caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Ash-Shura፣ አንቀጽ 18

መካ · የወረደበት ቅደም ተከተል 62 · 42:18

يَسْتَعْجِلُ بِهَا ٱلَّذِينَ لَا يُؤْمِنُونَ بِهَا وَٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ مُشْفِقُونَ مِنْهَا وَيَعْلَمُونَ أَنَّهَا ٱلْحَقُّ أَلَآ إِنَّ ٱلَّذِينَ يُمَارُونَ فِى ٱلسَّاعَةِ لَفِى ضَلَٰلٍۭ بَعِيدٍ

Amharic Translation - Africa Academy18. እነዚያ በእርሷ የማያምኑት በእርሷ ያቻኩላሉ:: እነዚያ በአላህ ያመኑት ግን ከእርሷ ፈሪዎች ናቸው:: እርሷ እውነት መሆኗንም በትክክል ያውቃሉ:: (ሙስሊሞች ሆይ!) አስተውሉ:: እነዚያ በሰዓቲቱ የሚከራከሩ ሰዎች ሁሉ በእርግጥ ከእውነት በራቀ ስህተት ውስጥ ናቸው::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqእነዚያ በእርሷ የማያምኑት በእርሷ ያቻኩላሉ፡፡ እነዚያም ያመኑት ከእርሷ ፈሪዎች ናቸው፡፡ እርሷም እውነት መኾንዋን ያውቃሉ፡፡ ንቁ! እነዚያ በሰዓቲቱ የሚከራከሩት በእርግጥ (ከእውነት) በራቀ ስሕተት ውስጥ ናቸው፡፡
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70