قَالَ يَٰقَوْمِ أَرَءَيْتُمْ إِن كُنتُ عَلَىٰ بَيِّنَةٍ مِّن رَّبِّى وَرَزَقَنِى مِنْهُ رِزْقًا حَسَنًا وَمَآ أُرِيدُ أَنْ أُخَالِفَكُمْ إِلَىٰ مَآ أَنْهَىٰكُمْ عَنْهُ إِنْ أُرِيدُ إِلَّا ٱلْإِصْلَٰحَ مَا ٱسْتَطَعْتُ وَمَا تَوْفِيقِىٓ إِلَّا بِٱللَّهِ عَلَيْهِ تَوَكَّلْتُ وَإِلَيْهِ أُنِيبُ
Amharic Translation - Africa Academy88. (እርሱም) አለ: «ህዝቦቼ ሆይ! ንገሩኝ እስቲ ከጌታዬ በሆነ አስረጅ ላይ ሆኜ ከእርሱም የሆነን መልካም ሲሳይ ቢሰጠኝ በቅጥፈት ልቀላቅለው ይገባልን? የከለከልኳችሁንም ነገር በመፈጸም ልለያችሁ አልሻም:: በተቻለኝ ያህል ማበጀትን እንጂ አልሻም:: ለደግ ሥራ መታደሌ በአላህ ፈቃድ ብቻ እንጂ በሌላ አይደለም:: በእርሱ ላይ ብቻ ተመካሁ:: ወደ እርሱም እመለሳለሁ።
Amharic Translation - Muhammad Sadiq«ሕዝቦቼ ሆይ! ንገሩኝ፤ ከጌታዬ በሆነ አስረጅ ላይ ብሆንና ከእርሱም የሆነን መልካም ሲሳይ ቢሰጠኝ (በቅጥፈት ልቀላቅለው ይገባልን) ከእርሱ ወደ ከለከልኳችሁም ነገር ልለያችሁ አልሻም፡፡ በተቻለኝ ያክል ማበጀትን እንጂ አልሻም (ለደግ ሥራ) መገጠሜም በአላህ እንጂ በሌላ አይደለም፡፡ በእርሱ ላይ ተመካሁ፡፡ ወደእርሱም እመለሳለሁ፤» አላቸው፡፡