وَمَا تَفَرَّقُوٓا۟ إِلَّا مِنۢ بَعْدِ مَا جَآءَهُمُ ٱلْعِلْمُ بَغْيًۢا بَيْنَهُمْ وَلَوْلَا كَلِمَةٌ سَبَقَتْ مِن رَّبِّكَ إِلَىٰٓ أَجَلٍ مُّسَمًّى لَّقُضِىَ بَيْنَهُمْ وَإِنَّ ٱلَّذِينَ أُورِثُوا۟ ٱلْكِتَٰبَ مِنۢ بَعْدِهِمْ لَفِى شَكٍّ مِّنْهُ مُرِيبٍ
Amharic Translation - Africa Academy14. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የሃይማኖት ሰዎች እውቀት ከመጣላቸው በኋላ በመካከላቸው ባለ ወሰን አላፊነት እንጂ በሌላ አልተለያዩም:: እስከተወሰነ ጊዜ በማቆየት ከጌታህ ያለፈች ቃል ባልነበረች ኖሮ በእነርሱ መካከል አሁኑኑ በተፈረደ ነበር:: እነዚያም ከኋላቸው መጽሐፍን እንዲወርሱ የተደረጉት ከእርሱ በእርግጥ ባወላዋይ ጥርጣሬ ውስጥ ናቸው::
Amharic Translation - Muhammad Sadiq(የሃይማኖት ሰዎች) ዕውቀቱም ከመጣላቸው በኋላ በመካከላቸው ለምቀኝነት እንጅ ለሌላ አልተለያዩም፡፡ እስከ ተወሰነም ጊዜ (በማቆየት) ከጌታህ ያለፈች ቃል ባልነበረች ኖሮ በእነርሱ መካከል (አሁን) በተፈረደ ነበር፡፡ እነዚያም ከኋላቸው መጽሐፉን እንዲወርሱ የተደረጉት ከእርሱ በእርግጥ በአወላዋይ ጥርጣሬ ውስጥ ናቸው፡፡