شَرَعَ لَكُم مِّنَ ٱلدِّينِ مَا وَصَّىٰ بِهِۦ نُوحًا وَٱلَّذِىٓ أَوْحَيْنَآ إِلَيْكَ وَمَا وَصَّيْنَا بِهِۦٓ إِبْرَٰهِيمَ وَمُوسَىٰ وَعِيسَىٰٓ أَنْ أَقِيمُوا۟ ٱلدِّينَ وَلَا تَتَفَرَّقُوا۟ فِيهِ كَبُرَ عَلَى ٱلْمُشْرِكِينَ مَا تَدْعُوهُمْ إِلَيْهِ ٱللَّهُ يَجْتَبِىٓ إِلَيْهِ مَن يَشَآءُ وَيَهْدِىٓ إِلَيْهِ مَن يُنِيبُ
Amharic Translation - Africa Academy13. (ሰዎች ሆይ!) ለእናንተ ከሃይማኖት ያንን በእርሱ ኑህን ያዘዘበትን ያንንም ወደ አንተ ያወረድነውን ያንንም ኢብራሂምን፤ ሙሳንና ዒሳንም በእርሱ ያዘዝንበት የሆነውን ሃይማኖትን በትክክል አቋቁሙ በእርሱም ላይ አትለያዩ በማለት ደነገገላችሁ::(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በአላህ አጋሪዎች ያ ወደ እርሱ የምትጠራቸው ነገር (ኢስላም) ከበዳቸው:: አላህ የሚፈልገውን ሰው ወደ እርሱ እምነት ይመርጣል:: የሚመለስንም ሰው ወደ እርሱ ይመራል::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqለእናንተ ከሃይማኖት ያንን በእርሱ ኑሕን ያዘዘበትን ደነገገላችሁ፡፡ ያንንም ወዳንተ ያወረድነውን ያንንም በእርሱ ኢብራሂምን ሙሳንና ዒሳንም ያዘዝንበትን ሃይማኖትን በትክክል አቋቁሙ በእርሱም አትለያዩ ማለትን (ደነገግን)፡፡ በአጋሪዎቹ ላይ ያ ወደርሱ የምትጠራቸው ነገር ከበዳቸው፡፡ አላህ የሚሻውን ሰው ወደእርሱ (እምነት) ይመርጣል፡፡ የሚመለስንም ሰው ወደርሱ ይመራል፡፡