caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Ash-Shura፣ አንቀጽ 15

መካ · የወረደበት ቅደም ተከተል 62 · 42:15

فَلِذَٰلِكَ فَٱدْعُ وَٱسْتَقِمْ كَمَآ أُمِرْتَ وَلَا تَتَّبِعْ أَهْوَآءَهُمْ وَقُلْ ءَامَنتُ بِمَآ أَنزَلَ ٱللَّهُ مِن كِتَٰبٍ وَأُمِرْتُ لِأَعْدِلَ بَيْنَكُمُ ٱللَّهُ رَبُّنَا وَرَبُّكُمْ لَنَآ أَعْمَٰلُنَا وَلَكُمْ أَعْمَٰلُكُمْ لَا حُجَّةَ بَيْنَنَا وَبَيْنَكُمُ ٱللَّهُ يَجْمَعُ بَيْنَنَا وَإِلَيْهِ ٱلْمَصِيرُ

Amharic Translation - Africa Academy15. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ወደ እዚህ መንገድም ጋኔንንና ሰዎችን ጥራ:: ልክ እንደታዘዝከዉም ቀጥ በል:: ዝንባሌያቸውን አትከተል:: «ከመጽሐፍም አላህ ባወረደው ሁሉ አመንኩ:: በመካከላችሁ በፍርድ ላስተካክልም ታዘዝኩ:: አላህ ጌታችን ጌታችሁም ነው:: ለእኛ ስራዎቻችን አሉን:: ለእናንተም እንዲሁ ስራዎቻችሁ አሏችሁ:: በእኛና በእናንተ መካከል ክርክር የለም:: አላህ በመካከላችን ይሰበስባል:: መመለሻው ወደ እርሱ ብቻ ነው።» በላቸው::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqለዚህም (ድንጋጌ ሰዎችን) ጥራ፡፡ እንደታዘዝከውም ቀጥ በል፡፡ ዝንባሌዎቻቸውንም አትከተል፡፡ «በላቸውም ከመጽሐፍ አላህ ባወረደው ሁሉ አመንኩ፡፡ በመካከላችሁም ላስተካክል ታዘዝኩ፡፡ አላህ ጌታችን ጌታችሁም ነው፡፡ ለእኛ ሥራዎቻችን አልሉን፡፡ ለእናንተም ሥራዎቻችሁ አልሏችሁ፡፡ በእኛና በእናንተ መካከል ክርክር የለም፡፡ አላህ በመካከላችን ይሰበስባል፡፡ መመለሻም ወደእርሱ ብቻ ነው፡፡»
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70