تَرَى ٱلظَّٰلِمِينَ مُشْفِقِينَ مِمَّا كَسَبُوا۟ وَهُوَ وَاقِعٌۢ بِهِمْ وَٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ وَعَمِلُوا۟ ٱلصَّٰلِحَٰتِ فِى رَوْضَاتِ ٱلْجَنَّاتِ لَهُم مَّا يَشَآءُونَ عِندَ رَبِّهِمْ ذَٰلِكَ هُوَ ٱلْفَضْلُ ٱلْكَبِيرُ
Amharic Translation - Africa Academy22. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በደለኞችን በሰሩት ስራ ዋጋ በትንሳኤ ቀን ፈሪዎች ሆነው ታያቸዋለህ:: እርሱም በእነርሱ ላይ የማይቀር ወዳቂ ነው:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚያም በአላህ ያመኑና መልካም ስራን የሰሩ ሁሉ በገነት ጨፌዎች ዉስጥ ናቸው:: ለእነርሱም በጌታቸው ዘንድ የሚፈልጉት ሁሉ አለላቸው:: ይህ ታላቅ ችሮታ ነው::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqበደለኞችን ከሠሩት ሥራ (ዋጋ በትንሣኤ ቀን) ፈሪዎች ኾነው ታያቸዋለህ፡፡ እርሱም በእነርሱ ላይ ወዳቂ ነው፡፡ እነዚያም ያመኑት መልካሞችንም የሠሩት በገነቶች ጨፌዎች ውስጥ ናቸው፡፡ ለእነርሱ በጌታቸው ዘንድ የሚሹት ሁሉ አልላቸው፡፡ ይህ እርሱ ታላቅ ችሮታ ነው፡፡