caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Hud፣ አንቀጽ 17

መካ · የወረደበት ቅደም ተከተል 52 · 11:17

أَفَمَن كَانَ عَلَىٰ بَيِّنَةٍ مِّن رَّبِّهِۦ وَيَتْلُوهُ شَاهِدٌ مِّنْهُ وَمِن قَبْلِهِۦ كِتَٰبُ مُوسَىٰٓ إِمَامًا وَرَحْمَةً أُو۟لَٰٓئِكَ يُؤْمِنُونَ بِهِۦ وَمَن يَكْفُرْ بِهِۦ مِنَ ٱلْأَحْزَابِ فَٱلنَّارُ مَوْعِدُهُۥ فَلَا تَكُ فِى مِرْيَةٍ مِّنْهُ إِنَّهُ ٱلْحَقُّ مِن رَّبِّكَ وَلَٰكِنَّ أَكْثَرَ ٱلنَّاسِ لَا يُؤْمِنُونَ

Amharic Translation - Africa Academy17. ከጌታው ዘንድ አስረጅ የደረሰውንና ከእርሱም የሆነ መስካሪ የሚከተለው ከቁርኣን በፊትም ለሙሳ መጽሐፍ መሪና እዝነት ሲሆን የመሰከረለት (ሰውና) የቅርቢቱን ህይወት እንደሚሻው (ሰው) ነውን? እነዚያ በእርሱ (ቁርኣን) ያምናሉ:: ከአህዛቦቹ በእርሱ የሚክድ ሰው ሁሉ መመለሻው እሳት ናት:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከእርሱም በመጠራጠር ውስጥ አትሁን:: እሱ ከጌታህ ዘንድ የሆነ እውነት ነው:: ግን አብዛኞቹ ሰዎች አያምኑም::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqከጌታው ከአስረጅ ጋር የኾነ ሰው፤ ከእርሱም (ከአላህ) የኾነ መስካሪ የሚከተለው፣ ከእርሱ በፊትም የሙሳ መጽሐፍ መሪና እዝነት ሲኾን (የመሰከረለት) (የቅርቢቱን ሕይወት እንደሚሻው ሰው ነውን?) እነዚያ በእርሱ (በቁርኣን) ያምናሉ፡፡ ከአሕዛቦቹም በእርሱ የሚክድ ሰው እሳት መመለሻው ናት፡፡ ከእርሱም በመጠራጠር ውስጥ አትሁን፡፡ እርሱ ከጌታህ የሆነ እውነት ነው፡፡ ግን አብዛኞቹ ሰዎች አያምኑም፡፡
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70