ذَٰلِكَ ٱلَّذِى يُبَشِّرُ ٱللَّهُ عِبَادَهُ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ وَعَمِلُوا۟ ٱلصَّٰلِحَٰتِ قُل لَّآ أَسْـَٔلُكُمْ عَلَيْهِ أَجْرًا إِلَّا ٱلْمَوَدَّةَ فِى ٱلْقُرْبَىٰ وَمَن يَقْتَرِفْ حَسَنَةً نَّزِدْ لَهُۥ فِيهَا حُسْنًا إِنَّ ٱللَّهَ غَفُورٌ شَكُورٌ
Amharic Translation - Africa Academy23. (ይህ ታላቅ ችሮታ) ያ አላህ እነዚያን በትክክል ያመኑትንና መልካሞችን የሰሩት ባሮቹን የሚያበስርበት ነው::(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) መልዕክቴን በማድረሴ ላይ የዝምድና ውዴታየን እንጂ ሌላ ዋጋ አልጠይቃችሁም በላቸው:: መልካም ስራ የሚሰራ ሰው ሁሉ ለእርሱ በእርሷ ላይ መልካምን ነገርን እንጨምርለታለን:: አላህ መሀሪ እና አመስጋኝ ነውና::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqይህ (ታላቅ ችሮታ) ያ አላህ እነዚያን ያመኑትንና መልካሞችን የሠሩትን ባሮቹን የሚያበስርበት ነው፡፡ «በእርሱ (መልክቴን በማድረሴ) ላይ በዝምድና ውዴታን እንጅ ዋጋን አልጠይቃችሁም» በላቸው፡፡ መልካሚቱንም ሥራ የሚሠራ ሰው ለእርሱ በእርሷ መልካምን ነገር እንጨምርለታለን፡፡ አላህ መሓሪ አመስጋኝ ነውና፡፡