فَلَوْلَا كَانَ مِنَ ٱلْقُرُونِ مِن قَبْلِكُمْ أُو۟لُوا۟ بَقِيَّةٍ يَنْهَوْنَ عَنِ ٱلْفَسَادِ فِى ٱلْأَرْضِ إِلَّا قَلِيلًا مِّمَّنْ أَنجَيْنَا مِنْهُمْ وَٱتَّبَعَ ٱلَّذِينَ ظَلَمُوا۟ مَآ أُتْرِفُوا۟ فِيهِ وَكَانُوا۟ مُجْرِمِينَ
Amharic Translation - Africa Academy116. ከናንተ በፊት ከነበሩት ከክፍለ ዘመናት (ሰዎች) ውስጥ በምድር ላይ ከማበላሸት የሚከለክሉ የመልካም ሥራዎች ቅሪት ባለቤቶች ለምን አልነበሩም? ግን ከእነርሱ ያዳንናቸው ጥቂቶቹ ከለከሉና ዳኑ:: እነዚያም የበደሉት ሰዎች አልከለከሉም። በእርሱ የተቀማጠሉበትን ተድላ ተከተሉ አመጠኞችም ነበሩ::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqከእናንተም በፊት ከነበሩት ከክፍለ ዘመናት ሰዎች ውስጥ በምድር ላይ ከማበላሸት የሚከለክሉ የመልካም ቀሪ ሥራዎች ባለቤቶች ለምን አልነበሩም? ግን ከእነሱ ያዳንናቸው ጥቂቶቹ (ከለከሉና ዳኑ)፡፡ እነዚያም የበደሉት ሰዎች (አልከለከሉም)፡፡ በእርሱ የተቀማጠሉበትን ተድላ ተከተሉ፡፡ አመጸኞችም ነበሩ፡፡