وَهِىَ تَجْرِى بِهِمْ فِى مَوْجٍ كَٱلْجِبَالِ وَنَادَىٰ نُوحٌ ٱبْنَهُۥ وَكَانَ فِى مَعْزِلٍ يَٰبُنَىَّ ٱرْكَب مَّعَنَا وَلَا تَكُن مَّعَ ٱلْكَٰفِرِينَ
Amharic Translation - Africa Academy42. እርሷም እንደ ተራራዎች በሆነ ማዕበል ውስጥ እነርሱን ይዛቸው የምትንሻለል ስትሆን (በአላህ ስም ተቀመጡባት።) ኑህም ልጁን ከመርከቢቱ የራቀ ሆኖ ሳለ «ልጄ ሆይ! ከእኛ ጋር ተሳፈር። ከከሓዲያንም አትሁን።» ሲል ጠራው።
Amharic Translation - Muhammad Sadiqእርሷም እንደ ተራራዎች በሆነ ማዕበል ውስጥ በእነርሱ (ይዛቸው) የምትንሻለል ስትሆን (በአላህ ስም ተቀመጡባት)፡፡ ኑሕም ልጁን ከመርከቢቱ የራቀ ሆኖ ሳለ «ልጄ ሆይ! ከኛ ጋር ተሳፈር ከከሓዲዎቹም አትሁን» ሲል ጠራው፡፡