فَلَعَلَّكَ تَارِكٌۢ بَعْضَ مَا يُوحَىٰٓ إِلَيْكَ وَضَآئِقٌۢ بِهِۦ صَدْرُكَ أَن يَقُولُوا۟ لَوْلَآ أُنزِلَ عَلَيْهِ كَنزٌ أَوْ جَآءَ مَعَهُۥ مَلَكٌ إِنَّمَآ أَنتَ نَذِيرٌ وَٱللَّهُ عَلَىٰ كُلِّ شَىْءٍ وَكِيلٌ
Amharic Translation - Africa Academy12. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «በእርሱ ላይ (የሀብት) ድልብ ለምን አልተወረደም? ወይም ከእርሱ ጋር መልአክ ለምን አልመጣም?» ማለታቸውን በመፍራት ወደ አንተ ከሚወርደው ከፊሉን ልትተው በእርሱም ልብህ ጠባብ ሊሆን ይፈራልሃል:: አንተ አስፈራሪ ብቻ ነህ:: አላህ በሁሉ ነገር ላይ (ወኪል) ተጠባባቂ ነው::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqበእርሱ ላይ የገንዘብ ድልብ ለምን አልተወረደም ወይም ከርሱ ጋር መልአክ ለምን አልመጣም ማለታቸውንም በመፍራት ወደ አንተ ከሚወርደው ከፊሉን ልትተው በእርሱም ልብህ ጠባብ ሊኾን ይፈራልሃል፡፡ አንተ አስፈራሪ ብቻ ነህ፡፡ አላህም በነገሩ ሁሉ ተጠባባቂ ነው፡፡