قَالُوا۟ يَٰلُوطُ إِنَّا رُسُلُ رَبِّكَ لَن يَصِلُوٓا۟ إِلَيْكَ فَأَسْرِ بِأَهْلِكَ بِقِطْعٍ مِّنَ ٱلَّيْلِ وَلَا يَلْتَفِتْ مِنكُمْ أَحَدٌ إِلَّا ٱمْرَأَتَكَ إِنَّهُۥ مُصِيبُهَا مَآ أَصَابَهُمْ إِنَّ مَوْعِدَهُمُ ٱلصُّبْحُ أَلَيْسَ ٱلصُّبْحُ بِقَرِيبٍ
Amharic Translation - Africa Academy81. «ሉጥ ሆይ! እኛ የጌታህ መልዕክተኞች ነን:: ህዝቦች ወደ አንተ በክፉ አይደርሱብህም:: ቤተሰብህንም ይዘህ ከሌሊቱ በከፊሉ ውስጥ ሂድ:: ከናንተም አንድም ወደ ኋላው አይገላመጥ:: ሚስትህ ብቻ ስትቀር:: እነሆ እርሷንማ እነርሱን የሚያገኛቸው ስቃይ ሁሉ ያገኛታልና:: ቀጠሯቸው ንጋቱ ላይ ነው:: ንጋቱ ቅርብ አይደለምን?» አሉት።
Amharic Translation - Muhammad Sadiq«ሉጥ ሆይ! እኛ የጌታህ መልክተኞች ነን፡፡ (ሕዝቦችህ) ወደ አንተ (በክፉ) አይደርሱብህም፡፡ ቤተሰብህንም ይዘህ ከሌሊቱ በከፊሉ ውስጥ ሊድ፡፡ ከእናንተም አንድም (ወደኋላው) አይገላመጥ፡፡ ሚስትህ ብቻ ስትቀር፡፡ እነሆ እርሷን (እነሱን) የሚያገኛቸው ስቃይ ያገኛታልና፡፡ ቀጠሯቸው እንጋቱ ላይ ነው፡፡ ንጋቱ ቅርብ አይደለምን» አሉት፡፡