caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Hud፣ አንቀጽ 7

መካ · የወረደበት ቅደም ተከተል 52 · 11:7

وَهُوَ ٱلَّذِى خَلَقَ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضَ فِى سِتَّةِ أَيَّامٍ وَكَانَ عَرْشُهُۥ عَلَى ٱلْمَآءِ لِيَبْلُوَكُمْ أَيُّكُمْ أَحْسَنُ عَمَلًا وَلَئِن قُلْتَ إِنَّكُم مَّبْعُوثُونَ مِنۢ بَعْدِ ٱلْمَوْتِ لَيَقُولَنَّ ٱلَّذِينَ كَفَرُوٓا۟ إِنْ هَٰذَآ إِلَّا سِحْرٌ مُّبِينٌ

Amharic Translation - Africa Academy7. አላህ ያ ሰማያትንና ምድርን በስድስት ቀናት ውስጥ የፈጠረ ነው:: ዐርሹም በውሃ ላይ ነበር:: የትኛችሁ ስራችሁ ያማረ መሆኑ ይፈትናችሁ ዘንድ ፈጠራችሁ:: «እናንተ ከሞት በኋላ በእርግጥ ተቀስቃሾች ናችሁ» ብትልም። እነዚያ የካዱት «ይህ ግልጽ ድግምት እንጂ ሌላ አይደለም።» ይላሉ::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqእርሱም ያ ሰማያትንና ምድርን በስድስት ቀኖች ውስጥ የፈጠረ ነው፡፡ ዐርሹም በውሃ ላይ ነበር፡፡ የትኛችሁ ሥራው ያማረ መሆኑን ይፈትናችሁ ዘንድ (ፈጠራቸው)፡፡ «እናንተ ከሞት በኋላ በእርግጥ ተቀስቃሾች ናችሁ» ብትልም እነዚያ የካዱት ይህ ግልጽ ድግምት እንጂ ሌላ አይደለም ይላሉ፡፡
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70