translation - Africa Academy63. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከሰማይ ውሃን ያወረደና በእርሱም ምድርን ከሞተች በኋላ ሕያው ያደረጋት ማን እንደሆነ ብትጠይቃቸው "አላህ ነው" ይሉሃል:: "ስለዚህ ምስጋና ሁሉ ለአላህ ነው።“ በላቸው:: ግን አብዛኞቻቸው ይህን አያውቁም።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَمَا هَٰذِهِ ٱلْحَيَوٰةُ ٱلدُّنْيَآ إِلَّا لَهْوٌ وَلَعِبٌ وَإِنَّ ٱلدَّارَ ٱلْـَٔاخِرَةَ لَهِىَ ٱلْحَيَوَانُ لَوْ كَانُوا۟ يَعْلَمُونَ
Amharic Translation - Africa Academy64. ይህም የቅርቢቱ ሕይወት መታለያና ጨዋታ እንጂ ሌላ አይደለም:: የመጨረሻይቱም አገር እርሷ በእርግጥ የዘላለም ህይወት አገር ናት:: የሚያውቁ ቢሆኑ ኖሮ ጠፊይቱን ሕይወት አይመርጡም ነበር::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَإِذَا رَكِبُوا۟ فِى ٱلْفُلْكِ دَعَوُا۟ ٱللَّهَ مُخْلِصِينَ لَهُ ٱلدِّينَ فَلَمَّا نَجَّىٰهُمْ إِلَى ٱلْبَرِّ إِذَا هُمْ يُشْرِكُونَ
Amharic Translation - Africa Academy65. በመርከቦች ውስጥ በተሳፈሩ ጊዜም አላህን መገዛትን ለእርሱ ብቻ ያጠሩ ሆነው ይጠሩታል:: ወደ የብስ በማውጣት ባዳናቸው ጊዜ ግን ወዲያውኑ እነርሱ ጣዖትን ያጋራሉ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
لِيَكْفُرُوا۟ بِمَآ ءَاتَيْنَٰهُمْ وَلِيَتَمَتَّعُوا۟ فَسَوْفَ يَعْلَمُونَ
Amharic Translation - Africa Academy66. በሰጠናቸው ጸጋ ሊክዱና ሊጠቃቀሙ ያጋራሉ፤ ወደ ፊትም የሚጠብቃቸውን ያውቃሉ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَوَلَمْ يَرَوْا۟ أَنَّا جَعَلْنَا حَرَمًا ءَامِنًا وَيُتَخَطَّفُ ٱلنَّاسُ مِنْ حَوْلِهِمْ أَفَبِٱلْبَٰطِلِ يُؤْمِنُونَ وَبِنِعْمَةِ ٱللَّهِ يَكْفُرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy67. ሰዎቹ ከየዙሪያቸው ሲነጠቁ እኛ አገራቸውን ጸጥተኛ ክልል ማድረጋችንን አያዩምን? በውድቅ ነገር ያምናሉን? በአላህም ጸጋ ይክዳሉን?
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَمَنْ أَظْلَمُ مِمَّنِ ٱفْتَرَىٰ عَلَى ٱللَّهِ كَذِبًا أَوْ كَذَّبَ بِٱلْحَقِّ لَمَّا جَآءَهُۥٓ أَلَيْسَ فِى جَهَنَّمَ مَثْوًى لِّلْكَٰفِرِينَ
Amharic Translation - Africa Academy68. በአላህ ላይ ውሸትን ከቀጣጠፈ ሰው ወይም እውነት በመጣለት ጊዜ ከአስዋሸ ሰው ይበልጥ ራሱን በዳይ ማነው? በገሀነም ውስጥ ለከሓዲያን መኖሪያ የለምን?(አለ)
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَٱلَّذِينَ جَٰهَدُوا۟ فِينَا لَنَهْدِيَنَّهُمْ سُبُلَنَا وَإِنَّ ٱللَّهَ لَمَعَ ٱلْمُحْسِنِينَ
Amharic Translation - Africa Academy69. እነዚያም በእኛ መንገድ የታገሉ ህዝቦችን መንገዳችንን በእርግጥ እንመራቸዋለን:: አላህ በእርግጥ ከበጎ ሰሪዎች ጋር ነውና፡:
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
→